TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የምስራቅ #ወለጋ ዞን ፀጥታና አስተዳደር ሀላፊ አቶ #ታከለ_ቶሎሶ ለBBC Afaan Oromoo እንደተናገሩት፣ ከካማሸ ዞን የተፈናቀሉ 13 ሺ አባወራዎች በምስ/ወለጋ ዞን በሳስጋና በሃሮሊሞ ወረዳዎች በሚገኙ መጠልያ ጣቢያዎች ሰፍረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል #ብርሃኑ_ጁላ

‹‹በውትድርና ዘመኔ በራስ ሕዝብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ #ጥቃት ተፈጽሞ #ያየሁት በምዕራብ ወለጋ ነው››

‹‹ለረጅም ዓመታት በውትድርና አገልግያለሁ፣ እንዲህ ዓይነት #ጭካኔ በወለጋ ከተፈጸመው በስተቀር አይቼ #አላውቅም፤››

‹‹በምዕራብ ወለጋ የተፈጸመውን ጭካኔ በቅርቡ #በቪዲዮ ምሥል ጭምር #ታዩታላችሁ፤››

‹‹የመከላከያ ሠራዊቱ ወደ #ወለጋ ሲገባ ያገኘነው #ጉድ ዘግናኝ ነው፤››

https://telegra.ph/በውትድርና-ዘመኔ-በራስ-ሕዝብ-ላይ-ጭካኔ-የተሞላበት-ዘግናኝ-ጥቃት-ተፈጽሞ-ያየሁት-በምዕራብ-ወለጋ-ነው-01-09-2
የሀዘን መግለጫ!

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ 3ተኛ ዓመት በማነጅመንት የ3ትኛ ድግሪ እጩ ተማሪ የነበረው ተማሪ ገመቺስ ታደሰ ጉቴ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ ፣የወለጋ ዩኒቨርሲቲ አስተስዳደር የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ፣ለቤተሰቦቹ ፣ለጒደኞቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛል።

#ወለጋ_ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia