TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔹 " እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሙስና የሚፈጸመው #በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው " የመ/ግ/ን/ባ

በመንግሥት የግዥ ሒደት እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሙስና የሚፈጸመው በኮንስትራክሽን ዘርፍ መሆኑን፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ ይህን ያስታወቀው ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በዘንድሮ በጀት ዓመት በ169 የፌዴራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሲስተም ተግባራዊ ተደርጎና አፈጻጸሙን ለማሳደግ፣ ከንግድ ማኅበረሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ነው፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐጂ ኢብሳ ምን አሉ ?

- በመንግሥት በግዥ ሥርዓት ውስጥ፣ ከ80 እስከ ከ90 በመቶ በላይ ሙስና የሚፈጸመው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው ብለዋል።

- ስሙን መጥቀስ ያልፈለጉት የመንግሥት ተቋም #በጨረታ አንደኛ የወጣ ድርጅት እያለ ሦስተኛ ከወጣው ጋር ውል መግባቱን፣ በዚህም ምክንያት ባለሥልጣኑ እስከ ፍርድ ቤት በመሄድ ሒደቱ እንዲቋረጥ ማደረጉን ገልጸዋል፡፡

- ከኮንስትራክሽን ጋር ተያይዞ ጨረታ የሚያወጡ የመንግሥት ተቋማት #የሚፈልጉዋቸው ተጫራቾች ካልመጡ እስከ #መሰረዝ እንደሚደርሱ አመልክተዋል።

- የመንግሥት ተቋማት ተጫራቾችን ሆን ብለው ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ ሕጎችን እንደ ምክንያት እንደሚጠቀሙ፣ ያሸነፉ ተጫራቾችንም #እንዲሰላቹ በማድረግ ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል፡፡

- በመንግሥት የግዥ ሥርዓት ምክንያት የሚመጡ ክሶች መኖራቸውን ገልጸው በዓመት እስከ 150 የሚደርሱ ክሶች እንደሚስተናግዱ ተናግረዋል። በአብዛኛው ጨረታ የማውጣትና የሚገመገምበት መሥፈርት በመለያየቱ ምክንያት በርካታ ተጫራቾች ክስ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የኢጋድ አባል አገሮችና የነጋዴ ሴቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቴ ምን አሉ ?

- በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ከታዩ ክፍተቶች አንዱ በጠቅላላ የመንግሥት ግዥ መባሉ ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል።

- የመንግሥት ግዥ ተብሎ ስያሜ ቢሰጠውም የመንግሥት ተቋማትና የንግዱ ማኅበረሰብ የሚገናኙ በመሆናቸው ከስያሜ ጀምሮ ማስተካከያ ይፈልጋል ብለዋል።

- የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ሙስናን ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጻዋል። ከዚህ ቀደም #በዩኒቨርሲቲዎች በሚደረጉ ግዥዎች ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶች እየቀረቡ እንደነበርና ሥርዓቱ መዘመኑ በተወሰነ መንገድ ችግሩን መቀረፉን አስረድተዋል፡፡

- በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ለሚታዩ የሙስና ብልሹ አሠራርን ከሥሩ ማድረቅ እንደሚገባ፣ በተለይ ተጫራጮች ወደ ተቋማት ሲሄዱ #ሲስተም_የለም የሚለው ቋንቋ የችግሩ መጀመርያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

- ተጫራቾች ወይም የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ለሙስና እንዳይጋለጡ መብቶቻቸውን ለማስጠበቅ ሞጋችና ተከራካሪ መሆን አለባቸው ብለዋል።

የመንግሥት ግዥ የንብረት ባለሥልጣን የመንግሥት ግዥ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ከበደ ምን አሉ ?

- የነባሩ የወረቀት የግዥ ሥርዓት የሙስና ተጋላጭነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት እየተደረገበት ነው ብለዋል።

- የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት መኖሩ የሚቀርፏቸው ችግሮች ሰፊ ከመሆናቸው ባሻገር፣ ለብዙ ተጫራቾች ዕድል ከመስጠት አኳያ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

- የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት በ2015 ዓ.ም. ሲጀመር የተመዘገቡት የንግድ ማኅበረሰብ አባላት 100 ብቻ የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጥቅሉ ከ15‚000 በላይ ተሻግረዋል።

- ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ በጀቷ 70 በመቶ የሚውለው ለግዥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸው ይህም በገንዘብ ሲቀየር 560 ቢሊዮን ብር ለግዥ እንደሚውል ተናግረዋል።

#ReporterNewspaper

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በማዕከል ደረጃ ያለውን የሰራተኛ ቁጥር በመቀነስ ከፍተኛ የሥራ ጫና ወደ አለባቸው ወረዳ እና ተቋማት #ስርጭት እንዲደረግ ወስኗል። ውሳኔው የተወሰነው ዛሬ በተካሄደው የካቢኔው የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲሆን ውሳኔው ከተማዋ ከምታመነጨው ገቢ እና ለህብረተሰብ ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር የማይመጣጠን በመሆኑ የተወሰነ እንደሆነ ነው የተገለጸው።…
#AddisAbaba #Update

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በውክልና ሰጥቶ የሚያሰራቸው የመንግሥት ተቋማት አገልግሎቶች የትኞቹ ናቸው ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ሰኞ ዕለት ካሳለፋቸው ውሳኔዎች ውስጥ አንዱ የአስተዳደሩ ተቋማትን አገልግሎቶችን ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ የሚለው እንደሆነ ይታወሳል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ለቢቢሲ አማርኛ በሰጡት ቃል ፤ በካቢኔው ስብሰባ ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶቻቸውን በውክልና ለግል ተቋማት እንዲያስተላልፉ ውሳኔ ላይ የተደረሰባቸው የከተማ አስተዳደሩ 5 መሥሪያ ቤቶች እና ሆስፒታሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከእነዚህ የከተማ አስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የንግድ፣ የትራንስፖርት እንዲሁም የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮዎች ይገኙበታል ብለዋል።

የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዲሁም አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን አገልግሎቶቻቸውን በከፊል ለግሉ ዘርፍ ከሚያስተላልፉት ውስጥ መካተታቸውን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ስር የሚገኙት የካቲት 12 እና የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታሎችም የዚህ ዕቅድ አካል ናቸውም ብለዋል።

ተቋማቱ ለግሉ ዘርፍ እንዲያስተላልፏቸው የተመረጡት የመንግሥት አገልግሎቶች 46 እንደሆኑ የገለፁት ወ/ሮ ሂክማ  ከእነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ የንግድ ፈቃድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና እድሳት እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩን የግብይት ማዕከላት የማስተዳደር አገልግሎቶች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።

አገልግሎቶችን ለሶስተኛ ወገን ማስተለለፍ ለምን ተፈለገ ?

ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ፦

- የተመረጡ አገልግሎቶችን ለግል ተቋማት ለማስተላለፍ የተወሰነው የመንግሥት ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ፍጥነት፣ ጥራት እና ውጤታማነት የተሻለ ለማድረግ ሲባል ነው።

- ሕብረተሰቡ ከአገልግሎት ውጤታማነት፣ ከአገልግሎት ተደራሽነት ጋር የሚያነሳቸው ጥያቄዎች አሉ። እነዚህን የአገልግሎት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አንዱ መፍትሄ አውትሶርስ አድርገን የግሉ ዘርፍ እንዲሰራቸው ማድረግ ነው።

- ይሄንን ሥራ የሚወስደው የግል ዘርፍ ለትርፍ የሚሰራ አካል ነው። ለትርፉ ሲል ሕብረተሰቡ ጋር የበለጠ ተደራሽ ይሆናል።

- መንግሥት ሁሉም ነገር ላይ ትኩረት አድርጎ ላይሰራ ይችላል ፤ እነዚህ አገልግሎቶች ወደ ግል ተቋማት ሲተላለፉ የመንግሥትን የመቆጣጠር እንዲሁም ሕግ እና ሥርዓትን ተግባራዊ የማድረግ አቅምን ጠንካራ ያደርጋል የሚል እምነት አለ።

- የተመረጡ አገልግሎቶች ከሚተላለፍላቸው አካላት መካከል #የግል_ባለሀብቶች ይገኙበታል። ባለሀብቶች አገልግሎቱን ተረክበው እንዲሰሩ የሚመረጡት #በጨረታ ነው።

- በተጨማሪ አገልግሎቶች ከሚተላለፉላቸው አካላት መካከል ተደራጅተው የሚሰሩ የንግድ ዘርፍ ማኅበራት፤ የተለያዩ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ። እነሱም ሥራውን ወስደው መሥራት የሚችሉበት ዕድል ይኖራል። ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ለሚሳተፉም ዕድል አለ።

- የከተማ አስተዳደሩ የተመረጡ አገልግሎቶችን ለሶስተኛ ወገን አካላት የሚያስተላልፍ ቢሆንም አገልግሎት አሰጣጡን ይቆጣጠራል።

ለምሳሌ ፦ የንግድ ፈቃድ ስታንዳርዶችን የሚያወጣው መንግሥት ነው። የግሉ ዘርፍ ይህንን ስታንዳርድ አሟልቶ ለመጣ ሰው ፈቃዱን ይሰጣል። አውትሶርስ አድርገው አገልግሎቱን ለመስጠት የወሰዱ ተቋማት በስታንዳርዱ መሠረት ‘ሰሩ አልሰሩም’ የሚለውን ቁጥጥር የሚያደርገው እና ፈቃዶችን ቼክ የሚያደርገው መንግሥት ነው።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia