TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል⬇️

በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት ከመደገፍና ከማሳደግ ውጪ ሌላ #አማራጭ እንደሌለ የደኢህዴን ሊቀ መንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል ገለፁ።

ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል 10ኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ድርጅታዊ ጉባዔ #መጠናቀቅን ተከትሎ ለጉባኤተኛው የማጠቃለያ መልእክት አስተላልፈዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪያት በማጠቃለያ ንግግራቸው፥ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በለውጥ ሂደት ላይ መሆኗን ገልፀው፤ የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና ጉባዔተኛው ለውጡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስራት አንዳለባቸው ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ ለውጥ #ለማደናቀፍ ሌት ተቀን የሚሰሩ ሀይሎች እንዳሉ ሊቀመንበሯ ገልፀዋል።

እነዚህ ሀይሎች 10ኛው የደኢህዴን ጉባዔ እንዳይሳካም ሲንቀሳቀሱ ነበር ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪያት፤ ከሀዋሳ ውጪ በህዝቦች መካከል #ግጭት ለመፍጠር ገንዘብ ተመድቦላቸው #ሲንቀሳቀሱ እንደነበረ ከክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በተሰራ ስራ ለማወቅ መቻሉን አንስተዋል።

የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና ጉባዔተኛው ይህንን በመገንዘብ እነዚህን የጥፋት ሀይሎች በንቃት መጠበቅና ማጋለጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የለውጥ ሂደት ከመደገፍና ካማሳደግ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም ያሉት ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት፥ ከዚህ ውጨ ያለው አማራጭ #የጥፋት አማራጭ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ስለዚህ የለውጥ ጉዞውን በማሳከት ሂደት የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና የጉባኤተኛው ሚና አጅግ የላቀ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ከነገ ጀምሮ #በሀዋሳ ከተማ የሚካሄደው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በማድረግ እንዲሁም የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ርብርብ መቀጠል ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።

በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የደኢህዴን ጉባዔተኞች ልክ በደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ያደረጉትን የነቃ ተሳትፎ፣ ዴሞክራሲያዊ ሂደትና ሰላማዊ ሁኔታን እንዲያስቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት አክለውም፥ 10ኛው የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ በዚህ መልኩ የተሳካ ሆኖ በመጠናቀቁም እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።

ጉባዔው የተሳካ እንዲሆን የሀዋሳ ከተማ እና የሲዳማ ዞን እንዲሁም የልግ ባለሀብቶች ላደረጉልት አቀባበል እንዲሁም የኢህአዴግ ጉባዔን ለማስተናገድ እያደረጉ ላለው ዝግጅት ለአመራሩ እና ለህዝቦች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወታደሮቹን በተመለከተ‼️

በቅርቡ የደመወዝ ጭማሬ ለመጠየቅ ወደ ቤተ መንግስት ስለመጡት ወታደሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለፓርላማው የተናገሩት ፡-

• የታጠቀ ወታደር ወደ ቤተ መንግስት የመጣው አገራዊ ለውጡን #ለማደናቀፍ ታስቦ የተደረገ ነበር፡፡

• ይሁን እንጂ ሁሉም የመጡት ይህን እሳቤ ይዘው ነው የመጡት ለማለት ያስቸግራል፡፡ በአንዳንድ #ተንኮለኞች ሴራ ተጠንስሶ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡

• በዕለቱ የተወሰደው እርምጃ በጥንቃቄ ባይሆን ኖሮ አገርን ወደቀውስ የሚከት ክስተት ነበር ፡፡

• አሁን ላይ ራሱ ወታደሩ በሴራው ውስጥ የነበሩትን የድርጊቱን መሪ እየለየ አሳልፎ እየሰጠ ነው፡፡

• በወቅቱ የወታደሮቹን አመጣጥ ወታደራዊ ጥበብ በሚጠይቀው መልኩ አረጋግቶ መመለስ መቻሉ አገርን የማትረፍ ወሳኝ እርምጃ አድርጌ ነው የምወስደው፡፡

• እየተዝናነሁ፣ እየሳቅኩ ቃለ መጠይቅ የሰጣሁት መንግስታችን ተነከ ብለው ከተለያዩ አቅጣጫዎች ህዝቡ ለመዋጋት እየመጠ ስለነበረ እነሱን ለማረጋጋት ነበር፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትውልድ አድን‼️

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት #ሠላማዊ የመማር ማስተማር ከባቢ ይፈጥራል ተብሎ የታመነበት “ትውልድ አድን” የተሰኘ የህይወት ክህሎት ሥልጠና መርሃ-ግብር ሊጀመር ነው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችም ሠላማዊ የመማር ማስተማር ከባቢ ለመፍጠር የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል።

የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም ዛሬ በዩኒቨርስቲዎች ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው  ይህንን የተናገሩት።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸውም ሠላማዊ የመማር ማስተማር ከባቢ ለመፍጠር የሚያስችል “ትውልድ አድን” የተሰኘ የህይወት ክህሎት ሥልጠና መርሃ-ግብር ሊጀመር መሆኑን በዚህ ወቅት ጠቁመዋል።

በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎችም መርሃ-ግብሩ በጅምር ላይ መሆኑን ጠቁመው በታዋቂ ግለሰቦች፣ በአርቲስቶችና በሥነ-ልቦና ባለሙያዎች የሚካሄድ ነው ብለዋል።

ሚኒስትሯ እንዳሉት አገሪቱ በአሁኑ ወቅት ሥር-ነቀል የለውጥ ሂደት ላይ በመሆኗ የተለያዩ ችግሮችን እያስተናገደች ነው።

በተለይም ሂደቱን #ለማደናቀፍ የሚሠሩ ኃይሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትኩረት ማድረጋቸውን ጠቁመው ይህ እንዲሆን የተፈለገው ተቋማቱ “ትንሿን ኢትዮጵያ” የመወከል አቅም ስላላቸው ነው ብለዋል።

ተማሪዎች ይህንን በመገንዘብ ችግሮችን ከወዲሁ መከላከል እንደሚገባ ገልጸው በዩኒቨርስቲዎች ሠላማዊ የመማር ማስተማር እንዲጠናከር መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia