TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቤንሻንጉል ጉሙዝ
(ትኩረት‼️)

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፓዊ ወረዳ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሰው ሕይወት እየጠፋ፣ አካል እየጎደለና ንብረት እየተዘረፈ መሆኑን ነዋሪዎች ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡

ከቀናት በፊት በዳንጉር ወረዳ በጫኝና አውራጆች መካከል በተነሳ ግጭት የተጀመረው አለመረጋጋት ወደተለያዩ አካባቢዎች #መስፋፋቱን ነው ነዋሪዎቹ ያስታወቁት፡፡

ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አስተያዬታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ‹‹እረኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ከብቶቻችንም እየተነዱ እየተወሰዱ ነው፡፡ ትናንት ገበያ መውጣት አልቻልንም፤ ዛሬም #በዓሉን ለማክበር ተቸግረን ፍርሃት ውስጥ ነን›› ብለዋል፡፡

ማምቡክ መንደር 49 አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ደግሞ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ዛሬ ገበያ ነበር፤ ገና ከመቆሙ በጠዋቱ ተበትኗል፡፡ በጫካው ውስጥ ተኩስና ቀስት ማስወንጨፍ አለ፡፡ ከዳንጉር አካባቢ ነው የግጭቱ መሠረት ያለው፤ መንግሥት በፍጥነት ሊደርስልን ይገባል፡፡ ሰዎች በየጫካው እየሞቱ ነው›› ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለትም የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቦታው መድረሱንም ገልጸዋል፡፡

የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት በበኩሉ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር አንጻራዊ #መረጋጋት ላይ መሆኑን ለአብመድ አስታውቋል፡፡ ሚያዝያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ አይሲካ ቀበሌ በአሽከርካሪ እና ጫኝና አውራጅ ሥራ በተሠማሩ ወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩ ተነግሮ ነበር፡፡

አሁን ላይ ችግሩን የፈጠሩ ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን እና ተጨማሪ የሰዉ ሕይወት #እንዳይጠፋ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አድጎ አምሳያ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ ኃይል በጋራ በመሆን ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia