TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️

ባለፈው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሶ ከተማ በፈፀመ ጥቃት #ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት #መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ።

ህዳር 11 ቀን 2011 ማታ ከሶስት ሰዓት በኋላ ታጣቂዎች የቤተሰብ አባላቱን በጥይት ገድለው ቤታቸውንም እንዳቃጠሉ በጥቃቱ ባለቤታቸውንና የባለቤታቸውን ወንድሞች ያጡት የስምንት ልጆች እናት ወ/ሮ #ልኪቱ_ተፈራ ይናገራሉ።

"መጀመሪያ ተኩስ ከከፈቱብን በኋላ ቤት ውስጥ ጭድ ጨምረው እሳት ለኮሱብን። እኔና ልጆቼ በጓሮ በር በኩል አመለጥን። ሌሎቹ ግን እዚያው ተቃጠሉ" በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ።

ልጃቸው አቶ ወጋሪ ፈይሳ በመኖሪያ ቤታቸው በወቅቱ ሃያ አንድ የቤተሰብ አባላት እንደነበሩና ቤታቸውም ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በመሆኑ ደህንነት ተሰምቷቸው እንደነበር ይናገራል።

ነገር ግን ያልጠበቁት ነገር መከሰቱንና በተፈጠረው ነገርም ህፃናት ልጆች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንዳሉም ይገልፃሉ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ ከተማው ውስጥ ግድያ ስለ መከሰቱ መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን እንደማያውቁ ገልፀዋል።

ከጥቃቱ የተረፉ የቤተሰቡ አባላት ሸሽተው የተጠለሉበት አዋሳኝ የምሥራቅ ወለጋ ሃሮ ሊሙ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጋሮማ ቶሎሳ ግድያው ስለመፈፀሙ ማረጋገጫ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"አባቴ ፈይሳ ዲሳሳ፣ ወንድሙ ዲንሳ ዲሳሳን ጨምሮ ስምንት የአጎቶቼ ልጆችን አጥተናል። ግድያው በጣም አሰቃቂ ነበር" ይላሉ አቶ ዋጋሪ።

በተመሳሳይ እለት የቤተሰብ አባላቱን ግድያ ጨምሮ በያሶ ከተማ በተፈፀመ ጥቃት አርባ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን ኗሪዎችና የአዋሳኝ ወረዳ አስተዳዳሪው ቢናገሩም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊው አቶ ሙሳ ግን አስር ሰው ብቻ ስለመገደሉ መረጃ እንዳላቸው ይገልፃሉ።

ሆኖም ግን ጉዳዩን በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ እንደሚያስፈልጋቸው "መንገድ በመዘጋቱ ነገሮችን በቅርበት ማጣራት አልቻልንም" በማለት ተናግረዋል።

አቶ ሙሳ እንደሚሉት የረቡዕ ጥቃት ከመፈፀሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ሁለት የመንግሥት ሰራተኞች ተገድለዋል። አርብ እለትም ደግሞ በካማሼ ሌሎች ሦስት ሰዎች መሞታቸውንም ገልፀዋል።

በያሶ ጥቃቱን የፈፀሙት ታጣቂዎች ከመሆናቸው በዘለለ ስለታጣቂዎቹ እስካሁን ምንም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለ አቶ ሙሳ ይናገራሉ።

'ያፈነገጡ የኦነግ ታጣቂዎች' ለአካባቢው ስጋት እየሆኑ እንደሆነ አቶ ሙሳ ቢናገሩም ያነጋገርናቸው ኗሪዎች እና የአዋሳኝ ወረዳ ሃላፊዎች ግን በአካባቢው #የኦነግ ታጣቂ እንደሌለ ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አራት የካማሺ ዞን ሃላፊዎች አሶሳ ከተማ ስብሰባ ቆይተው ወደ ካማሺ በመመለስ ላይ ሳሉ በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ብዙዎች መገደላቸውንና ወደ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ግን ነገሮችን #ለመቆጣጠር በያሶ ከተማ ፌደራል ፖሊስ፤ በካማሽ ደግሞ መከላከያ ሠራዊት እንደገባ አቶ ሙሳ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሳውላ ከተማ #ረብሻ ሁለት ሰዎች ተገደሉ አምስት ቆሰሉ‼️
.
.
በትናንትናው ዕለት በጋሞ ጎፋ ዞን #ሳውላ_ከተማ በተካሔደ ስብሰባ ላይ በተቀሰቀሰ ኹከት ሁለት ሰዎች #መገደላቸውን እና አምስት መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የሳውላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር #ብስራት_አንበርብር በከተማዋ ሊካሔደ በታቀደው ስብሰባ ላይ የተፈጠረውን ረብሻ ለመቆጣጠር የጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን እና አምስት ሰዎች
መቁሰላቸውን ለ«DW» አረጋግጠዋል።

በስብሰው የተካፈሉ አንድ የአይን እማኝ በዞኑ ጉዳይ ላይ ለመመካከር የተጠራውን ስብሰባ "የሚቃወሙ ብዙ ወጣቶች ወጥተው ነበር። መጨረሻ ላይ እኛን ሊወክሉ የማይችሉ ሰዎች ወደ ስብሰባው መምጣት የለባቸውም በሚል ይመስለኛል" ሲሉ የኹከቱን ምንጭ ተናግረዋል። ስብሰባው እንደታቀደው ሳይካሔድ መቋረጡን የተናገሩት የአይን እማኙ የድንጋይ መወራወር ድርጊት መመልከታቸውም ገልጸዋል።

ኮማንደር ብስራት አንበርብር በበኩላቸው "እንግዶችም ወደ አዳራሹ ሊመጡ አልቻሉም። [ወጣቶቹ] ዙሪያውን ከበቡ። እኛ ስንከላከል በድንጋይ መስታወቶችን መስኮቶችን እየመቱ በአጥር ላይ ዘለው ለመግባት ጥረት ሲደረግ ነው የጸጥታው ኃይል በተኩስ አካባቢውን በተኩስ ለማስለቀቅ ጥረት ያደረገው። ሁለት ሰው እዚያ አካባቢ ሞቷል። አምስት የሚሆኑ ሰዎች ቆስለዋል" ሲሉ አስረድተዋል።

ፖሊስ ግጭቱን በማነሳሳት የተጠረጠሩ ያላቸውን 78 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ኮማንደሩ ጨምረው ተናግረዋል። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የሚገኘው የሳውላ አካባቢ ባለፈው ጥቅምት ወር በዞን ደረጃ እንዲዋቀር ከተነሳ ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳ ግጭት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን DW ዘግቧል።

የክልሉ ምክር ቤት በቅርቡ ባካሔደው መደበኛ ጉባኤ አካባቢው ቀደም ሲል ከነበረበት የጋሞ ጎፋ ዞን በመውጣት ራሱን ችሎ በዞን ደረጃ እንዲዋቀር ወስኗል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ(ሸዋንግዛው-ሀዋሳ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ኦሮሚያ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ በቡርጂና በጉጂ ማህበረሰብ መካከል ግጭት ተቀስቅሶ አራት ሰዎች #መገደላቸውን ንብረት መውደሙንና የተፈናቀሉ መኖራቸውን ነዋሪዎች ለ DW ተናግረዋል። የከተማው ምክትል ከንቲባ ግን ግጭቱ መከሰቱን አምነው ሁለት ሰዎች መሞታቸውንና የተፈናቀለ ግን አለመኖሩን ገልፀዋል።

©DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጊንቢ ከተማ ሁለት ወጣቶች #በታጠቀ ኃይል #መገደላቸውን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ከትላንት በስቲያ አንድ በጉልበት ሥራ የሚተዳደር ወጣት ሲገደል፣ ትላንት ደግሞ የአእምሮ ጤና እክል ያለበት ወጣት ተገድሏል፤ ይላሉ የዓይን እማኞች፡፡ ከትላንት በስቲያ እና ትላንት ከተማውማዋ በከፍተኛ የጦር መሣሪያ ድምፅ ስትታመስ መቆየቷን ነዋሪዎች ተናግረዋል፤ የአካባቢው ኮማንድ ፖስት በበኩሉ #የመከላከያ_ሰራዊት ማንንም አልገደለም ብሏል፡፡

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መነ ቤኛ‼️

ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ መነ ቤኛ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ላይ በጥይት ተመተው #መገደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ።

የዞኑ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ተረፈ፤ የተገደሉት ሁለቱ የፌደራል ፖሊስ አባላት የፊንጫአ ኃይል ማመንጫ እና ጌዶ ከተማ ላይ የሚገኝ የኃይል ማከማቻ ጠባቂዎች ነበሩ ብለዋል።

''መኪና ላይ ሆነው ወደ ፊንጫአ እየተጓዙ ሳሉ ተኩስ ተከፈተባቸው'' በማለት አቶ ደሳለኝ ሁኔታውን ያስረዳሉ።

ጥቃቱን ማን እንደሰነዘረ አልታወቀም የሚሉት አቶ ደሳለኝ የፌደራል ፖሊስ አባላቱ ትናንት እኩለ ቀን ገደማ መገደላቸውን ተናግረዋል።
በምዕራብ ኦሮሚያ አከባቢዎች የጸጥታ መደፍረስ ካጋጠመ ሰንብቷል።

የክልሉ መንግሥት በአከባቢው ለሚደርሱ ጥቃቶች የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ተጠያቂ ያደርጋል። በቅርቡ የኦዲፒ መአከላዊ ኮሚቴ አባል እና የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በሰጡት መግለጫ ኦነግ የመንግሥት ባለስልጣናትን ይገድላል፣ የአስተዳደር ስርዓቱን ያፈራርሳል፣ ዘረፋ እና ሚሊሻዎችን ጦር ያስፈታል ሲሉ ኦነግን ከሰዋል።

በሌላ በኩል የኦነግ ሊቀመንበር አቶ #ዳውድ_ኢብሳ ድርጅታቸው ከመንግሥት ጋር ከስምምነት ላይ የደረሰባቸው ጉዳዮች በመንግሥት እየተጣሱ ነው በማለት ቅሬታቸውን ይናገራሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
በቴፒ በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች ተገደሉ‼️

በቴፒ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች #መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በሌላ በኩል አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ሲቪሎች መቁሰላቸውን የከተማው ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር አመልክቷል፡፡

የግጭቱ መንስዔ ከሥልጣንና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር የተያያዘ የማንነት ጥያቄ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ በፊት የፀጥታ ችግር በፈጠሩ ግለሰቦች ላይ ዕርምጃ ያለመውሰድ እና የህግ የበላይነትን ያለማስከበር ግጭቱ ዳግም እንዲቀሰቀስ አድርጓል ነው የተባለው፡፡ በከተማው አሁንም ውጥረት እንዳለና ቱኩስ እንደሚሰማ የከተማው ነዋሪዎች ይናግራሉ፡፡

ምንጭ፦ VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

ዛሬ ማለዳ በሊቢያ የስደተኞች እስር ቤት ላይ በተፈጸመ የአየር ድብደባ በትንሹ 44 ሰዎች #መገደላቸውን የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። በትሪፖሊ ከተማ ታጁራ በተባለ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞች እስር ቤት ላይ ባነጣጠረው የአየር ድብደባ 130 በላይ ስደተኞች መቁሰላቸውን በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው የሊቢያ መንግሥት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በትንሹ 6,000 #ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን፣ ሶማሌያውያን፣ ሱዳናውያን እና የሌሎች የአፍሪካ አገራት ዜጎች በሊቢያ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር በሚገኙት እስር ቤቶች ታጉረው ይገኛሉ። አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ የተያዙት የአውሮፓ ኅብረት በገንዘብ በሚደግፋቸው እና ባሰለጠናቸው የባሕር በር ጠባቂዎች ነው።

Via #DW
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ኮንጎ ውስጥ የኢቢላ ወረርሽኝን በማጥፋ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሁለት የማኅበረብ ጤና ሠራተኞች፣ ምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ክፍለ-ሀገር ኬቬዮ ውስጥ #መገደላቸውን፣ የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ ሰኞ አስታወቀ። ሠራተኞቹ ለወራት ያህል ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ ይደርስባቸው እንደነበርም፣ የሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድሬዳዋ ከተማ የሰው ህይወት ማለፉ ተሰምቷል!

በድሬዳዋው ግጭት ሰዎች #መገደላቸውን እንዳረጋገጡ የዐይን እማኞች ተናግረዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ግጭቱ የብሔር መልክ አለው። ግጭቱን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት ቢኖርም ለጥቃት የመደራጀት ጉትጎታ በመታየቱ ሥጋት አይሏል።

Via Eshet Bekle/DW/

-ከጋዜጠኛ እሸት በቀለ በተጨማሪ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የሆኑ የድሬዳዋ ነዋሪዎች በተፈጠረው የፀጥታ ችግር የሰው ህይወት እንዳለፈ አረጋግጠውልናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በመታወቂያ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ እንደተወሰነላቸው ጠበቃቸው ተናግሩ። በ2013 በተካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት በጸጥታ ኃይሎች ከቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ታስረው ቆይተዋል።…
አብዲ ኢሌ ከእስር ተፈቱ።

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ።

ከ6 ዓመት በፊት ነሐሴ 21/2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለው አስካሁን በእስር ላይ የቆዩት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ከእስር የተለቀቁት ዐቃቤ ሕግ ክሱን በማንሳቱ መሆኑን ጠበቃቸው ገልጸዋል።

ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው እስክንድር ገዛኸኝ ፤ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክሳቸው ተነስቶ የተለቀቁት ዛሬ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም. መሆኑን አመልክተዋል።

ከአቶ አብዲ በተጨማሪም በተመሳሳይ በእሳቸው የክስ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታይ የነበሩ የሌሎችም ተከሳሾች ክስ ተቋርጦ መለቀቃቸውን ጠበቃው ተናግረዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው ከዓመታት በፊት ጀምሮ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ሲመሩ የነበሩት አቶ አብዲ፣ በክልሉ ውስጥ ከተፈጸሙ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ግድያዎች እና የመንግሥት ሀብት ብክነት ጋር በተያያዘ ክስ ይቀርብባቸዋል።

በቀድሞው ርዕሰ መስተዳደር ላይ ከቀረቡባቸው ክሶች መካከልም በ2010 ሰኔ እና ሐምሌ ወራት ውስጥ “በሶማሌ ክልል የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ በማሰብ ‘ሄጎ’ በሚል ስያሜ የሚታወቅ ወጣቶች ቡድን አደራጅተዋል” የሚል ይገኝበታል።

በወቅቱ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው፣ ንብረት እና አብያተ ክርስቲያናት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።

ዐቃቤ ሕግም ባቀረበው የክስ ዝርዝር በተከሰተው ግጭት ምክንያት ፦
* 59 ሰዎች #መገደላቸውን
* ከ250 በላይ መቁሰላቸውን
* በመንግሥት፣ በግል እና በሃይማኖት ተቋማት ንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ገልጾ ነበር።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

ፎቶ፦ ፋይል

@tikvahethiopia