TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሀጫሉ_ሁንዴሳ ከፋና ጋዜጠኛ ጋር በነበረው ቆይታ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተውለት መልሷል።

እኔም ዝግጅቱን ከሰማው በኋላ የአቅሜን ከዚህ በታች በፅሁፍ አስቀምጬዋለሁ።
.

ጥቂት ስለ ጂራ...?

ጂራ ማለት አለን ማለት ነው። የህዝቡን ስነ ልቦና ስታይው አለን የሚያስብል ነው።... ጂራ ኤርትራም ገብቷል። ህዝብ ተለያይቶ አይለያይም። ኤርትራዊያንም ጂራ ገብቷቸዋል ማለት ነው።
.
.
ስለ ስሙ...??

ሀጫሉ ማለት "ይብለጥ" ማለት ነው። አባቴ በልጅነቴ ፈጣን እና ንቁ ስለነበርኩ ያወጣልኝ ስም ነው። እኔ ከማንም እበልጣለሁ ብዬ አላስብም።"
.
.
ስለ ዶክተር አብይ...??

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የሀገራችን ህዝቦች ዴሞክራሲ ምን እንደሚመስል ያዩ ይመስለኛል። ባልተለመደ መልኩ የሰው ልጅ የተሰማውን በአደባባይ እንደፈለገ እንዲናገር ...ከሀገራችን ህዝብ አምዕሮ በላይ የሆኑ ነገሮች ታይተዋል።

#ግን ህዝባችን ለመላመድ ጊዜ የሚያስፈልገው ይመስለኛል። ሲረገጥ፣ ሲጨቆን፣ ሲበደል የነበረ ህዝብ በአንድ ጊዜ እንደዚህ ፈሪሀ እግዚያቤር ያለው መሪ መጥቶ #እንደፈለክ ሁን ሲለው ያን እራሱ እንዴት አድርጎ መሆን እምደሚችል ላያቅበት ይችላል።

በአጠቃላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ከመንግስትም ከህዝብም እንጂ በሂደት የሚስተካከል ይመስለኛል።
.
.
.
ስለ ሀምሌ 7 የሚሊኒየም አዳራሽ ዝግጅት...?

እኔ እንደዛን ዕለት ቦታና ወቅቱን መርጬ ያስተላለፍኩት መልዕክት ያለም አይመስለኝም። ጠቅላይ ሚንስቱር ግና እንደተመረጡ ...እያንዳንዱን በየፕሮፌሽኑ ልምድ ሲሰጡ ነበር አርቲስቱንም እንደዛው የህዝባችሁን ጩኸት አሰሙ ያመናችሁበትን ስሩ ብለው ነው የመከሩት። የሳቸው ምክር More ጉልበት ሆኖኛል። እኔ የዛን ቀን ምንም ሀጢያት አልሰራሁም። እኔ ኢትዮጵያ የማውቃት #አዲስ_አበባ ብቻ አይደለችም። ምናልባት ድግስ ሊኖር ይችላል አዲስ አበባ ላይ ...መተማ ላይ ኢትዮጵያዊ ከሞተ ኢትዮጵያዊ እየሞተ ነው ብሎ address ማድረግ ..ሀረር ላይ ኢትዮጵያዊ ከሞተ ኢትዮጵያዊ እየተገደለ ነው ስለዚህ መንግስት አንድ ነገር ማድረግ አለበህ ብሎ በጥበብ መልክ ለማስተላለፍ እኔ ቦታው ነው ቦታው አይደለም ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። እንግዳን መናቅ አይመስለኝም።
.
.
ሀጫሉ ዘረኛ ነው ይሉሀል??

#ዘረኛ ነህ ካልሽኝ ዘረኛ #አደለሁም። እኔ ያሳደገኝ እና የወጣሁት ከኦሮሞ ማህበረሰብ ነው። በኦሮሞ ማህበረሰብ #ዘረኝነት ይኮነናል። በገዳ ስርዓት ውስጥ ዘረኝነት ይኮነናል። ዘረኛ መሆንም #አልችልም። ዘረኛ ብሆን ኢንተቪው የምናደርገው በአስተርጓሚ ነው።

አፌን የፈታሁት በኦሮሚኛ ነው። ዘረኛ ስላልሆንኩ ነው በአማርኛ የማወራው። ለሌላውም ቋንቋ አድናቆት እና ክብር አለኝ።

በምን አይነት መልኩ ተረድተውኝ እንደዚህ እንዳዚህ እንዳሉኝ ሊገባኝ አይችልም። ምናልባት የሚመስለኝ እሱ የሚዘፍነው ኦሮሞ...ኦሮሞ...ኦሮሚያ እያለ ነው የሚል ከሆነ ኦሮሞና ኦሮሚያ ከኢትዮጵያ ውጭ አይደሉም። ኦሮሞ ሆኜ ስለ ሱዳን እና ስለ ኬንያ ብዘፍን ነው የሚያስወቅሰኝ። ለምሳሌ አንድ ዘፈን አለ የሻምበል በላይነህ ዘፈን...
ወልቃይት ጠገዴ፤ ሰሜን አርማጭሆ ዳንሻና ሁመራ
ሰውም ጎንደሬ ነው መሬቱም ያማራ ..ብሎ የሚዘፍነው ዘፈን አለ ይሄ ዘረኝነት ሊያስብለው አይችልም።
.
.
.
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን እንዴት ታየዋለህ...??

ኢትዮጵያ painting ናት ለኔ። ኢትዮጵያን ስንስላት 80 ቀለሞችን ቀላቅለን ነው የምንስላት። እነዛ 80 ቀለሞች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ናቸው። ለኔ ኢትዮጵያዊነት የ80 ብሄር ብሄረሰቦች ቅልቅል ውጤት ናት። በኢትዮጵያዊነቴ ማንም ሰው አንተ ኢትዮጵያን አትወድም አንተ ኢትዮጵያን ትወዳለህ ሊለኝ አይችልም። #ምክንያቱም ቅድመ አያቴ ቦንሲቱቃበታ ከዚህ #መቀሌን ነፃ ለማውጣት በእግሯ ስትጓዝ ኦሮሞ እዛ ስላለ አይደለም። እኔ የአያቴ አስክሬን ሲሸ ኝ አውቃለሁ ሲፎከርላት የነበረው በፈረስ .."ቦንሲቱ ጋፋ መቀሌ እየተባለ ቦንሲቱ ያኔ በመቀሌ ጊዜ..." እየተባለ ሲፎከርላት ነው አስክሬና ሲሸኝ የነበረው።

በህይወት የሌሉ ቅድመአያቶቼ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር አጥንታቸውን ከስክሰዋል።

ማንም ሰው ሀጫሉ #በኢትዮጵያዊነቱ ላይ እንደዚህ ያለ አቋም አለው የለውም የሚል መብት የለውም ምክንያቱም እኔ ስለማውቀው። ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው። ምክንያቱም 80 ቀለም ስላለው።
.
.
ስጋት አለኝ ስጋቴ ምንድነው ...ድሮ መንግስት ሀላፊነቱን ይረሳና ጡንቻውን የሚያሳይበት ነበር። ያን ነገር ምስኪን ህዝብ ለመቀየር ይሄ ነው የማይባል መስዋትነት ከፍሏል። ከከፈለ በኋላ አሁን ይመስለ ኛል በተወሰነ መልኩ ባልተጠበቀ መንገድ ህዝባዊነት የሚታይበት ነገር አለ ስጋቴ ምንድ ነው ይሄን መንግስት መያዝ እንዳያቅተው ነው ስጋቴ። ጥንቃቄ እንደሚፈልግ እና በጥንቃቄ ማየት እንዳለበት።
.
.
በቀጣይ ስለ ሚሰራው ስራዎች...??

አሁን ከመንግስት ትወርጅና ደግሞ misunderstanding ተፈጥሮ ልዩነት ማስፋት ሳይሆን በማጥበብ ሀገርን ማኖር እንደሚቻል #በመከባበር አንዱ ያንዱን ሀሳብ ለማድመጥ በመዘጋጀት በመተማመን፣ በመነጋገር አብሮ ለመኖር እንደሚቻል የሚያሳዩ ስራዎችን ለመስራት ነው ወደፊት የማስበው።
.
.
ጎንደር ተውልከድ ወይም መቀሌ ተወልደክ ቢሆን ኖሮ የአሁኑን አይነት ሰው ትሆን ነበር??

#ጎንደሬነቴ ክብሬ ነው! ማለቴ አይቀርም..
.
.
.
ከሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ምን ተማርክ?
(ሀጫሉ የኢትዮጵያ ባለውለታው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ዘመንድ እንደሆነ ይታወቃል)
.
.
ኢትዮጵያዊነታቸውን እና ኦሮሞነታቸውን እንዴት እንዳካሄዱት ነው የተማርኩት።
.
.
.
ለኢትዮጵያ ህዝብ ምን ሙዚቃ ትጋብዛቸዋለህ??

.ጂራ...ጂራ...ጂራ...(የራሱን ሙዚቃ)
.
.
.
የነዋይ ደበበ - የክብሬ መመኪያ (በራሱ ድምፅም ትንሽ አንጎራጉሯታል)

የክብሬ መመኪያ ደስታና ህይወቴ
ሌላ ምን ሀብት አለኝ ሀገሬ ናት ሀብቴ
እሰይ እሰይ ...ዛሬም እሰይ ነገም እሰይ
#ኢትዮጵያ እምዬ...

ሀጫሉ ሁንዴሳ ከፋና ብሮድክስቲንግ FM 98.1 ጋር በነበረው ቆይታ!

ማሳሰቢያ ከይቅርታ ጋር፦ ምናልባት የቃላት ስህተት አፃፃፍ ላይ ካለ እርማት ስጡበት።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከነቀምት⬇️

"ፀግሽ ዛሬ የተፈናቀሉትን ለመርዳት 07 ያለው መጠለያ ልብስ፣ ጫማ፣ ምግብ፣ ዳይፐር፣ ሞዴስ፣ ወተት ይዘን ሄደን ነበር በጣም #ያሳዝናሉ። ብዙ ሰዎች ከሰፈር ምግብና ልብስ እዘው እየሄዱ ነው ያለው። ርብርቡ ደስ ይላል #ግን ያለው ነገር በቂ አይደለም። ቦንሳ ከነቀምት"

@tsegabwolde @tikvahethiopia