TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሶሳ🔝የሰላም እናቶች #አሶሳ ከተማ ይገኛሉ። የሰላም እናቶች ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ከአገር ሽማግሌዎች ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ከአሶሳ ከተማ ከተውጣጡ የህዝብ ወኪሎች ጋር በሰላም ዙሪያ ተወያይተዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመከላከያ ሰራዊት ቀን🔝

7ኛው የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል #አሶሳ ከተማ እና በአማራ ክልል #ባህርዳር ከተማ በፓናል ውይይት በመከበር ላይ ነው።

“ህገ መንግስታዊ ስረአታችንና ህዝባዊ ባህሪያችንን ጠብቀን የተጀመረውን ለውጥ እናስቀጥላለን'' በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።

የምእራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ አስተዳደር ብርጋዴል ጄነራል እንዳልካቸው ወ/ኪዳን በውይይቱ ላይ እንዳሉት በህገ መንግስታዊ መርሆዎች የተቋቋመው የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚሰጠውን ተልእኮዎችን በላቀ ድል እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት ታሪካዊ አመሰራረት ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። በፓናል ውይይቱ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት የህዝብ ወኪሎ፣ የምእራብ ዕዝ እና የ22ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣ የሰራዊት አባላት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ሪፖርተራችን ያለለት ወንድዬ ከአሶሳ ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና በባሕር ዳር ከተማ ሙሉዓለም የባሕል ማዕከል 7ኛው የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን እየተከበረ ነው፡፡

በበዓሉ ላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሉ መንግሥት ሰላምና ደኅንነት አባላትና አመራሮች፣ የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ከፍሎች እየታደሙ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክረተሪያት ኃላፊ አቶ #ንጉሡ_ጥላሁን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናትም በበዓሉ አከባበር እየተሳተፉ መሆኑን አብማድ ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሶሳ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነው በዛሬው እለት በአሶሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሶሳ

የቤንሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ብሄራዊ ክልሎች መንግስታት የልማትና የጸጥታ ትብብር የጋራ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡ የምክክር መድረኩን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት አቶ አሻድል ሀሰንና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እየመሩት ሲሆን የካቢኔ አባላትም እየተሳተፉ ናቸው፡፡

በምክክር መድረኩ በ2011ዓ.ም በልማትና በጸጥታ ዘርፎች በጋራ የሰሯቸው የጸጥታ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል፡፡ የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችና ያጋጠሙት ተግዳሮቶች ይገመገማል፡፡ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ተግዳሮቶችን ለማስወገድ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የ2012 እቅድም ቀርቦ ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሶሳ የሰላም አየር እየነፈሰ ነው!

አሁን በስራ ምክንያት ያለሁት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ዋና ከተማ #አሶሳ ነው። ሞቃት የአየር ንብረት የሚስተዋልባት፣ አረንጓዴ፣ እና ቀይ ለም አፈር ያለው መሬት ያላት። አሶሳ ከመጣሁ እነሆ ሶስተኛ ቀኔ አለፈ።

አንዳንድ ጓደኞቼ እንዲሁም ቤተሰቦቼ ጋር ተደዋውዬ በስልክ ሳወራ ከኔ ሁኔታ ይልቅ ስላለሁበት ቦታ #አሶሳ አብዝተው ይጠይቃሉ። ገና ለመምጣት በነበርኩበት ግዜ እራሱ ምነው ወደዛ መሄድህ... ? በሰላም ነው? እያሉ በጥያቄ ያጨናነቁኝ ቁጥራቸው ብዙ ነው። መጠየቃቸውን እንደ መጥፎ ነገር ባልቆጥረውም አንድ ነገር ግን በአእምሮዬ ብቅ እንዲል ሆኗል። እኔ ባለሁበት ሰዐት አሶሳ እጅግ #የተረጋጋች፣ ሰላማዊ እና የዕለተ ቀን እንቅስቃሴዋን የምትከውን ከተማ ነች።

ምናልባት የሰዎች ጥያቄ የመጣው ከጊዜያት በፊት በክልሉ በመተከል፣ ካማሺ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ በነበረው አለመረጋጋት እና ግጭት ይመስለኛል። እስካሁን ድረስ ግን ብዙ ሰዎች በክልሉ እንዲሁም በሌሎች ክልሎች ሰላማዊ ሁኔታ ያለ #አይመስላቸውም

ሰላም እና መረጋጋትም የማይመቻቸው እና እንቅልፍ የሚነሳቸው አካላት በየማህበራዊ ሚዲያው በሚፈጥሩት ዉዥንብር ምክንያት እና በማይረቡ ተናፋሽ ወሬዎች ማለቴ ነው እና አሁን በአሶሳ ፍፁም #የሰላም አየር ነው እየነፈሰ ያለው ያለው። እንዲሁ በሌሎች ክልሎችም እንዳጣራሁት ከሆነ በብዛት የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው። የኢትዮጵያ ሰላም እየተመለሰ ነው። ይመለሳልም። ኢትዮጵያ በሰላም፣ እስከዘላለም ትኑር።

Y ነኝ ቤተሰባችሁ ከአሶሳ!

ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው ..

- ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣
- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ
- የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ
- ወልዲያ
- ሪፍትቫሊ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት እያስመረቁ ነው።

#ባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 363 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ተማሪዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐ-ግብሮች፤ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሶስተኛ ዲግሪ እና የስፔሻሊቲ ህክምና የሰለጠኑ ናቸው።

#አሶሳ_ዩኒቨርሲቲ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 237 ተማሪዎችን ነው በማስመረቅ ላይ የሚገኘው።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለ8ተኛ ጊዜ ሲሆን የዛሬዎቹ ተመራቂዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።

#የኢትዮጵያ_ሲቪል_ሰርቪስ_ዩኒቨርሲቲ

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲም በተለያየ የትምህርት መስኮች በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ የተማሩ ናቸው።

ከእለቱ ተመራቂዎች ውስጥ 153 የሚሆኑት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በውጭ ግንኙነት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሰለጠኑ እጩ ዲፕሎማቶች ናቸው።

#ወልዲያ_ዩኒቨርሲቲ

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,537 ተማሪዎችን አስመርቋል።

#ሪፍትቫሊ_ዩኒቨርስቲ

የሪፍትቫሊ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 16, 967 ተማሪዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም አስመርቋል።

መረጃው የetv ነው።

@tikvahethiopia
#አዲስአበባ #አሶሳ

➡️ " በስራ ዘመን ቆይታዬ ይህን ያህል ክብደት የሚመዝን ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው " - ዶ/ር ረታ ትዕዛዙ (ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል

👉 " የ3 ቀን ጨቅላ ህፃን አንገቷ ላይ በአፈጣጠር ትልቅ እብጠት ይዛ የተወለደች ቢሆንም የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎላታል አሁን በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ ናት " -
አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል

በአዲስ አበባ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቤቴልሄም አመኑ የተባለች እናት 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወንድ ልጅ በተደረገላት የቀዶ ህክምና በሰላም ተገላገለች።

የሆስፒታሉ የማህፀን ስፔሻሊስት እና የዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ረታ ትዕዛዙ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል " በስራ ዘመን ቆይታዬ ይህን ያህል ክብደት የሚመዝን ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው " ብለዋል።

ልጆች ከ5 ኪሎ በላይ ሆነው ሲወለዱ የሚደረግላቸው ህክምና መኖሩን የገለጹት ዶ/ር " ለልጁ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ መረጃ በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጓል።

የ3 ቀን ጨቅላ ህፃን አንገቷ ላይ በአፈጣጠር ትልቅ እብጠት (Bilateral huge cystic hygroma) ይዛ የተወለደች ስትሆን  በእብጠቱ ምክንያት ጡት መጥባትም ሆነ እንደ ልቧዋ መተንፈስ አትችልም ነበር።

በ13/4/17 ዓ/ም በሆስፒታሉ የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎላት አሁን በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል።

አሁን እንደልቧ መተንፈስ ጡት መጥባትም ጀምራለች ተብኳል።

በህክምናው ላይ የተሳተፉ ባለሞያዎች ፦
🙏 Surgeons ፦ ዶ/ር ሮቤራ ተሾመ እና ዶ/ር መብራቴ ወ/መድህን
🙏 Anaesthesiologist ፦ ዶ/ር ሲሳይ እብስቱ
🙏 Anesthesia team: ደመቀ ወ/ኪዳን፣ ተሰፋዬ አሰፋ እና ሰለሞን አዳሙ
🙏 Scrub Nurse ፦ሲ/ር ሳይሽልዋል ወርቁ (ቹቹ)
🙏 Circulator Nrs ፦ አልሃጅ ሀሰን እንደሆኑ ሆስፒታሉ አሳውቋል።


@tikvahethiopia