TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬇️

ዛሬ በአዲስ አበባ መድኃኔዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት አካባቢ ከምልክትና #ባንዲራ ቀለም ጋር በተያያዘ መጠነኛ ግጭት ተፈጥሯል፡፡

ቅዳሜ መስከረም 5/2011 ዓ.ም ወደ ሀገር የሚገቡትን የኦነግ አመራሮች ለመቀበል የተዘጋጁ ወጣቶች የአስፓልት ጠርዝን የሚደግፉት ድርጅት መለያ ቀለም በሚቀቡበት ወቅት ነበር ግጭቱ የተቀሰቀሰው፡፡

ድንጋይ መወራወሩ ያለማቋረጥ በመቀጠሉ ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን #አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል፡፡

የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ህዝብ ግንኙነት ታዬ ደንደአ ዛሬ በፌስ ቡክ ገጻቸው “ስለ ምልክት ሳይሆን ስለ ሀገር ከልብ እናስብ፤ ሀገር ካለች ባንዲራ መስቀል እና ሀውልት መገንባት አይከብድም፤ ሀገር ከሌለ ግን ባንዲራ ብቻውን ትርጉም የለውም” ብለዋል፡፡

የግንቦት 7 ሊቀ መንበር ብርሀኑ ነጋ (ዶ/ር) ባለፈው እሁድ አዲስ አበባ ሲገቡ ተመሳሳይ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡

©ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia