TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19ETHIOPIA

በደሴ ከተማ 30 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል!

በደሴ ከተማ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዘ ግለሰብ መገኘቱን ተከትሎ ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ 30 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ #ለአብመድ አሳውቋል።

የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያለው ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ የናሙና ምርመራ ተደርጎለት ግንቦት 15/2012 ዓ.ም የኮሮና ቫይረስ እንዳለበት ተረጋግጧል፡፡

አሽከርካሪው አማራ ክልል ከገባ በኋላ መጋቢት 10/2012 ዓ.ም ጋሼና ከተማ ጭነት አራግፎ፣ ወልድያ አድሮ በማግስቱ ወደ #ደሴ ከተማ አስተዳደር መሄዱ ታውቋል፡፡

ወደ ከተማ አስተዳደሩ በገባ በማግስቱ የጤና ባለሙያዎች ጥቆማ ደርሷቸው ወደ ቤቱ ቢሄዱም ስላላገኙት ለሁለት ቀናት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

ግንቦት 11/9/2012 ዓ.ም ወደ ከተማው የገባው ግለሰቡ በ13/2012 ማለዳ በግል ሆስፒታል ለህክምና በሄደበት ተገኝቶ ነበር ወደ ለይቶ ማቆያ የገባው፡፡

በዕለቱ አሽከርካሪውን ጨምሮ ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ አምስት (5) የሆስፒታሉ ሰራተኞች ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል https://telegra.ph/AMMA-05-25

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ደሴ

የኢትዮጵያ 🇪🇹 ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ደሴ ገቡ።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ደሴ የገቡት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ወገኖችን ለመጎብኘት ነው።

የደሴ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል ፥ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ተፈናቅለው ደሴ የሚገኙ 300 ሺህ ዜጎች እንዳሉ አሳውቀዋል።

የፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጉብኝትም ተፈናቃዮች ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ በትክክል ለመረዳት እንደሆነ ገልፀዋል።

ከጉብኝታቸው በኋላም ለተፈናቃዮች ድጋፍ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከንቲባው አስታውቀዋል።

Photo Credit : ENA

@tikvahethiopia
#Dessise #Kombolcha

በዛሬው ዕለት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የ #ደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ሲሾሙ አቶ መሀመድ አሚን ደግሞ የ #ኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።

የደሴ ከተማ አሰተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት 31ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

በሌላ በኩል የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ መሀመድ አሚን ኮምቦልቻ ከተማን በከንቲባነት እንዲመሩ ሾሟቸዋል።

@tikvahethiopia
#ደሴ

በቆሻሻ ማቃጠያ ውስጥ የነበረ የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ ፈንድቶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

በደሴ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ስልክ አምባ ትምህርት ቤት በተለምዶ ሚካኤል ጀርባ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በነበረ የቆሻሻ ማቃጠያ ቦታ ከቆሻሻ ማቃጠያው የወዳደቁ የቁራሊዬ እቃዎችን እየሰበሰቡ የነበሩ ሶስት የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ ፈንድቶ በሶስቱም ላይ ጉዳት አድርሷል።

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችም በአሁኑ ሰአት የህክምና አገልግሎት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የከተማው ማህበረሰብ አካባቢውን በሚገባ በመፈትሽ የተለየ ነገር ካገኘ ባቅራቢያ ለሚገኝ የጸጥታ ሀይል ጥቆማ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው የደሴ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#ደሴ

" 11 ሰዎች ቆስለዋል ፤ በእንሰሳት ላይ ሞትና ከፍተኛ ቁስለት ደርሷል " - የደሴ ከተማ አስተዳደር

በደሴ ከተማ ፤ በሰኞ ገበያ ሳላይሽ ቀበሌ አካባቢ ቆራሊዮ የሚያከማቹ ሰዎች ቆራሊዮ ከመኪና ሲያራግፉ ቦንብ ፈንድቶ 11 ሰዎች ቆስለዋል።

በእንስሳት ላይም ሞትና ከፍተኛ ቁስለት ደርሷል።

ፍንዳታው ያጋጠመው ዛሬ 5:30 ላይ ሲሆን በቆራሊዮ መጋዘን ከመኪና ላይ ወርዶ ሚዛን ሲመዘን ከነበረ ኬሻ ውስጥ የፈነዳ ቦንብ 11 ሰዎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ 3 በጎችን እና 1 ፍየልን ገድሎ 15 በጎችን ለጉዳት ዳርጓል።

በቦታው ላይ የበኣል የፍየል እና የበግ ግብይት ስለነበር ብዙ ሰዎችና እንስሳት እንዲጎዱ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በግ ሲገዙ የነበሩ እና የቀን ሰራተኞች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ተጎጂዎች ወደ ሆሰፒታል ተወስደዋል።

መረጃው ከደሴ ከተማ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#ደሴ

ከደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተዘርፈው ሊወጡ የነበሩ የህክምና ቁሳቁሶች ተያዙ።

ትላንት ነሀሴ 2 በግምት ከሌሊቱ 6 ሰአት ከደሴ ከተማ አጠቃላይ ስፔሻለይዝድ ሆስፒታል ከ638 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ማሽን ተሠርቀው ሊወጡ ሲሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገለፀ።

ተሰርቆ ሊወጣ የነበረው ፦

- የላብራቶሪ ማሽን 4 ኦሎምፐስ (olomps) ማይክሮስኮፕ፣
- 1 ላቦመድ (labomed) ማይክሮስኮፕ፣
- 1 የኬሚስትሪ ማሽን(ዲያሚንሽን ማሽን ትንሿ ፕሪንተር፣
- 1 NEO-BIL የቢል ማሽን፣
- 5 አዲስ ዶግለር የበር ቁልፍና የተለያዩ የኤሌትሪክ ገመድና ቁሳቁስ ነው።

የህክምና ቁሳቁሶቹ ሰርቀው ሊወጡ ሲሉ እጅ ከፍንጅ በጥበቃ ሰራተኞች የተያዙ ግለሰቦች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው።

ድርጊቱን የፈፀሙ ግለሰቦችን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ አልተገለፀም።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሃይማኖት አየለ ፤ ከአሁን በፊትም #በሆስፒታሉ_ሰራተኞች ከ6 መቶ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ ለክሮኒክ በሽታ የሚታዘዙ መድሀኒትና ሌሎች መድሀኒቶች መዘረፉን ተነግረዋል።

ዘረፋ ያካሄዱ 3 ሰራተኞች ከስራ ተባረው በህግ እንዲጠየቁ ሲደረገ አንድ ባለሙያ ላይ ከደረጀ ዝቅ እንዲል መደረጉን ገልፀዋል።

ዶ/ር ሃይማኖት ፤ " የጥበቃ ስራውን አጠናክረን ስንቀሳቀስ የስርቆት ወንጀሉ ከውጭና ከውስጥ የተያያዘ ቁርኝት ያላቸው የሌብነት ሰንሰለት እንዳለ ተረድተናልና ህብረተሠቡ ሊያግዘንና ሊተባበረን ይገባል " ብለዋል።

መረጃውን ከደሴ ኮሚኒኬሽን ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ደቡብ_ወሎ በደቡብ ወሎ ከታች ቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ህዝቡን እንዲረጋጋ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ የሀገር መከላከያን ልብስ በመልበስ መከላከያ በመምሰል በአቋራጭ መንገዶች ሲጓዙ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። በአሉባልታ ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደ ዞኑ እየገቡ መሆኑን የገለፀው…
#Update

#ሰቆጣ

መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮምቦልቻ

ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር።

በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው ተገልጾ መላው ነዋሪ ተረጋግቶ በንቃት አካባቢውን በመጠበቅ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በከተማዋ እስከሁን ባለው ከ400 በላይ ባጃጆች እና 80 ሞተሮች በህግ ቁጥጥር ስር ገብተው ማጣራት ተደርጎ ወደየመጡበት እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ሁሉም ነዋሪ በቀበሌና ቀጠና ብሎክ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትና በእቃ ዋጋ ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ይደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።

#ደሴ

ዛሬ በደሴ ከአምስቱም ክ/ከተሞች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ተደርጎ የነበረ ሲሆን በዚሁ መድረክ ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎችን በማሰራጨት ህዝቡ ላይ የስነልቦና ጫና ለማሳደር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የከተማው ወጣት በሙሉ በሀሰተኛ ወሬ እና በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ሳይረበሽ ከመላው የከተማው ነዋሪ ጋር በመሆን አካባቢውን እና የከተማውን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

በከተማው የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ተነግሯል።

#ወልድያ

ወልዲያ ከተማ አዳሯ ሰላም የነበረ ሲሆን የዛሬ ውሎዋም ሰላም ነው። አሁንም ቢሆን መላው ነዋሪ ተረጋግቶ አካባቢውን በመጠብቅ የከተማዋን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ሰቆጣ መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል። #ኮምቦልቻ ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር። በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው…
#Update

#ወልድያ

ሰሞኑን በአሉባልታና ሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ የተወሰነ አለመረጋጋት ውስጥ የነበረችው ወልድያ ዛሬ ወደ ቀደመ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሷ ተገልጿል። ከከተማዋ ወጥተው የነበሩም ተመልሰዋል። መደበኛ ትራንስፖርት ፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች የመንገድ ዳር አገልግሎቶች ጀምረዋል።

ዛሬ ጥዋት ላይ አቢሲንያ እና ህብረት ባንኮች ስራ መጀመራቸው እና ሌሎች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ መገለፁ ይታወሳል ፤ በዚሁ መሰረት ከሰዓት በከተማው ውስጥ ያሉ ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

#ደሴ

ደሴ ከተማ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለች ሲሆን ህብረተሰቡ አሁንም ከሀሰተኛ መረጃ እና አሉባልታ በመራቅ ሰላሙን ሊያስጠብቅ ይገባዋል። በሀሰተኛ መረጃ አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።

#ኮምቦልቻ

ዛሬም እንደትላንቱ ኮምፖልቻ ከተማ እና ነዋሪዎቿ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሆኑ አሁንም ነዋሪው ተረብሾ አካባቢውን ለቆ ፣ ንብረቱን ጥሎ እንዲወጣ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና አሉባልታዎች ሊኖሩ ይችላሉና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

#ሐይቅ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተሰራጨ የሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ ነዋሪዎችን የመመለስ ስራ በከተማው አስተዳደር እየተሰራ ነው። በተጨማሪ በከተማው የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እንዲሁም የኬላ ላይ ፍተሻ እየተደረገ ሲሆን መላው ነዋሪ የወጡትን ክልከላዎች እና ገደቦች እንዲያከብር ተጠይቋል።

#ሸዋሮቢት

በትላንትናው ዕለት " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች የተገደሉት የሸዋሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት በደብረ ኃይል ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን መፈፀሙን ከተማ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ልክ ጎንደር እንደተደረገው በደብረብርሃን ከተማም ክልከላዎች ተጣሉ። ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ #ህጋዊ_መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል ተብሏል። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ " እንዲቻል በሚል ክልከላዎችን መጣሉን…
#ደሴ

የአማራ ክልል ከተሞች ተመሳሳይ / #አንድአይነት ይዘት ያላቸው ክልከላዎችን እየጣሉ ይገኛሉ።

ማምሻውን የደሴ ከተማ ኮማንድ ፖስት በጎንደር እና ደብረብርሃን የተጣሉትን አይነት ተመሳሳይ ክልከላዎች መጣሉን ገልጿል።

ኮማንድ ፖስቱ የጣላቸው ክልከላዎች ከላይ ተያይዘዋል።

በሌላ በኩል ፤ የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ ለከተማው ነዋሪዎች ባሰራጨው መልዕክት " በከተማው እየተሰራ ያለው ልማት ለደቂቃም ሊስተጓጎል አይገባም። " ብሏል።

" ህዝባችን ሰላም ፣ ልማት እንደሚፈልግ ጠንቅቀን እንረዳለን። " ያለው ኮማንድ ፖስቱ " የደሴ ህዝብ ከእንግዳህ በሴራ እየተጎዳ መቀጠል የለበትም " ሲል ገልጿል።

" ወጣቶቻችን በሆደ ሰፊነት በትዕግስት በስክነት ነገሮች እንዲፈቱ እንደሚፈልጉና ልማቱን ምንም እንቅፋት እንዲፈጠርበት እንደማይፈልጉ ጠንቅቀን እናውቃለን " ሲል የገለፀው ኮማንድ ፖስቱ " መንግስት ህግ ለማስከበር የተደራጀ ኃይል እና ዝግጅት ቢኖረውም ከተማችን ነገሮች በሰከነ መንገድ በውይይት እንደፈቱ ከመፈለግ ታግሰናል። " ብሏል።

የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ " ዋናው ችግር ከሌላ ቦታ በመጡ ኃይሎች አስተባባሪነት እንጂ በከተማው ህዝብ እንዳልሆነ ህዝባችን ልብ ሊል ይገባል " ብሏል።

የደሴ ከተማ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት " ከሌላ ቦታ መጡ " ያላቸው ኃይሎች እነማን እነድሆኑና ከየት እንደመጡ ባወጣው መግለጫ ያለው ነገር የለም / ማብራሪያም አልሰጠም።

@tikvahethiopia
#ደሴ

የደሴ ፖሊስ መምሪያ ፤ በውሸት " ታግቻለሁ " በማለት ቤተሰቦቹን  500 መቶ ሺህ ብር የጠየቀ ግለሰብ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሽ ብር የጠየቀው ግለሰብ አልጋ ቤት ውስጥ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።

ተጠርጣሪው ግለሰብ ከደቡብ ወሎ ዞን ከመካነሰላም ወደ ደሴ በመምጣት ደሴ ከተማ ቧንቧ ውሀ ክፍለ ከተማ በ " ካራ ጉቱ " ከሚባለው አካባቢ ጫካ ውስጥ በመግባት ከጓደኛው ጋር በመመካከር  ጓደኛው የታገተ በማስመሰል እራሱን  በገመድ ዛፍ ጋር በማሰር ፎቶውን ለቤተሰቦቹ በመላክና በስልክ 500 መቶ ሽ ብር ላኩልኝ በማለት ይነግራቸዋል።

ቤተሰቦቹም ደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ 2ኛ/ዋ/ፖ/ጣቢያ ያመለክታሉ።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ግለሰቡ ታግቻለሁ እያለ ሲያወራና ቤተሰቦቹንና የአካባቢውን ሰው እያስጨነቀ እያለ ከሌሊቱ 07:00 ስዓት በህብረተሰቡ ጥቆማ መነኸሪያ አካባቢ አልጋ ቤት  ውስጥ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ሊያውለው ችሏል።

መረጃው የደሴ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#ደሴ

ከደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ህዝብ መኃል በሚገኘው በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ ምክንያት እየተሰቃቁ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ቆሻሻው በሚወገድበት ጊዜ እስከ ቤታቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ይህ ሁኔታ የህፃናት ልጆቻቸውን ጤና እንዲሁም የራሳቸውን ጤና አደጋ ላይ እንደጣለውና እስከ ዛሬ ድረስ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሆስፒታሉ ቢያቀርቡም መፍትሄ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ከህፃናት ልጆቻቸው ጤና የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ ላሉበት ቦታ የሚመጥናቸውን ካሳ ካገኙ ቦታውን ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ደሴ ከደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ህዝብ መኃል በሚገኘው በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ ምክንያት እየተሰቃቁ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ቆሻሻው በሚወገድበት ጊዜ እስከ ቤታቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል። ይህ ሁኔታ የህፃናት ልጆቻቸውን ጤና እንዲሁም የራሳቸውን ጤና አደጋ ላይ እንደጣለውና እስከ ዛሬ ድረስ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሆስፒታሉ ቢያቀርቡም መፍትሄ እንዳላገኙ ገልጸዋል።…
#ደሴ

“ አንድ ቀን ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ እንዲሆኑ ፣ ከቦታው እንዲነሱ የከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ነው የምንጠብቀው ” - ደሴ ሆስፒታል

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ፣ በሆስፒታሉ በኩል የሚቃጠለው ቆሻሻ ወደ ቤታቸው እየገባ እንደተቸገሩ ፣ መጀመሪያ ዝም ብሎ ሜዳ ላይ ሲቃጠል እንደነበር ፣ ዘመናዊ ማስወገጃ ከተሰራ በኋላ ግን ሙሉ ወደ ግቢዎች ውስጥ እንደሚገባ ፣ በተደጋጋሚ ለችግሩ መፍትሄ ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

መንደሮቹ በተለይም ህፃናት ልጆች ያሉባቸው እንደሆኑ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ፣ አሁን ባሉበት ሁኔታ ከመኖር ለቤታቸው የሚመጥን ካሳ ከተከፈላቸው ቦታውን ለቀው መሄድም እንደሚሻላቸው ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት #ቪዲዮም በቃጠሎው ወቅት ቆሻሻው ወደ ቤት እንደሚገባ ያስገነዝባል።

ነዋሪዎቹ ላነሱት ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው  የሆስፒታሉ ባለስልጣን ፤ “ አሁን ያ ሁሉ አልፎ በዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ፣ ሕጋዊ ማስወገጃ ተሰርቶለት፣ ድሮ ከነበረው ችግር የወጣበት ቀን ነው ” ብለው፣ “ ከነበረው ችግር ወጣ ነው እንጂ ችግሩ ብሶ ቀጥሏል አልልም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በእርግጥ #ከሕዝብ_መኖሪያ ሊወጣ ተቋሙ ግድ ነው። አሁን ግን ያለው የቆሻሻ አወጋገድ በአዎሮፓ ህብረት እና በፈረንሳይ መንግሥት ተደግፎ Almost ሰባት ወሩ ከነሐሴ መጨረሻ ጀምሮ ዘመናዊ የሆነ፣ ስታንዳርዱን የጠበቀ ማቃጠያ ተሰርቶለታል ” ነው ያሉት።

እኚሁ ባለስልጣን አክለውም ፣ “ ግን ከሰው መሀል ነው። ያ በሕጋዊ መንገድ ሲቃጠል እንደድሮው እንኳ ብናኝ እንኳ አያርፍባቸውም። ጭሱ ግን ሊሸት ይችላል ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ዘመናዊ ማቀጠያ ቢሰራም ቆሻሻው እየገባ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ባቀረቡት መሠረት ማብራሪያ እንዲሰጡ ለባለስልጣኗ ጥያቄ አቅርቧል።

እሳቸውም ፤ “ ጭሱ ታካሚንም ይረብሻል፣ ከሕዝብ መሀል መሆናችን ነውና ዋናው ትልቁ ችግር። ጭሱማ እንዴት ይቀራል ? ተኔሬተር ነውኮ ግን የሚጨሰው ” ነው ያሉት።

“ እነዚህ አሁን የሚጨስባቸው ጠቅላላ በካዳስከርና በከተማ ማስተር ፕላን የሆስፒታሉ ቦታዎች ናቸው ” ብለው ፣ “ አንድ ቀን ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ እንዲሆኑ፣ ከቦታው እንዲነሱ የከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ነው የምንጠብቀው ፣ እንጂ አሁን ላይ እጅግ የተሻለ ነገር ነው ያለው ” ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም፣ “ ለምን ብትል በጣም ብዙ ተሰቃይተው አልፈዋል፣ ከዚህ አሁን ካለው በላይ። ግን ከጎኑ ያለው ሰው አይሸተውም አልልህም። ግን ከፍታው ከአራት ሜትር በላይ ሆኖ፣ ከአምስት፣ ከስድስት ሜትር በላይ ከፍ ብሎ የሚጨስ የተሰራበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ” ብለዋል። 

“ አሁን ላይ ራሱ ሞዲፋይ አለው ተነሬተሩ። የተሰራው ማቃጠያ #ሞዲፋይ አድርገው አሁንም እዛው ላይ የሰሩት ከፍታውን ካለው ጨምረው ሊሰሩት እያሰቡ ነው። በቅርብ ቀንም ይሰራል። ሁለተኛ ደግሞ ከውጪ ያልገባ ጭስ አልባ ማቃጠያ ማሽን አለን። በቅርብ ጊዜ (ከወር በኋላ) ይደርሳል። ብዙ ነገሮችን የሚቀንስልን ” ሲሉም ተናግረዋል።

ደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ በርካታ ነዋሪዎች ግን ፤ በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ በየዕለቱ ስቃያቸውን እያዩ እንደሆነ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ የትንንሽ ልጆቻቸው ጤና አደጋ ላይ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia