TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram

የመግቢያ ነጥብ ዝቅ ተደረገ!

#ASTU #AASTU

የአዲስ አበበ እና አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲትዎች መግቢያ ነጥብ ዝቅ አለ!

የተማሪዎችን ፍላጎትና በተደጋጋሚ የሚነሳውን የመግቢያ ነጥብ ዝቅ ይበልልን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት የAPPLIED SCIENCE መግቢያ ሆኖ በማስታወቂያ የተገለጸው ለወንድ፡190 እና ለሴት፡185 ከነበረው ዝቅ ተደርጎ

ለወንድ፡ 176 እና
ለሴት፡166

የAPPLIED SCIENCE መግቢያ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን እያሳወቅን እስከ ነገ መስከረም 20/01/2012 ዓ.ም. ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዚህ መስክ መመደብ የምትፈልጉ የ2011ዓ.ም. የዪኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች፤ ለት/ቤታችሁ ፍላጎታችሁን በመግለጽ ምርጫችሁን ት/ቤታችሁ እንዲያስገባላችሁ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

https://app.neaea.gov.et/

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AAiT #NOKIA #AASTU

#NOKIA | ኖኪያ የ4G እና 5G የቴሌ ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ ለመዘርጋት መዘጋጀቱን ገለፀ። ኩባንያው ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር የዲጂታል ክህሎትንና የፈጠራ አቅምን ማጎልበት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

ፊርማውን የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ እና የአዲስ አበባ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩትን በመወከል ዶክተር ኢንጂነር ኢሳያስ ገብረዮሀንሰ እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅና ምዕራብ አፍሪካ የኖኪያ ተጠሪ ዳንኤል ጃገር ፈርመውታል።

ስምምነቱ ኩባንያው ለሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስክ አለም የደረሰበትን አሰራር እና የቴክኖሎጂ ገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የትምህርት እና ስልጠና ፕሮግራሞችንና የልምድ ልውውጦችን ማዘጋጀትን እንደሚያካትት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AASTU

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መመርመሪያ ላቦራቶሪ ሥራ ማስጀመሩን ኢቢሲ ዘግቧል።

በሁለት የመመርመሪያ ማሽኖች በተጀመረው የኮቪድ-19 ምርመራ እያንዳንዳቸው በአንዴ የዘጠኛ ስድስት (96) ሰዎች ውጤት የመስጠት አቅም እንዳላቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ASTU #AASTU

ሁለቱ የኢትዮጵያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስገባ ነጥብ ያዝመዘገቡ ተማሪዎችን ለመቀበል በዛሬው ዕለት ጥሪ አቅርበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ አውጥተዋል።

የመመዝገቢያ መስፈርቱ የሲቪክስ ትምህርትን ሳይጨምር የስድስት ትምህርት ድምር ውጤት ከዚህ በታች እንደተገለፀው ነው።

ለታዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤ/ጉሙዝ ፣ ጋምቤላ) ፦

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 395 ለሴት 390
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 385 ለሴት 380


ለሌሎች ክልሎች ፦

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 400 ለሴት 395
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 390 ለሴት 385


የምዝገባ ጊዜው ከየካቲት 21 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ሲሆን ምዝገባው የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል ተብሏል።

ከላይ የተቀመጠውን የምዝገባ መስፈርት የሚያሟሉ ተማሪዎች በማንኛውም ስፍራ ሆነው በኢንተርኔት www.aastu.edu.et እና www.astu.edu.et ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

ፈተናው መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚሰጥ ተነግሯል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#AASTU

የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች " ትምህርት ስለተጠናቀቀ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ እንደተባሉና ችግር ላይ መሆናቸውን" ገልጸውልናል።

በተለይ ከትግራይ ክልል የመጡ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ትራንስፖርት አለመኖሩ እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶችን በማንሳት መቸገራቸውን ያስረዳሉ።

በጉዳዩ ዙሪያ የጠየቅናቸው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አለምእሸት ገብረወልድ ተከታዩን ምላሽ ሰጠውናል።

"መደበኛ ነባር ተማሪዎች እስካሁን በግቢው ነው የሚገኙት። ማንም የወጣ ተማሪ የለም።"

"የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በጉዳዩ ዙሪያ እየመከሩ ነው። የትኞቹ ተማሪዎች ናቸው መቆየት ያለባቸው በሚለው ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እየተወያዩ ነው።"

"ዩኒቨርሲቲው የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች የትኞቹ ናቸው የሚለውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ውሳኔው እንደሚያሳውቅ" ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

More : @tikvahuniversity
#AASTU #ASTU

በ2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ ጥሪ ቀርቧል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በቀጥታ (online) በመስጠት ነው የሚቀበሉት።

የትምህርት መስኮቹ ምን ምን ናቸው ?

/ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ /

#ኢንጂነሪንግ ፦ አርክቴክቸር፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ፣ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ፣ ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ፣ ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ ፣ ኤሌክትሮ መካኒካል ኢንጂነሪንግ ፣ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ፣ ማይኒንግ ኢንጂነሪንግ ፣ ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ

#አፕላይድሳይንስ ፦ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ፣ ፉድ ሳይንስ፣ አፕላይድ ኒውትሪሽን ፣ ጂኦሎጂ፣ ባዮቴክኖሎጂ

/ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ /

#ኢንጂነሪንግ ፦ አርክቴክቸር፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ፣ ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ ፣ ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ፣  ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ፣ ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ ፣ ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ ኢንጂነሪንግ፣ ሶፍት ዌር ኢንጂነሪንግ

#አፕላይድሳይንስ ፦ አፕላይድ ቦዮሎጂ፣ አፕላይድ ኬሚስትሪ፣ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ፣ ፋርማሲ፣ አፕላይድ ፊዚክስ ፣ አፕላይስ ጂኦሎጂ፣ አፕላይድ ማቲማቲክስ

የምዝገባ ጊዜ፡- ከመስከረም 06 እስከ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሆነ ተገልጿል።

ምዝገባው የሚጠናቀቀው መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ላይ ነው።

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et / www.astu.edu.et ድረገጽን በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን በድህረ ገጽ የምዝገባው ቀን ካበቃ በኋላ ይደረጋል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ ፤ በምዝገባ ወቅት በመረጡት ዩኒቨርሲቲ (የፈተና ጣቢያ) በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

NB. ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ የማይጠየቅ ሲሆን የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ፍላጎቱ ያላቸው አመልካቾች ይህን አውቀው ቅድሚያ እንዲመዘገቡ ተብሏል።

@tikvahethiopia