TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እኛ የTIVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት በዘር፣ በብሄር እና በሀይማኖት #ያልተከፋፈልን በልዩነታችን #ተከባብረን #ተዋደን እና #ተፈቃቅረን የምንኖር የምስኪኗ እናታችን #የኢትዮጵያ ልጆች ነን! የእናታችንን #ድህነት እስከወዲያኛው ለመሸኘት ደከምን ሰለቸን ሳንል በተሳማራንበት የስራ መስክ ለሀገራችን የምንሰራ ኢትዮጵያዊያን ነን! በሀገራችን #የሰላም ጉዳይ አንደራደርም! ባለን አቅም ሁሉ #ለተቸገሩት እንደርሳለን! ኢትዮጵያዊነታችንን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር እናሳያለን!

ፈጣሪ ሀገራችንን ይጠብቃልን!
አንድ ላይ ስንሆን ምንም አይከብደንም!
ሰውነት ያሰባሰበን ኢትዮጵያዊያን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#IOM

" በቅርብ ከደርሱት #አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው " - የተመድ የስደተኞች ድርጅት

ስደተኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በሊቢያ ባሕር ዳርቻ ተገልብጦ፣ ሕፃናትና ሴቶችን ጨምሮ ከ60 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የተመድ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።

ቅዳሜ የደረሰው አደጋ፣ ወደ #አውሮፓ ለመሻገር በሚሹ ስደተኞች ላይ በሜዲትሬንያን ባሕር ላይ በቅርቡ ከደርሱት አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው ተብሏል።

የተመድ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እንዳለው፣ 86 ሰዎችን ይዛ ስትጓዝ የነበረው ጀልባ፣ ከፍተኛ ማዕበል ገጥሟት በሊቢያ ምዕራባዊ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው " ዙዋካ " ከተሰኘች ከተማ አቅራቢያ ስትገለበጥ 61 ሰዎች #ሰምጠዋል

ድርርቱ ማዕከላዊው የሜዲትሬንያን ባሕር፣ ለፍልሰተኞች አደገኛ የጉዞ መሥመር መሆኑ ቀጥሏል ብሏል።

#ሊቢያ በጦርነት በመታመስ ላይ ያለች አገር ብትሆንም፣ ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ #ሁከትን እና #ድህነት በመሸሽ ወደ አውሮፓ መሻገር ለሚፈልጉ ስደተኞች ተመራጭ መተላለፊያ ሆናለች፡፡

የስደተኞች ድርጅቱ እንደሚለው፣ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈርንጆች 2023 ብቻ ከ2 ሺሕ 500 በላይ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በባሕር ላይ #ሕይወታቸውን_አጥተዋል

መረጃው የቪኦኤ ነው።

@tikvahethiopia