TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Woldia

ከደሴ ወደ ወልድያ ከተማ የሚገባው የኤሌክትሪኮ ኃይል እክል እንዳጋጠመው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስታወቁን የወልዲያ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

ተቋሙ ከደሴ ወልድያ ከተማ የሚገባው 66 ኬቪኤ የትራንስሚሽን መስመር ባልታወቀ ምክንያት በሀብሩ ወረዳ ቀበሌ " ቀርጨም በር " አካባቢ ባለ 4 ቋሚ ምሰሶ በእሳት በመቃጠሉ ምክንያትና የደረሰውንም ጉዳት የአካባቢው ነዋሪ (ማኅበረሰብ) አደጋው መድረሱን ለሚመለከታቸው አካላት ባለማሳወቁ በፍላጋ ማግኘቱን አስታውቋል።

ተቋሙ የደረሰውን ጉዳት በመጠገን አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑን አስታውቆ ኅብረተሰቡ በትእግስት እንዲጠብቅ አሳስቧል።

ምንጭ ፦ የወልዲያ ከተማ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#Woldia

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና ለአማራ ክልል መንግሥት ጥያቄዎችን ማቅረቡን ገልጿል።

ከተማ አስተዳደሩ ቀደም ሲል የተጀመረውና ኅብረተሰቡ ለጤና እክልና ለተለያዩ ችግሮች እያደረገ ያለው የከተማዋ የአስፋልት መንገድ ግንባታ በፍጥነት ወደ ሥራ የሚገባበትን መንገድ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለ ስልጣን አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው ጥያቄውን አቅርቧል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የኅብረተሰቡን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በተገቢው መንገድ ምላሽ ለመስጠት ወቅቱን የሚዋጅ አደረጃጀት መፍጠር የሚያስችለውን የከተማዋን የሪጅዮ ፖሊታንት መዋቅር ጥያቄ ለክልሉ መንግሥት በድጋሜ በጽሑፍ አቅርቧል።

ከተማ አስተዳደሩ ለከተማዋ መልማት ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ተገቢ ጥያቄዎች የከተማዋን እድገት የሚመኝ ሁሉ ጉዳዮቹን አጀንዳ በማድረግ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡን ከወልዲያ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Amhara , #Woldia 📍

" የጥሩ ባህላዊ ሕግ፥ ሥርዓት ባለቤት ነን ብለን የምንናገርበት የሞራል አቅም እያጣነ ነው " - የውይይት ተሳታፊዎች

PDN (Partners In sustainable Development) የተባለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ከUSAID Prmoting the Experience in peacful Coexistence of Diverse Communities in Wollo, Amhara Region ፕሮጀክትና ከባህል ቱሪዝም ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀው በባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት ላይ ያተኮረ ውይይት በወልዲያ ተካሄደ።

የሃይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእድር መሪዎች እና የመንግሥት ባለድርሻ አካላት የተካተቱበት ነበር።

የወልዲያ ኮሚኒኬሽን ባወጣው ዘገባ ተሳታፊዎቹ " እንደ ወሎየነት ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያዊነት ከመቻቻል ፣ ከአብሮነት ፣ ከእውነታነት ፣ ከአድሏዊነት የጸዳ በአበጋሮች፣ በሼሆች፣ በቀሳውስቶች፣ በሀገር ሽማግሌዎች፣ በእድሮች፣ በለገገዲ፣ በመሳል፣ በሼህ ለጋ፣ በዘወልድ፣ የሚከናወኑ ትክክለኛ ባህላዊ የዳኝነት (ፍርድ) እና የግጭት አፈታት ባህላዊ ስርዓት ብሎም እስከ አባ ገዳ ፣ አውራምባ እና ሌሎች ባህላዊ የመልካም የአስተዳደር ስርዓት ሲዳሰስ የድንቅ ባህል ፣ ትውፊት ፣ ወግ፣ እሴት፣ ስርዓት ባለቤት መሆናችንን ባንክድም አሁን ላይ እያፈርን ነው " ብለዋል።

አክለውም በእውነት እና ሚዛናዊነት ቦታ ሀሰትና አድሏዊነት እየነገሠ፤ በመቻቻልና አብሮነት ፈንታ መለያዬት እየገነነ፤ በጥሩ ባህላዊ እሴት አካባቢና ሀገር መፈናቀልና መገዳደል እየሰፈነ፤ አባቶቻችንና እናቶቻችን የገነቡት ቅርስ በቱሪዝም ሀብት የሚሰጠው ጥቅም ተዘንግቶ ቤተ-እምነትን እየፈረሰ ፣ የእምነት አባቶች እየተገደሉ፣ ህጻናትንና ሴት ለሞትና ስቃይ እየተዳረጉ ነው ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሀገር በቀል ሽማግሌ ተንቆ በባህላችን፣ በወጋችን፣ በእምነታችን፣ ቋንቋችን፣ የማይመስለን "ገልጋይ መስሎ ገፍታሪ" ካላስታረቀን ብሎ የሚባዝን የራሳችን ወገን እየተገዳደረን ፤ ይን እና ይህንን የመሰለው ተዳምሮ የጥሩ ባህላዊ ሕግ፣ እሴት ባለቤት ነን ብለን የምንናገርበት የሞራል አቅም እያሳጠን ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Amhara-Woldia-02-13

@tikvahethiopia
#Amhara , #Woldia📍

በወልዲያ ከተማ ዳርቻ የተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰማው የተኩስ ድምፅ " #በወታደራዊ_ስልጠና_የዒላማ_ልምምድ " ምክንያት መሆኑን የከተማው የሰላምና ሕዝብ ደህንነት ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል።

@tikvahethiopia
#Woldia

የእሳት አደጋ ባልና ሚስትን ህጻን ልጃቸውን ጨምሮ ለሞት ዳረገ።

ወልድያ ከተማ በ06 ቀበሌ " ጎልጎታ " ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር የካቲት 18 ለ19/2014 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ባልና ሚስትን ህጻን ልጃቸው ጨምሮ ለሞት ሲዳርግ 3 ሰዎችን በቃጠሎ ለቁስለት ዳርጓል።

3ቱ ቁስለኞች በወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

የእሳት አደጋው መንስኤና ንብረት ላይ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት እየተጣራ መሆኑን የወልዲያ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዋግኽምራ 📍 የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ፤ ዋግ ኽምራ ዞን የሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማህበረሰቡን መጎብኘታቸውን ፅ/ቤታቸው አስታውቋል። ዶ/ር ዐቢይ ፤ ከማህበረሰቡ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት የአገው ሕዝብን የኪነ-ህንፃ ልህቀት እና ፍልስፍናዊ መሰረት አድንቀው እነዚህን እሴቶች የመጠቀም እና ፈተናዎችን ለማሸነፍ አንድነትን ማስጠበቅ ያለውን ጠቀሜታ…
#Woldia📍

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የዒድ አል ፈጥርን ዋዜማ ከወልድያ ከተማ ሕዝብና በአካባቢው ካለው ሠራዊት ጋር ማክበራቸውም ገለፀዋል።

በዚህም የተሰማቸድን ደስታ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " ጀግናው ሠራዊታችን የሕዝቡን ደኅንነት እና ልማት በደሙ ለማስከበር ወትሮ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል። " ያሉ ሲሆን " ይሄንን ሕዝብና ሠራዊት በዓላማ አንድነት ያጸናውን ግንብ፣ እንኳን ሊደፍሩት ሊጠጉት አስፈሪ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት በትንሳኤ በዓል ዋዜማ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ተገኝንተው ከማእከላዊ እዝ እና ከማህበረሰቡ ጋር ተገናኝተው እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ፦ " ወልድያ ገብርኤል በእሳት እየተቃጠለ ነው የሚለው መረጃ የተዛባ መረጃ ነው። ከማንም ይምጣ ተራራ በሰተሰሜን አቅጣጫ አባው ተራራ አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የአካባቢው መኅበረሰብ እና የጸጥታ አካሉ እሳቱ ቃጠሎው እንዳይስፋፋ የማድረግና የማጥፋት ስራ በመስራት ይገኛል። ሆኖም ወልድያ ገብርኤል በእሳት እየተቃጠለ ነው የሚለው መረጃ የተዛባ መረጃ ነው። በተራራው…
#Update #Woldia

ፖሊስ ደን በማቃጠል ተሳትፈዋል ያላቸውን 59 ሰዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

ታሪካዊውንና ጥንታዊውን የምንም ይምጣ የተራራ ደንን በእሳት በማቃጠል ተሳትፈዋል ያላቸውን 59 ሰዎችን የወልድያ ከተማ ፖሊስ በሕግ ቁጥጥር ስር አውሏል።

ትላንት የወልድያ ከተማ መስራች የታላቁ ራስ ዓሊ ቤተ መንግሥት የነበረበት አካባቢ ደን ለቃጠሎ የተዳረገ ሲሆን አጥፊዎቹ በአቀዱት ልክ ወደ ሌላ አካባቢ ሳይዛመት በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ከተማ አስተዳደሩ ቃጠሎው ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይዛመት ላደረጉ ሁሉም የጸጥታ አካላት እና የአካባቢው ነዋሪዎች ምስጋና አቅርቧል።

ምንጭ፦ ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን

@tikvahethiopia
#WOLDIA #WOLLO

ላለፉት ሁለት ሶስት ዓመታት በኮቪድና በጦርነቱ ምክንያት ትምህርታቸው ተስተጓጉሎ የቆዩት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች ከትናንት ጀምሮ ወደ ግቢያቸው እየገቡ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ዛሬ ህዳር 3/ 2015 ዓ.ም በምህንድስና የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 1062 ወንዶች እና 332 ሴቶች በድምሩ 1394 ተማሪዎችን በመጀመሪያና በ2ኛ ዲግሪ አስመርቋል።

መረጃው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ እና የውሎ ዩኒቨርሲቲ ነው።

@tikvahethiopia
#Woldia : የወልድያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በይፋ ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪ አቀረበ።

ጤና ጣቢያው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው ደብዳቤ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ተደጋጋሚ ጦርነት ከተጎዱት ተቋማት መካከል አንዱ ይኸው የወልድያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አንዱ ስለመሆኑ ገልጿል።

በጦርነት ወቅት በደረሰው ጉዳት ተቋሙ ከህንፃው በቀር ምንም ነገር የሌለው መሆኑን የገለፀ ሲሆን ችግሩ አሳሳቢ በመሆኑና ሁሉም ዜጋ በጨለማ የሚዋለዱትን እናቶችን ፣ የሞያተኞችንም ችግር በመመለከት በቻለው መጠን እገዛ እንዲያደርግ ይፋ ጥሪ አቅርቧል።

1. ለጥበቃ ምቹ የሆነ በር ስለሌለዉ በር ማሰራት የሚቻልበት፤

2. ዙሪያ ገባው አጥር የሌለዉ ስለሆነ አጥር የሚሰራበት፤

3. መብራት ሲጣፍ የላብራቶሪ አገልግሎት የወሊድ አገ/ት መስጠት ስለማይቸል ጄኔነተር የሚማላበት፤

4. የዉስጥ ለዉስጥ የዉሃ መስመር ከቆይታው የተነሳ የተበላሽ ስለሆነ የማደስ ስራ የሚሰራበት፤

5. የማዋለጃ ቁሳቁስ እና ሌሎች የቁስል መስፊያ መቀሶች ማጽጃ (Sterilizeation ማለትም Auto Clive መግዛት የምንችልበት (ልግሳ)፤

6. የጸሀፍት መሳሪያ ፣ ኮምፒዉተር እና ፕሪንተሮች ለማሟላት

7. ወንበርና ጠረጴዛዎች አጅግ አንገብጋቢ ችግሮች ስለሆኑ አቅም ያላችሁ ሁሉ የድጋፍ ትብብር ታደርጉ ዘንድ በጤና ጣቢያው ታካሚዎች እና በወልድያ ማህበረሰብ ስም ተጠይቋል።

የባንክ አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፦ 1000023835871

ይህ ጤና ጣቢያ ከ1964 ዓ/ም ጀምሮ ከሆስፒታል ባልተናነሰ መልኩ በዙሪያው ላለው የገጠር ቀበሌና ለከተማ አስተዳደሩ ህዝብ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

@tikvahethiopia
#Woldia

በወልድያ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ  ፤ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎችም ተጥለዋል።

ወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ እና ክልከላ ማስቀመጡ ተገልጿል።

ክልከላዎቹ ፦

- ጭፈራ ቤቶች፥ ካፍቴሪያዎች፣ ሬስቶራንቶች እና የመሳሰሉት ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

- ለባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00  ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ፤ ከተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ለጸጥታ ሥራ ከተመደቡ ተሽከርካሪዎች ውጭ በዚህ ምደባ ስምሪት ያልታቀፉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2:00 እስከ ጧቱ 12:00  ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።

- የሰው እንቅስቃሴ ለጸጥታ ሥራ ከተመደበው ሰው ውጭ ከምሽቱ 3:00 እስከ ጧቱ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በማንኛውም ቦታና ጊዜ ለጸጥታ ሥራ ስምሪት ከተመደበ አካል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ሥራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

- የመንግሥትን የታጠቀ ኀይል ያስከዳ፣ በተለያየ መንገድ አማሎ የጦር መሳሪያ የገዛ፣ የለወጠ፣ ባልተገባ መንገድ መታወቂያ የሰጠ፣ መንገድ የመራ ማንኛውም አካል በሕግ ተጠያቂ ይሆናል ተብሏል።

- የመንግሥት የጸጥታ ኀይል ሕግና ስርዓትን ለማስከበር በሚያከናውናቸው ተግባሮች ዙሪያ ማንኛውም ሰው የመተባበር ግዴታ ተጥሎበታል ፤ የማይተባበር በሕግ ይጠየቃል ተብሏል።

የኮማንድ ፖስቱ በአብዛኛውን በሌሎች ከተማዎች የተጣሉ ክልከላዎችን አይነት ይዘት ያለው ክልከላ ነው የጣለው። (#ሙሉ ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል)

ኮማንድ ፖስቱ ይህ ውሳኔ የተላለፈባቸው ምክንያቶች ፦ በከተማው የተጀመሩ ልማቶችን " አመጹን መቀላቀል ሲገባህ ልማትን እያስቀጠለክ " በሚል ዛቻ ልማትን የማደናቀፍ ፤ በሙስና፥ በሌብነት፥ እና በተለያዩ ብልሹ ወንጀሎች ስጋት ያለባቸው አካላት የዕለት ጉርስ ፈላጊዎችን በገዘብ በመግዛት ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠርና ለማባባስ የሚያደርጉት ሙከራ በመረጃ ደረጃ የተገኘ በመሆኑ ነው ብሏል።

ከዚህ ባለፈ የትንሳኤ እና የረመዳን ሃይማኖታዊ ሁነቶችን በሰላም ለማጠናቀቅ ለዕኩይ ዓላማ የተሰማሩ ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠር ነው ሲል አሳውቋል።

(የወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia