TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛል።

የአሁኑ ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑን ከቀናት በፊት መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ ኦንላይን (የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች) ፤ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ በወረቀት ነው የሚሰጠው።

ይህ የፈተና አሰጣጥ አካሄድ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ፣ በመንግሥት በጀት ፣ በትምህርት ቢሮዎች ላይ ጫናውን እንደሚቀንስ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ #ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አመልክቷል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶቹ እየተደረጉ ሲሆን የሶፍትዌር ስራው ከወዲሁ መጠናቀቁ ተገልጿል።

የዘንድሮውም ምዝገባ በኦንላይን ሲሆን፣ ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ ይደረጋል ፤ በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ እያለ ይሄዳል ተብሏል።

የተሻሉ የፈተና አዘጋጆች፣ ፈተናዎች እንዳይሰረቁ የሳይበር ጥበቃ፣ የደህንነት ካሜራዎች ፣ የተቋማት ትብብር (ኢንሳ፣ ፈተናዎች አገልግሎት) ፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የፈተና ህትመት ዝግጅት ከዚህ ቀደሙም በተሻለ መልኩ ጠንካራ ስራ በጋራ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከወዲሁ እራሳቸውን ለመመዘኛ ፈተናው ብቁ እና ዝግጁ እያደረጉ መሄድ ያለባቸው ሲሆን መምህራን፣ ወላጆች፣ መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተማሪዎችን እያገዙ ለፈተናው እንዲዘጋጁ ማደርግ አለባቸው።

በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ገብተው ባለፉት ሁለት ብሄራዊ ፈተናዎች ማለትም በ2014 እና 2015 ከተፈተኑት አጠቃላይ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥተው ያለፉት እጅግ ጥቂት ናቸው።

በ2014 ፈተና 896,520 ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 30,034 ወይም 3.3 በመቶ ብቻ ሲሆኑ በ2015 ፈተና 845,099 ተማሪዎች ተፈትነው ማለፍ የቻሉት 27,267 ወይም 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው።

በተለይ ፈተናው በየአካባቢው ካሉ ትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ ወጥቶ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተመዘገበው ውጤት ብዙሃኑን ያስዳነገጠ እንዲሁም የትምህርት ስርዓቱ ያለበትን አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ያመላከተ ሆኗል።

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

የተፈጥሮ ሣይንስ ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ፊዚክስ፣
ኬሚስትሪ፣
ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ታሪክ፣
ጂኦግራፊ፣
ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።

በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።

ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል።

የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የ2016 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና መቼ ሊሰጥ ታቅዷል ?

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም ሰጥተው በነበረ ማብራሪያ ፤ የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።

ሚኒስትሩ ፤ የዚህ ዓመት ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑንም በወቅቱ ገልጸው ነበር።

ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ #ኦንላይን (የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች) ፤ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ #በወረቀት ለመስጠት ነው እቅዱ።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ሰጥተውት በነበረው ማብራሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ #ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ የሶፍትዌር ስራው መጠናቀቁንም ይፋ አድርገው ነበር።

የዘንድሮው ምዝገባ በኦንላይን እንደሚሆን ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ እንደሚደረግ እና በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ እያለ እንደሚሄድ ሚኒስትሩ ከወራት በፊት መግለፃቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መዘገቡ አይዘነጋም።

#ምንጭ@tikvahuniversity (ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ)

#ድብዳቤው ፦ ከክልል የትምህርት ቢሮዎች የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia