TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢንጂነር አይሻ⬇️

ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሴት የአገር መከላከያ ሚኒስትር ሾመች። ኢንጂነር #አይሻ_መሃመድ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ የአገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ሰብሰባ ኢንጂነር አይሻ መሃመድን #የአገር_የመከላከያ_ሚኒስትር አድርጓቸዋል።

ኢንጂነር አይሻ የአፋር ክልል ተወላጅ ሲሆኑ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በትራንስፎርሜሽናል ሊደር ሺፕ ኤንድ ቼንጅ አግኝተዋል።

በአፋር ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ ሃላፊ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርም ነበሩ። በአሁኑ ወቅትም የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

በዛሬው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባም የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሴት የአገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከተሾሙት 20 የካቢኔ አባላት መካከል አስሩ ሴቶች ናቸው።

ምንጭ፦ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዴፓ‼️

ኢንጂነር #አይሻ_መሃመድ የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አብዴፓ/ ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል።

አብዴፓ የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አወል_አርባ ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

አብዴፓ የፓርቲውን ስራ አስፈፃሚዎች ኮሚቴ አባላት ምርጫንም አካሂዷል። በዚህም መሰረት፦

1.ኢ/ር አይሻ መሃመድ
2.አቶ አወል አርባ
3.አቶ ኢብራሂም ዑመድ
4.አቶ አህመድ ሱልጣን
5.ወ/ሮ ዘሃራ ዑመድ
6.አቶ መሃመድ ሃሠን
7.አቶ መሃመድ ጠይብ
8.አቶ ጣሃ አህመድ
9.አቶ ዓሊ ሁሴን ዌኢሳ
10.አቶ ኤላማ አቡበከር
11.አሊ ሁሴን ዑመር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጠዋል።

ከህዳር 23 ጀምሮ በሰመራ ሲካሄድ የቆየው የአብዴፓ 7ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባዔም ባለፉት አመታት በክልሉ በነበረው አፈፃፀም እና በወደፊት የልማት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንጂነር አይሻ መሃመድ‼️

#የመከላከያ_ሰራዊት_ቀን የሰራዊቱን አቅም በማሳየት እና የሰራዊቱ ሞራል በመገንባትም ጭምር ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር #አይሻ_መሃመድ አስታወቁ።

ሚንስትሯ በሰጡት የማጠቃለያ መግለጫ 7ተኛው የኢፊዲሪ የመከላከያ ሰራዊት ቀን በስኬት ተጀምሮ በስኬት እንደተጠናቀቀ ተናግረዋል።

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ አባላት ያሉት ኮሚቴ ተዋቅሮ በአሉን እንዴት እናስኪድ በሚለው ጉዳይ ላይ መግባባት ላይ ተደርሶ ወደ ስራ እንደተገባ ሚንስትሯ አስታውሰዋል።

በተለያዩ ቦታዎች የተደረጉት የፓናል ውይይቶች እና የተለያዩ ዝግጅቶች ህብረተሰቡንና የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የበለጠ እንዲቀራረቡ እንዳደረገም ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ሰአት የመከላከያ ሰራዊተ በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች ህገ መንግቱን የማስከበር ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ እና የሕብረተሰቡን ሰላም ለመጠበቅ የሃገሪቱን ሉአላዊነት ከውስጥም ከውጭም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ እይተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ነው መከላከያ ሚኒስትሯ የገለፁት።

ምንጭ፦ EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የመከላከያ ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር #አይሻ_መሃመድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ አዲስ ከተሾሙት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አምባሳደር መሀመድ #ሳሊም_አልራሺዲ ጋር በፅ/ቤታቸው ተነጋግረዋል፡፡ አምባሳደር መሃመድ በዚሁ ወቅት የሁለቱን አገሮች ግንኙነቶች በማሳደግ በኩል ጠንክረው እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ በተለይም በአቅም ግንባታ ዘርፍ ተቋሙን ለማገዝ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ ክብርት ሚኒስትሯም ሁለቱ አገራት ያላቸው የረጅም ጊዜ ግንኑኙት ዘመናትን የተሻገረ መሆኑን ገልፀው አምባሳደር መሀመድ በኢትዮጵያ ውጤታማ የቆይታ ጊዜያት እንዲኖራቸው ተመኝተዋል፡፡

Via Defense Minister Office, Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia