TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ: አደጋው የደረሰበት ቦታ👆

#ቢቢሲ #ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሆስኒ ሙባረክ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ!

የቀድሞ የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ስርዓተ ቀብር በወታደራዊ ስነስርአት በክብር ተፈፀመ፡፡

የቀብር ስነ-ስርዓቱ በካይሮ ከተማ በፊልድ ማርሻል ታንታዊ መስጂድ ሲፈፀም በስፍራው የወቅቱ ግብጽ ፕሬዝዳንት አብዲል ፈታ አልሲሲ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሟች ቤተሰቦች እና ደጋፊዎቻቸው ተገኝተዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱ አስከሬን የቤተሰባቸው የመቃብር ቦታ ላይ እንደሚያርፍ የተገለፀ ሲሆን የግብጽ መንግስትም የሶስት ቀን ብሔራዊ የሀዘን ቀን አውጇል፡፡

[#ቢቢሲ #ሮይተርስ #ኢቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

በአለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ [#COVID19] ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን የአለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ÷ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከቻይና ውጭ ስምንት እጥፍ ያህል አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ሪፖርት መደረጉን  ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ኮሪያ፣ጣሊያን፣ኢራንና ጃፓን የተከሰተው ወረርሽኝ ከፍተኛ  መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ቴድሮስ፤ በአሁኑ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አደጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም  አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

#ሮይተርስ #ቢቢሲ #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሩዋንዳ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ተንቀሳቃሽ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮችን በዋና ከተማዋ መጠቀም ጀምራለች።

ሩዋንዳ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ካልተመዘገበባቸው የሰብ ሳህራን አፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነች።

ይሁን እንጂ ሀገሪቱ ወረርሺኙን ቀድሞ ለመከላከል በዋና ከተማ ኪጋሊ ተንቀሳቃሽ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮችን ዜጎቿ እንዲጠቀሙ ተግባራዊ አድርጋለች።

በሩዳንዳ ተንቀሳቃሽ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮቹ የተተከሉት ባንኮች ፣ በገበያ ማዕከላት ፣ በባስ ስቴሽኖች እና በሬስቶራንቶች ውስጥ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።

#ሮይተርስ #ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ትላንት ጎረቤታችን ሱዳን ውስጥ አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፏል ፤ ይህ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ተይዞ እንደነበረ ሀገሪቱ አስታውቃለች፡፡

ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ በዚህ ወር የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን ጎብኝቶ እንደነበረ ነበረና ሀሙስ እለት ህይወቱ ማለፉ ነው የታወቀው፡፡

በ50ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የነበረው ግለሰብ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ መሞቱን የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

#ሮይተርስ #ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል ተፈናቃዮች በተጠለሉበት ካምፕ ላይ ተፈፀመ በተባለ የአየር ጥቃት 56 ሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩት መቁሰላቸውን ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የእርዳታ ሰራተኞች እንደነገሩት ሮይተርስ ዘግቧል።

የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው በክልሉ ሰሜናዊ ምዕራብ በምትገኘውና የኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ባለች ደደቢት ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት አርብ ዕለት መሆኑንም የእርዳታ ሰራተኞቹ ገልጸዋል።

ቅዳሜ የእርዳታ ሰራተኞች ለሮይተርስ እንደተናገሩት የሟቾች ቁጥር በአካባቢው ባለስልጣናት መረጋገጡን ነው።

የረድዔት ድርጅት ሰራተኞች ህፃናትን ጨምሮ ሆስፒታል ውስጥ ያነሷቸውን የቆሰሉ ሰዎችን ፎቶግራፍ ለሮይተርስ መላካቸው ተገልጿል።

የ ' ሽረ ስሁል አጠቃላይ ሆስፒታል ' ከጎበኙት የረድኤት ሰራተኞች መካከል አንደኛው እንደገለጹት መጠለያ ካምፑ በርካታ በእድሜ አዛውንትናና ህፃናት ያሉበት ነው።

ትምህርት ቤቱ እንዴት እና ለምን ጥቃት እንደደረሰበት ግልፅ አይደለም።

ሮይተርስ ጥቃቱ በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠም ብሏል።

ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ስለጉዳዩ ለመጠየቅ ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ፅፏል።

ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ መንግስት ብዙ ጊዜ ሲቪሎችን እንደማያጠቃ መግለፁን ሮይተርስ አስታውሷል።

UNOCHA ባወጣው መግለጫ ከታህሳስ 10-ታህሳስ 15 ድረስ በትግራይ ላይ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት መደረጉን አስፍሯል።

ታህሳስ 21/2014 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት ከጥቅምት ወር ወዲህ ከተከሰቱት በጣም አስከፊ፣በርካታ ሞቶች ሪፖርት የተደረጉበትና በተከተታይ የተፈጸመ ነው ብሏል።

በርካታዎቹ ጥቃቶች ሪፖርት የተደረጉት በአላማጣ፣ ኮረም፣ ማይጨው፣ መኮኒና ሚላዛት መሆኑን ጠቅሷል።

#ሮይተርስ

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ #1 ፦

➡️ #ሴኔጋል ፦ በምዕራብ ሴኔጋል ፤ ቲቫዋን በምትሰኝ ከተማ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ ቃጠሎ 11 አዲስ የተወለዱ ህጻናት መሞታቸውን ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ተናግረዋል።

➡️ #አፍጋኒስታን ፦ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል እና ሰሜናዊ ከተማ ማዛር ኢ ሻሪፍ ከተከታታይ በደረሱ ፍንዳታዎች ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። ዳኢሽ ለጥቃቱ ኃላፊነት መውሰዱን ሮይተርስ ዘግቧል።

➡️ #ሩስያ ፦ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ወታደሮቻቸውን ወደ ሀገሪቱ ከላኩ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩክሬን ውስጥ በወታደራዊ ዘመቻው ከቆሰሉ ወታደሮች ጋር ተገናኝተዋል። በሌላ የሩስያ ጉዳይ ፤ ሀገሪቱ ያለባትን የውጭ ሀገራት እዳ በራሷ መገበያያ ገንዘብ “ሩብል” ለመክፈል ወስናለች ፤ እዚ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ከቀናት በፊት በሩሲያ በአሜሪካ ባንኮች በኩል የምትፈጽመውን የውጭ ዕዳ ክፍያ ፍቃድ መሰረዙን ተከትሎ ነው።

➡️ #ዩክሬን ፦ ወደ ሰቨሮዶንስክ ከተማ የሚወስደውን አውራ ጎዳና ለመቆጣጠር በሩስያ እና ዩክሬን ኃያሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተደረገ ነው። ሩሲያ ይህን ከተማ ለመቆጣጠር ተቃርቢያለሁ ብትልም አንድ ከፍተኛ የዩክሬን ባለሥልጣን ነገሩን አስተባብለዋል። ይህ ጎዳና ዩክሬን የምትቆጣጠራቸውን ከተሞች ሩሲያ ከያዘቻቸው ከተሞች ጋር የሚያገናኝ ከፍ ያለ ወታደራዊ ዋጋ ያለው ነው።

➡️ #ጋምቢያ ፦ የጋምቢያ መንግስት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ከ20 አመታት በላይ በዘለቀው የስልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል በተባሉ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ወንጀሎች ላይ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል።

#አልጀዚራ #ቲአርቲወርልድ #ስፑትኪን #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
የIMF ሰዎች እዚህ ኢትዮጵያ ናቸው።

ብሉምበርግ የዜና ወኪል ፤ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ለኢትዮጵያ ሊሰጥ በሚችለው ድጋፍ አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ የድርጅቱ ባለሥልጣናት አዲስ አበባ ይገኛሉ ብሏል።

በእርስ በርስ ጦርነቱ ሳቢያ ኢትዮጵያ ከIMF ጨምሮ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር የነበራት ግንኙነት ተቀዛቅዞ መቆየቱ ይታወሳል።

እንደ ብሉምበርግ ዘገባ የተቋሙ የባለሙያዎች ቡድን ኢትዮጵያ ከIMF ሊደረግላት ስለሚችለው ድጋፍ አስፈላጊውን “ቴክኒካዊ ሥራ ለማከናወን” ነው አዲስ አበባ የሚገኘው።

ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ በተመለከተ ውይይት እና አስፈላጊውን ሁኔታ እንዲያመቻቹ የተላኩት የIMF ባለሥልጣናት ለ10 ቀናት ያህል ይቆያሉ።

ቃላቸውን ለሮይተር የዜና ወኪል የሰጡ የIMF ቃል አቀባይ በበኩላቸው ፤ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው ምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግላት ተቋሙን እንደጠየቀች ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ፤ " ሊሰጥ የሚችለው ድጋፍ አገሪቱ ለምታካሂደው አገር በቀል የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እና ምጣኔ ሀብቷን በማረጋጋት ለሰብአዊ ድጋፍ፣ ለሥራ ፈጠራ እና ለድህነት ቅነሳ የሚውል ይሆናል " ብለዋል።

የIMF ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ የሚያደርጉት ቴክኒካዊ ውይይት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና በተቋሙ መካከል ሰብአዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮችን ለማሻሻል የተደረገ ንግግር ተከታይ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም መካከል ሲካሄድ የነበረው የድጋፍ፣ የብድር ስረዛ እና ሽግሽግ ንግግር በከፊል በትግራይ ሲካሄድ ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶ ነበር።

ብሉምበርግ እንደዘገበው ኢትዮጵያ ጦርነቱ ያስከተለውን ውድመት መልሶ ለመገንባትና የገጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመሸፈን አስፈላጊ ለሆኑ የገቢ ምርቶች ክፍያ ለመፈጸም ድጋፍ ያስፈልጋታል።

ጦርነቱ ካስከተለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ባሻገር በአፍሪካ ካሉ የመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች መዳረሻ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን እና ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የተነሳ ከዓለም ባንክ (World Bank) አንዲሁም ከIMF የምታገኘውን ድጋፍ ገትቶት መቆየቱን አስታውሷል።

በጦርነቱ እና በዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ምክንያት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር የገጠማት ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ከመመዝገቡ በላይ እጥረትም ተከስቷል።

#ቢቢሲ #ብሉምበርግ #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ድርድር መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ መሮ ዲሪባ ፥ የታጠቂ ቡድኑን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሚያደራድር ሦስተኛ አካል መኖሩን ለቢቢሲ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል። ጃል መሮ አደራዳሪዎቹ እነማን እንደሆኑ በስም ከጥቀስ ተቆጥበዋል። መሮ ዲሪባ ታጣቂ ቡድኑን ወክለው ከመንግሥት ጋር የሚደራደሩ የልዑክ ቡድን አባላት ወደ #ታንዛኒያ ጉዞ እያደረጉ ስለመሆኑ አሳውቀዋል።…
#Update

" ወደ ፖለቲካዊ ስምምነት እንደሚያመራ ተስፋ እናደርጋለን " - ኑር ሙሀሙድ

የኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጣቂ ቡድን መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በታንዛኒያ ከፊል ራስ ገዝ በሆነችው #ዛንዚባር ንግግር መጀመራቸውን ኢጋድ አሳውቋል።

የኢጋድ ቃል አቀባይ ኑር ሙሀሙድ ሼይኽ በታንዛኒያ ንግግር መጀመሩን ገልጸው ፤ " ወደ ፖለቲካዊ ስምምነት እንደሚያመራ ተስፋ እናደርጋለን " ብለዋል።

ሁለቱም ተደራዳሪ አካላት ንግግር ስለመጀመሩ ማረጋገጫ ቢሰጡም ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረጉም ፤ የታንዛኒያ ባለስልጣናትም ስለድርድሩ የተለየ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ሮይተርስ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ነገር ግን ስለ ድርድሩ በቅርበት የሚየውቁ ሁለት ሰዎችን ዋቢ በማድረግ ባሰራጨው ዘገባ የኢትዮጵያ መንግሥት ተደራዳሪ ልዑክ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሚመራ ሲሆን በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቡድን በማን እንደሚመራ ዘገባው ያለው ነገር የለም።

#ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#እስራኤል

ኔታኒያሁ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ከእስራኤል ለማስወጣት ለሚያዝ እቅድ ፍቃድ መስጠታቸው ተነገረ።

በትላንትናው ዕለት በቴል አቪቭ ጎዳናዎች ላይ በኤርትራዊያን ስደተኞች መካከል የተፈጠረውን አስከፊ ግጭት ተፈጥሮ ነበር።

ይህን ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ደም በተቃባው ግጭት ላይ የተሳተፉት ስደተኞች በሙሉ በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ አክለውም ሁሉም #አፍሪካዊያን ስደተኞች ከእስራኤል እንዲወጡ ለሚያዝ እቅድ ፍቃድ መስጠታቸውንም ገልጸዋል።

ትላንት ቅዳሜ የፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን አስተዳደርን በሚቃወሙ እና በሚደግፉ ኤርትራዊያን መካከል ግጭት ተነስቷል።

ተቃውሞውና ግጭቱ በእስራኤል ኤርትራ ኤምባሲ ፊት ለፊት ነው የተካሄደው። የእስራኤል የአደጋ አገልግሎት ተቋም 114 ሰዎች በግጭቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል።

የእስራኤል ፖሊሶች የግጭቱን ተሳታፊዎች ለመበተን የፕላስቲክ ቦምቦችን የተጠቀሙ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ በፖሊሶቹ ላይ ድንጋይ ወርውረዋል።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፖሊስ ተቃዋሚዎቹ ላይ እሳት መርጨቱን የዘገበ ሲሆን በአጸፋው 27 ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል አስታውቋል።

በተያያዘ ሮይተርስ እጃቸው እና ጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች በህጻናት መጫወቻ ሜዳዎች ሲደበቁ መመልከቱን ዘግቧል።

በእስራኤል 20,000 ኤርትራዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹም በህገወጥ መንገድ በግብጽ አድርገው የመጡ ናቸው።

#ቪኦኤ #ኤኤፍፒ #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Puntland #Somalia ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ይፋ አድርጋለች። ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው #ፑንትላንድ በሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ከዚህ ቀደም ሰጥታው የነበረውም ዕውቅና አንስታለች። የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ፑንትላንድ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና…
#Somalia

° " ስለዚህ ጉዳይ መረጃው የለኝም " - አቶ ነብዩ ተድላ

ሶማሊያ ፥ በሶማሊያ #የኢትዮጵያን_አምባሳደር የሆኑትን ሙክታር ሞሃመድ ዋሬን ወደ ሀገራቸው #እንዲመለሱ ማድረጓን ሁለት ከፍተኛ የሶማሊያ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ #ሮይተርስ ዘግቧል።

ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገችበት ምክንያት ከሶማሊላንድ ጋር የገባቸው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እንደሆነ ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈ ሶማሊያ በፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችን ዘግቻለሁ ብላለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል።

የፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ነገር ?

ፑንትላንድ ከሕገ-መንግስት ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ከቀናት በፊት ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

ከአሁን በኃላም ማንኛውም ፍላጎቷን ለማስጠበቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ የውጭ ግንኙነትም እንደምታደርግ ገልጻለች።

ሶማሌላንድም ምንም እንኳን እስካሁን ሶማሊያ ' የራሴ ግዛት ነሽ ' ብትላትም ራሷን እንደ ነጻ ሀገር መቁጠር ከጀመረች አመታት አልፈዋል። የውጭ ግኝኑነቶችንም ታደርጋለች።

የሰሞኑን የፑንትላንድ ነገር ለሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት " በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ " ሆኖበታል።

ከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ሰሞኑን ፥ " ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ተቆራጠናል ፤ እውቅናም አልሰጥም " ካለች በኃላ ከፍተኛ ባለስልጣናቷ ኢትዮጵያ / አዲስ አበባ ለውይይት መግባታቸው መነጋገሪያ ሆኗል።

እዚህ አዲስ አበባ የመጣው በገንዘብ ሚኒስትሯ ሞሃመድ ፋራህ ሞሀመድ የተመራ ልዑክ ነው።

ልዑኩ ከኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ጋር መክሯል።

በዚህም ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላትን ዘርፍ ብዙ ትብብሮች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗ ተገልጿል።

የፑንትላንድ ልዑክም ፥ ኢትዮጵያ በፑንትላንድ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን ገልጾ የፑንትላንድ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት እንዳለው አረጋግጧል።

በዚህ ወቅት የፑንትላንድ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ መምጣታቸው ግጥምጥሞች ወይስ ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር የተያያዘ ነው ?

" ጉብኝቱ የቆየ ቀጠሮ ነው " - አቶ ነብዩ ተድላ

ዛሬ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፑንትላንድ በገንዘብ ሚንስትሯ መሀመድ ፋራህ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አ/አ ጉብኝት ማድረጉን ገልጸዋል።

ይህ ጉብኝት ከሰሞነኛው የፑንትላንድ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር #የማይገናኝ እንደሆነ እና የጉብኝት ፕሮግራሙም የቆየ ቀጠሮ መሆኑን አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Rwanda #UK ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን እንደተቃረበ ቪኦኤ ዘግቧል። የዕቅዱ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስደተኞቹን #በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና…
" ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን፤ ... የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖችንም ተከራይተናል " - ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ

ዩናይትድ ኪንግደም በቁጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ መላክ ትጀምራለች።

የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ስደተኞች/ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመመለስ የተያዘውን እቅድ መጀመር የሚያስችለውን " የሩዋንዳ እቅድ " የተሰኘውን ረቂቅ ሕግ ትላንት አጽድቋል።

ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ፥ " በቀጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ባለው ጊዜ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን " ብለዋል።

ለዚህም ፤ የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖች ኪራይ መፈጸሙና ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የሚወስዱ ሰራተኞችም መሰልጠናቸው ተነግሯል።

52,000 ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዋ ሩዋንዳ ይዘዋወራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቅርብ አመታት ፦
- #ከአፍሪካ
- ከመካከለኛው ምስራቅ
- ከኢስያ ጦርነት እና ድህነት የሚሸሹ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ዩናይትድ ኪንግደም ገብተዋል።

እነኚህ ስደተኞች በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በትንንሽ ጀልባዎች ተጉዘው ነው ዩናይትድ ኪንግደም የሚገቡት። #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#ኢራቅ

የኢራቅ ፓርላማ #ግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል።

በአዲሱ ሕግ መሠረት ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት ሊታሰሩ ይችላሉ።

በአዲሱ ሕግ ፦

➡️ የግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤

➡️ ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ፤

➡️ ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ዶክተሮችን፤

➡️ " ሆን ብለው " እንደ #ሴት የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ።

የሕጉ ዓለማ ፥ " የኢራቅን ማህበረሰብ ከሞራል ዝቅጠትና ግብረ ሰዶማዊነት ከሚያደርሰው አደጋ ለመጠበቅ ነው " ተብሏል።

ረቂቁ መጀመሪያ ላይ ግብረሰዶማውያን #በሞት እንዲቀጡ የሚል የነበረው ቢሆንም በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ተቃውሞ መሻሻሉ ነው የተሰማው።

የኢራቅ ፓርላማ አባል የሆኑት አሚር አል-ማሙሪ ፥ " አዲሱ ሕግ #ኢስላማዊ እና ማህበረሰባዊ እሴቶችን የሚቃረኑ ልዩ ጉዳዮችን ለመዋጋት ትልቅ እርምጃ ነው " ብለዋል።

#አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መ/ ቤቷ በኩል ሕጉን ፤ " ለሰብአዊ መብትና ነፃነት ጠንቅ ነው " በማለት ሕጉን ተቃውማለች።

" ሕጉ የኢራቅን ኢኮኖሚ የሚያቀዛቅዝ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅምን ያዳክማል" ብላለች።

የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ሕጉን ተቃውመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጮች #ቢቢሲ እና #ሮይተርስ መሆናቸውን ይገልጸል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IRAN🇮🇷 የኢራኑ ፕሬዝዳንት እና አብረዋቸው የነበሩ ከፍተኛ ባለስልጣናት (የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ጨምሮ) እየተፈለጉ ነው። ህዝቡ መሪዎቹ ምንም ሳይሆኑ በህይወት ተርፈው ይመለሱ ዘንድ ፈጣሪውን እየለመነ ይገኛል። ፕ/ት ኢብራሂም ራኢሲ እና ሌሎች ባለስልጣናት ኢራን ከአዘርባጀን ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ ላይ የተገነቡ 2 ግድቦችን መርቀው ከከፈቱ በኋላ በሂሊኮፕተር ወደ ታብሪዝ ከተማ ሲያመሩ ነው…
#ኢራን

የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ተሳፍረውባት በነበረው ሄሊኮፕተር በደረሰው አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

ይህንንም የሀገሪቱ የመንግሥት አረጋግጧል።

ከሳቸው በተጨማሪ በሂሊኮፕተር ውስጥ አብረው የነበሩት የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አሚር አብዶላሂያን እና ሌሎች በርካታ ሰዎች ሞተዋል።

ሮይተርስ በአደጋው ፕሬዚዳንቱ ሲጓዙባት የነበረችው ሄሊኮፕተር #ሙሉ_በሙሉ መቃጠሏን " አንድ የኢራን ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

" የፕሬዜዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሄሊኮፕተር በአደጋው ሙሉ በሙሉ ተቃጥላለች። በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም ተሳፋሪዎች ሳይሞቱ አልቀሩም " ብለዋል ስማቸው ያልተጠቀሰው ባለስልጣን።

#ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#Somalia

• " የትውልድ ሀገሬ እየሄደችበት ያለው አቅጣጫ በዚህ መጠን አስግቶኝ አያውቅም "- ሙርሳል ካሊፍ


ጎረቤት ሶማሊያ በሀገሪቱ የጸጥታ ክፍተት ሊፈጠር ይችላል ስትል አስጠንቅቃ ፤ የአፍሪካ ሰላም አሰከባሪ ኃይሎች ከሶማሊያ ለቀው የሚወጡበትን ፍጥነት እንዲቀንሱ መጠየቋ ተሰምቷል።

ሮይተርስ ተመለከትኳቸው ያላቸው ሰነዶች እንደሚያሳዩት ከሶማሊያ ጋር ድንበር የሚዋሰኑ አጎራባች ሀገሮች፣ ዳግም እያንሰራራ የሚገኘው የአል-ሻባብ ቡድን ስልጣን ሊቆጣጠር ይችላል የሚል ስጋት ገብቷቸዋል።

በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) ሰላም አስከባሪ ኃይል እ.አ.አ በታህሳስ መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ሶማሊያን ለቆ ለመውጣት ዝግጅቱን የጨረሰ ሲሆን በቁጥር አነስተኛ የሆነ ኃይል በቦታው እንደሚተካ ይጠበቃል።

ሆኖም የሶማሊያ መንግስት ለአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ጸጥታ ም/ቤት ጊዜያዊ ሊቀመንበር ባለፈው ወር በላከው ደብዳቤ፣ አሁን ካሉት 4 ሺህ ወታደሮች ግማሽ የሚሆኑትን እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ለማስወጣት የተያዘውን እቅድ ወደ መስከረም እንዲያሻግር ጠይቋል።

መንግስት ቀድም ሲል ለህብረቱ አስገብቶት በነበረው እና ሮይተርስ በተመልከተው ሰነድም፣ ሰላም አስከባሪው ኃይል ለቆ የሚወጣበት ጊዜ በሶማሊያ ኃይሎች " ዝግጁነት እና አቅም ላይ እንዲመሠረት " ጠይቆ ነበር።

በተመድ የፀጥታው ም/ቤት ተልዕኮ የተሰጠው ቡድን ባካሄደው የጋር ግምገማም " የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል በችኮላ መውጣታቸው የፀጥታ ክፍተት እንደሚፈጥር " አስጠንቅቋል።

የፓርላማው መከላከያ ኮሚቴ ገለልተኛ አባል የሆኑት ሙርሳል ካሊፍ ፤ " የትውልድ ሀገሬ እየሄደችበት ያለው አቅጣጫ በዚህ መጠን አስግቶኝ አያውቅም " ብለዋል።

ሶማሊያ ለሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ጸጥታ ኃይል ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ደጋፊ የሆኑት አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የሰላም አስከባሪውን ኃይል ለመቀነስ የወሰኑት ዘላቂነት ያለው የረጅም ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ የማድረጉ ሁኔታ ስጋት ውስጥ ስለከተታቸው መሆኑን አራት የዲፕሎማቲክ ምንጮች እና አንድ የዩጋንዳ ከፍተኛ ባለስልጣን ለሮይተርስ ተናግረዋል።

የሶማሊያ ፕሬዝዳንትና የጠ/ሚ ፅ/ ቤት በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም።

#ሮይተርስ #ቪኦኤ

@tikvahethiopia