TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዎላይታ

“ ሆስፒታል ባለመኖሩ ሕዝቡ እስከ ሞት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ነው ” - አንድ የጤና ባለሙያ

“ ዞኑም፣ ከተማ አስተዳደሩም ሆስፒታል ቢኖር የሚል ሀሳብ አለው ” - የወላይታ ሶዶ ዞን ጤና መምሪያ።

በወላይታ ዞን የሚገኙ አንድ የጤና ባለሙያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦ " የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ሕዝብ የመንግሥት ሆስፒታል ባለመኖሩ ሕዝቡ እስከ ሞት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ነው " ብለዋል።

" እንደ አገር የሚተገበረው የሕዝብ ጤና ተቋማ ጥምርታ ሌሎች አካባቢዎች ላይ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ ያለ ቢሆንም ለቦሎሶ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ግን ተግባራዊ አልሆነም " ሲሉ ወቅሰዋል።

" የሕዝብ ብዛት ከ1 ሚሊዮን እስከ 1.5 ሚሊዮን ከሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ተሰርቶ አገልግሎት መሰጠት እንዳለበት ይገለጻል። የቦሎሳ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ሕዝብ ከ1 ሚልዮን እንደሚበልጥ ይገመታል። ህዝቡ ግን ይህንን ሰብአዊ መብት ለማግኘት አልታደለም " ብለዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ አነጋግሯል።

ምን መለሱ ?

አረካ እና ቦሎሶ ሶሬን አማክሎ አገልግሎት የሚሰጥ ዱቦ የመጀመሪያ ደረጃ የግል ሆስፒታል አለ። የሕዝቡ ቅሬታ ‘የመንግሥት ሆስፒታል ለምን አይኖርም’ የሚል ነው ቅሬታው አግባብነት ያለው ነው።

ሌሎችም ምንም አይነት ሆስፒታል የሌለባቸው አካባቢዎች ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶ የመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እየገነባ ነው የቆየው ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ይኼኛውም አካባቢ (ቦሎሳ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ) በመንግሥት ሆስፒታል ተደራሽ ቢሆን ጥሩ ነው የሚለውን እንደ ዞን መግባባት ላይ እየደረስን ነው።

እንደ ዞን፣ የከተማ አስተዳደርም ይሄ ጥያቄ የሕዝብ ጥያቄ እንደሆነ ተቀብሏል። ጥያቄው እንደ ጥያቄ እንዳለ እናውቃለን፤ ለግንባታው የሚያስፈልገው በጀት እንዲታቀድበት፣ በመደበኛ የመንግሥት በጀት እንዴት መስራት እንደሚቻል እየታሰበበት ነው።

በሌላ በኩል ቅሬታ አቅራቢ ጤና ባለሙያው በበኩላቸው፣ “ ለህዝብ ተሰርቶ አገልግሎት እንዲሰጡ የተሠሩ ጤና ጣቢያዎች ቢኖሩም ብዙዎቹ #ዝግ_ናቸው” ብለዋል።

አንድ የግል ሆስፒታል ቢኖርም ለመታከም የዋጋ መናር እንደሚስተዋልበት፣ የብቁ ቀዶ ጥገና ችግር እንዳለ፣ በዚህም አንዲት እናት ችግር እንደደረሰባቸው፣ የጤና ባለሙያዎች ከሰለጠኑበት ሙያ ውጪ ስለሚሰሩ ከዚህ በፊት ሁለት እናቶች እንደሞቱ አስረድተው፣ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

ይህንኑ ቅሬታ በተመለከተ የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ  ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ምን ምላሽ ሰጡ ?

ትክክል ነው። ያለው ሂደት አጠቃላይ ዝርዝሩን እኛም ይዘናል። ሕዝቡም ያነሳል፣ ትክክል ነው። የሕክምና ባለሙያዎች (የዱቦ ሆስፒታል) አሁን በቂ እውቀት ያላቸው ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ነው። አጋጣሚ የተፈጠሩ ክፍተቶች ለምን ተፈጠሩ የሚለውን እናያለን።

በእኛ ደረጃ ዝግ የሆነ ጤና ጣቢያ የለም። ጤና ባለሙያ ተመድቦ ሁሉም ጤና ባለሙያዎች አገልግሎት እየሰጡ ነው በሥራ ሰዓት። ግን አልፎ አልፎ ከትርፍ ሰዓት ክፍያ በጊዜ ባለመከፈሉ ምክንያት ‘አልተከፈለም’ በሚል ሥራ ቦታ ላይ የባለሙያ አለመገኘት ሁኔታዎች አሉ።

የጤና ባለሙያው በበኩላቸው ፦
- የትርፍ አበል አለመከፈል፣
- በደመወዝ መቆራረጥ ምክንያት ቅሬታ ስላለ፣ ሌጋማ፣ ዎይቦ፣ ጋራ ጎዶ፣ ባንጫ እና ሌሎች ጤና ጣቢያዎች በቀን አንድ ባለሙያ ገብቶ የሚመጡ ሕሙማንን ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ መረጃ ከመስጠት ውጭ የሚሰጠዉ አገልግሎት የለም " ብለዋል።

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia