TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ታዬ ደንደአ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ  ታዬ ደንደአ በህግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፀጥታ እና ደኀንነት የጋራ ግብረ ኃይል አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Update

የአቶ ታዬ ደንአደን በቁጥጥር ስር መዋል በተመለከተ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል ምን አለ ?

ግብረ ኃይሉ አቶ ታዬ ደንደአ፥ ከለውጡ በፊት የኦነግ አባል የነበሩና በእስር ቤት የቆዩ መሆኑን ገልጿል።

የለውጡ መንግስት ባደረገላቸው ምህረት ከማረሚያ ቤት ተለቀው በተሰጣቸው እድል በተለያዩ የክልል እና የፌደራል መንግስት የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲሰሩ ነበር ብሏል።

ይሁን እንጂ አቶ ታዬ ከህዝብና የመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተለይም ደግሞ የሰላም ሚንስትር ዴኤታ ሆነው ሰላምን ለማስፈን መሥራት ሲገባቸው በተቃራኒዉ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ፀረሰላም ኃይሎች ጋር በመተሳሰር ለጥፋት ተልዕኮ በህቡዕ ሲሰሩ እንደተደረሰባቸው ገልጿል።

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ሲፈፀሙ በነበሩ የሽብር ተግባራት በተለይም ደግሞ #ከእገታ_ጋር በተያያዘ እጃቸው እንደአለበት ተደርሶበታል ብሏል።

አቶ ታዬ ደንደአ፤ በመንግስት ቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደሚችሉ ሲገምቱ ታጋይ ለመምሰል በራሳቸውና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች አፍራሽና ፀረ ሰላም ፅሁፎችን፣ ንግግሮችንና መግላጫዎችን በማን አለብኝነት ሲያስተላልፉና ሲሰጡ ቢቆዩም ከተጠያቂነት ማምለጥ ባለመቻላቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል።

ግብረኃይሉ አቶ ታዬ መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን ተቀብለው እየሰሩ በነበረበት ወቅት መንግስታዊና የፓርቲ መዋቅሩን በሴራ ለመናድ በህቡእ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውና ጥናትና ክትትል ሲደረግበት እንደነበር አመልክቷል።

በተደረገው ክትትልም አቶ ታዬ " ከኦነግ ሸኔ " አመራሮችና በሽብር ወንጀል ከተጠረጠሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ጋር ትስስር በመፍጠር መንግስትን በአመጽ፣ በሽብርና፣ በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲያሴሩ እንደ ተደረሰበት ገልጿል።

ተጠርጣሪ ታዬ በህግ ቁጥጥር ሥር ሲውሉ በመኖሪያ ቤታቸው ዉስጥ በተደረገ ፍተሻ ፦
* በህቡዕ ለሚያደርጓቸው ፀረ-ሰላም እንቅስቃሴ ሲገለገልባቸዉ የነበሩ የተለያዩ 9 ሞባይሎች፣
* 4 ላፕቶፖች፣ 3 አይፖዶች፣ በርካታ ፍላሾች፣
* 4 የተለያዩ ተሸከርካሪ ሰሌዳዎች
* ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣
* ክላሽንኮቭ ጠመንጃና ሽጉጦች ከመሰል ጥይቶች ጋር
* የኦነግ ሸኔ አርማዎችና በተለያዩ ግለሰቦች ስም የተዘጋጁ የኦነግ ሸኔ መታወቂያዎች፣ ሰነዶችና ማስታወሻዎች ተገኝተዋል ብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ በብርበራ ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በ3 መታወቂያዎች የሚጠቀም አንድ " የኦነግ ሸኔ " አባል ተደብቆ መገኘቱንና በቁጥጥር ሥር መዋሉንም ገልጿል።

ግብረኃይሉ አቶ ታዬ ደንደአ በተመደቡባቸው ከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ላይ ሆነው በተደጋጋሚ መንግስትን #ገዳይ እና #ጨፍጫፊ እያሉ ሲወቅሱ የሚደመጥ ቢሆንም፤ በተግባር ግን ከሽብርተኞች፣ ጽንፈኛችና ነፍሰ ገዳዮች ጋር የጥፋት ትስስር የነበራቸው ራሳቸው መሆኑ በተደረገ ክትትል ተረጋግጧል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TayeDendea

አቶ ታዬ ደንደአ ትላንት በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ የስንብት ደብዳቤ አያይዘው ከለጠፉ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ጠንካራ ቃላትን ተጠቅመው ትችት ከሰነዘሩ በኃላ #በሕግ_ሊያስጠይቃቸው የሚችል ጉዳይ ይኖር እንደሆነ ተጠይቀው ነበር።

አቶ ታዬ ፤ " በሕግ መጠየቅ ምን ችግር አለው ፣ ነገር ግን ሕግ የታለና በሕግ ይጠይቁኛል። ከጠየቁኝ ደግሞ ዝግጁ ነኝ " የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

በሕግ ሊጠየቁ የሚችልበት እድልም እንደሌለ ተናግረው ነበር።

ዛሬ የፀጥታ እና የደህንነት የጋራ ግብረኃይል አቶ ታዬን ደንደአን በሕግ ቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሲሆን መኖሪያ ቤታቸው ላይም ብርበራ አድርጓል።

ግብረ ኃይሉ አቶ ታዬ ደንደአን ፦

- በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ሲፈፀሙ በነበሩ የሽብር ተግባራት በተለይም ደግሞ #ከእገታ ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት አሳውቋል።

(አቶ ታዬ ደንደአ በ #ሰላም_ሚኒስቴር ውስጥ ሆነው በተለያዩ ጊዜ በሚፈፀሙ የእግታ ጉዳዮች እጃቸው እንዳለበት የታወቀው መቼ ነው ? ከዚህ ቀደም ታውቆ ከሆነ ለምን እስከዛሬ ዝም ተባሉ ለሚለው ጉዳይ የተብራራ ነገር የለም)

- የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሰላምን ለማስፈን ከመስራት ይልቅ ከፀረሠላም ኃይሎች ጋር ተሳስረው ለጥፋት ተልዕኮ በህቡዕ ሲሰሩ ነበር ብሏቸዋል።

- መንግስት እና የፓርቲ መዋቅሩን በሴራ ለመናድ በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበር ብሏቸዋል።

- መንግሥት በሽብርተኝነት ከፈረጀው ከኦነግ ሸኔ አመራሮች እና በሽብር ወንጀል ከሚጠረጠሩ ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ትስስር ፈጥረው መንግስትን በአመፅ፣ በሽብርና በትጥቅ ለመጣል ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል ብሏል።

አቶ ታዬ ደንደአ ከሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን እና በራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡ የነበረ ሲሆን ትላንት ታሕሳስ 1 በኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተፃፈ ደብዳቤ ከስልጣን እንዲነሱ ተደርገዋል።

አቶ ታዬ ከስልጣን ለመነሳታቸው ምክንያቱ ጦርነት ተቃውመው ስለእርቅ ስለተናገሩ እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል። " በጦርነቱ ጊዜ ጦርነቱን ስደግፍ ሲያበረታቱኝ ነበር ሕዝቡ ይታረቅ ስንል ነው ያመማቸው " ያሉት አቶ ታዬ ሰላምን በመደገፌ ነው ከስልጣን የተነሳሁት ብለዋል።

ግብረ ኃይሉ ግን አቶ ታዬ ስልጣን ላይ ቁጭ ብለው እራሳቸው ያሉበትን #መንግስት እና #ፓርቲ ለመናድ መንግስትንም በሽብር ትጥቅ ለመጣል ከፀረሠላም ኃይሎች ጋር ሲሰሩ እንደደረሰባቸው አመልክቷል።

ልክ በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ሲያውቁ ደግሞ #ታጋይ ለመምሰል በየማህበራዊ ትስስር ገፆች ፀረ-ሰላም ፅሁፎችን እና ንግግሮችን ሲያስተላልፉ ነበር ብሏል።

@tikvahethiopia