TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ ዞን 4 ወረዳዎች ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ #የምግብ_እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ፡፡

በዞኑ በሎጂጋንፎ፣ ያሶ አጋሎ ሜጢና ካማሺ ወረዳ ለሚገኙት ተረጂዎች በፀጥታ ስጋት ምግብ ለማቅረብ አለመቻሉን ተሰምቷል፡፡

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ #ገርቢ_ሎላሳ ዛሬ ለሸገር ራድዮ ሲናገሩ ታጣቂዎች አሁንም መንገዱን #ስለዘጉት የእርዳታ እህል ለማቅረብ አዳጋች ሆኗል ብለዋል፡፡

ባሳለፍነው ቅዳሜ በመከላከያ ሰራዊት ታጅቦ የእርዳታ እህል ወደ ዞኑ ያደረሰ መኪና በመመለስ ላይ ሳለ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ 2 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቆስለዋል ብለዋል አቶ ገርቢ፡፡

መንግስት ታጣቂዎቹን በመከላከልና መንገዱን በማስከፈት በአፋጣኝ የእርዳታ እህል ማቅረብ እንዲችል የዞኑ አስተዳዳሪ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ‼️

#ግምታዊ_ዋጋቸው 300 ሺህ ብር የሆኑ #የምግብ_ዘይት እና የተለያዩ #የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ። ዛሬ የካቲት 08 ቀን 2011 ዓ ም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ የሰሌዳ ቁጥራቸው ኮድ 3- 37064 ኦሮ እና 02872 ሐረ የሆኑ ሚኒባስ እና አይሱዙ ጭነት ተሽከርካሪዎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን በመያዝ እና መነሻቸውን ከጅግጅጋ አቅጣጫ በማድረግ ወደ ሐረር ከተማ ሊገቡ ሲሉ ጅግጅጋ እና ሐረር መካከል ቦምባስ በምትገኝ ቦታ ላይ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በሚኒባስ ተሸከርካሪ ውስጥ በርካታ የምግብ ዘይት ሲያዙ በአይሱዙ የጭነት ተሸከርካሪ ውስጥ ደግሞ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ልባሽ ጨርቆች ተይዘዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹም ለጊዜው #እንዳመለጡ ታውቋል፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን የፈዴራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና የጉምሩክ ፈታሾች በጋራ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት ከገቢዎች ሚኒስቴር የተኘው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳሳቢ የምግብ እጥረት...#ኢትዮጵያ

በደቡብ ኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች አሳሳቢ #የምግብ_እጥረት እንዳለ ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን አሳሰበ። ቡድኑ በተለይ የጎሳ ግጭት አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ባፈናቀለበት በደቡብ ክልል በምግብ እጥረት ይበልጡን የተጠቁት ህጻናት መሆናቸውን ዐስታውቋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት በጌድኦ በምግብ እጥረት እጅግ የተጎዱ ከ200 የሚበልጡ ህጻናትን ማከሙን ቡድኑ ይፋ አድርጓል። የቡድኑ የመስክ ሥራ አስተባባሪ ማርኩስ ቦይኒንግን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ወላጆች ህጻናትን ወደ ክሊኒካቸው ይዘው የሚመጡት እጅግ ዘግይተው ነው። አንዳንዶቹም የሞት አፋፍ ላይ የሚገኙ ናቸው። ቶሎ ክሊኒኩ ባለመድረሳቸው ሕይወታቸው የሚያልፍ ህጻናት እንዳሉ ቡድኑ ተናግሯል። ሆኖም ቡድኑ የሞቱ ህጻናትን ቁጥር አልገለጸም። ጌድኦ የሚገኙት የተፈናቃዮች ማቆያ ሥፍራዎች ውስጥ የመጠለያ ኹኔታ፣ የውኃ አቅርቦት እና የንጽህና አጠባበቅ እጅግ አሳሳቢ መሆናቸውን ቦይኒንግ አስረድተዋል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አስቸኳይ የሳዑዲ አረቢያ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነና ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፎ ነበር። የሳዑዲ ፀጥታ ኃይሎች በሰሩት ኦፕሬሽን ተይዘው በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የውሃ የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች እጥረት እንዳጋጠማቸው ተሰምቷል።…
#Update #SaudiArabia

በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ ለሚገኙ ዜጎች የሚደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲቆም ተወሰነ።

ውሳኔው የተላለፈው ማህበረሰቡ ባለፉት ጥቂት ቀናት እጅግ በሚያኮራ መልኩ ፈጣን ድጋፍ በማድረግ በቂ የሆኑ ቁሳቁሶች በመለገዙ፤ ለግዜው እነዚህን ቁሳቁሶች በአግባቡ መጠቀም ስለሚያስፈልግ መሆኑን በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅህፈት ቤት አሳውቋል።

ነገር ግን እንደ አስፈላጊነቱ ቆንስላው በድጋሜ የቁሶች ድጋፍ ካስፈለገው ጥያቄውን ሊያቀርብ እንደሚችል ጠቁሟል።

በቀጣይ ቀናት በማቆያ ጣብያ ለሚገኙ ዜጎች #የምግብ አገልግሎት ሲያስፈልግ ከቁጥጥር ከደህንነትና ከተገቢ የስራ ዕቅድና አፈፃፀም አኳያ አመቺ እንዲሆን ከቆንስላ ጽ/ቤቱ እና ከኮሚኒቲው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ብቻ ድጋፉ እንዲቀርብ ጥሪ ቀርቧል።

የሳዑዲ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነና በዚህ ኦፕሬሽን ተይዘው በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ ለሚገኙ ዜጎች የውሃ የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች እጥረት በመከሰቱ ዕርዳታ ማድረግ የሚችሉ ካሉ እንዲያቀርቡ መጠየቁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ📈 የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል። የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምሥራቃዊ ዩክሬን ላይ “ወታደራዊ ዘመቻ” መጀመሩን መግለጻቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ቢቢሲ ዘግቧል። በዚህም ሳቢያ በ7 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል። ውጥረት እና ግጭቱ የሚቀጥል ከሆነ የነዳጅ ዋጋ ከዚህም በላይ…
የሩስያ እና ዩክሬን ፍጥጫ #እንደኛ ባሉ አዳጊ ሀገራት ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅእኖ ምንድነው ?

[በዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የቀረበ]

- #የምግብ_ዋጋ_መናር : ኢትዮጵያ ስንዴ የምትገዛባቸው ሶስት ዋና ዋና ሀገራት ሩስያ፣ ዩክሬን እና አውስትራሊያ ናቸው። በተለይ ሩስያ እና ዩክሬን በአለም ላይ ካለው የስንዴ ገበያ አንድ አራተኛውን ይሸፍናሉ። ዩክሬን 40 % የሚሆነውን የስንዴ ምርቷን ለመካከለኛው ምስራቅ እና እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አዳጊ ሀገራት በሽያጭ ታቀርባለች። ታድያ ይህ አቅርቦት በጦርነት ምክንያት ሲስተጓጎል የምርት/ምግብ አቅርቦት መስተጓጎሉ አይቀርም። ይህም በአንዳንድ ሀገራት የሚታየውን የዋጋ ግሽበት አባብሶ ህዝባዊ ቁጣ ሊቀሰቅስ ይችላል።

- #የነዳጅ_ዋጋ_መጨመር : የሩስያ እና ዩክሬንን ፍጥጫ ተከትሎ አሁን ላይ የነዳጅ ዋጋ ከ100 ዶላር በላይ እንዳሻቀበ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ፣ ይህ ዋጋ ከዚህም በላይ በፍጥነት ሊጨምር ይችላል የሚል ግምት አለ። ሩስያ በአለም ላይ የተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ በማምረት ከፍተኛውን ድርሻ ከሚይዙ ሀገራት መሀል ትመደባለች። ታድያ ይህ ግጭት የአለም የነዳጅ ዋጋን እጅጉን እያናረው ይገኛል፣ ይህም በተለይ እንደ ሀገራችን ላሉ ነዳጅ ገዢ ሀገራት እጅጉን ፈታኝ ግዜ እንደሚያመጣ ግልፅ እየሆነ ነው።

- #የእርዳታ_መቀነስ : ብዙ ግዜ እንደሚታየው አንድ ቦታ ላይ ትልቅ ችግር ሲከሰት ትኩረት ወደዛ ይዞራል። ለምሳሌ በሶርያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን ወዘተ ችግሮች ሲከሰቱ ከረጂ ሀገራት የሚገኘው ድጋፍ እዚህም፣ እዛም ይከፋፈል እና ይቀንሳል። አሁን ደግሞ ሀገራችን በጦርነት እና ድርቅ ምክንያት ከፍተኛ አለም አቀፍ ድጋፍ የምትሻበት ግዜ ነው፣ ነገር ግን ይህ እየተባባሰ የመጣ ፍጥጫ ትኩረት እንዳያሳጣን ስጋት አለ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
📩 ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የምግብ ዘይት ዋጋ ከሳምንታት በፊት ከነበረበት ምን አይነት ለውጥ እየተመለከታችሁ ነው ? አቅርቦቱስ እንደልብ አለ ? ከተማችሁን በመግለፅ በ @tikvahethiopiaBOT መልዕክታችሁን አስቀምጡልን። @tikvahethiopia
#TikvahFamily🍛

" በሚዲያው ላይ የሚነገረው እና በመሬት ላይ ያለው ሁኔታ አይገናኝም " - የቲክቫህ አባላት

ከዘይት ዋጋ ጋር በተያያዘ ከሳምንታት በፊት ከነበረው ምን የተቀየረ ነገር አለ ? አቅርቦትስ እንደልብ እየተገኘ ነው ? የሚል ጥያቄ ለቤተሰቦቻችን ቀርቦ ነበር።

በሁሉም አቅጣጫዎች የሚገኙ የቤተሰብ አባላቶች መልዕክታቸውን በመላክ ሁኔታው አስረድተዋል። ያለውን ችግር እና ምሬት ገልፀዋል፤ መፍትሄ ይፈለግ ዘንድም ጠይቀዋል።

በአንዳንድ ቦታዎች አቅርቦቶች ቢኖርም በዋጋው ላይ አንዳች ግን ለውጥ እንዳላዩ የገለፁት አባላቶቻችን በአንዳንድ ቦታ ደግሞ አቅርቦት ማነስ ምክንያት በሚባለው ዋጋ ለመግዛት እራሱ ማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀዋል።

በተለይ ከውጭ የሚገባው የፈሳሽ ዘይት ዋጋ አምስት ሊትሩ አሁንም ከ880 - 1000 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው ፤ እንዲህ ያሉ መለማመዶች ተገቢ እንዳልሆነ አንስተዋል።

ዋጋውን እንዲህ በየቀኑ እያለማመዱን በዚሁ ተሰቅሎ እንዳይቀር ያሰጋናልም ብለዋል።

መወደዱን የተቀበልን በድህነት ውስጥ ያለን ዜጎች መከራ ላይ ነን፤ ለመኖርም እየሰጋን ነው ሲሉ ያሉበትን የከፋ ሁኔታ አስረድተዋል።

የነዋሪው ገቢ አይጨምርም ዘይት ሆነ ሌላው ሁሌም ዋጋው እንደናረ ነው ፤ ዓለም አቀፍ ሁኔታው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለመረዳት ባያስቸግርም እዚሁ ሀገር ውስጥ ያለው የከፋ አሻጥር፣ ሙስና፣ የአስተዳደር ጉድለት ችግሩን እያባባሰው ነው ብለዋል።

ከተለያዩ ከተሞች በ @tikvahethiopiaBot የተላኩ መልዕክቶችን በጥቂቱ ከታች ያንብቧቸው።

(በተጨማሪ ቤተሰቦቻችን በብዙ ሺዎች የሚቆጠረውን የናተን አስተያየት በአንድ ለመሰብሰብ የሚከብድ ስለሆነ ከታች ባለው አስተያየት መስጫ ላይ ተጨማሪ ማስቀመጥ ትችላላችሁ)

NB. ውድ ቤተሰቦቻችን እንደሁል ጊዜው ማንኛውም የጥላቻ ንግግር ሆነ ሃሳብ፣ ስድብ፣ ሰውን ማንቋሸሽና ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ መልዕክት ማስፈር በቀጥታ እስከመጨረሻው ከቤተሰባችን ጋር እንደሚያለያይ ይታወቅ።

https://telegra.ph/Tikvah-Family-04-05
#Update

ኢንዶኔዥያ በሀገር ውስጥ #የምግብ_ዘይት አቅርቦት ላይ መሻሻሎች መታየቱን ተከትሎ እ.ኤ.አ. ከሰኞ ግንቦት 23 /2022 ጀምሮ የፓልም ዘይት ወደ ውጭ እንዳይላክ የተጣለው እገዳ እንደሚነሳ ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶ በዛሬው ዕለት ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#የWFP_ማጠንቀቂያ

የተመድ ዓለም ምግብ ፕሮግራም ለረሃብ የተጋለጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመመገብ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ካልተቻለ በሚቀጥሉት ከ12 እስከ 18 ወራት ውስጥ ዓለም፥ የጅምላ ስደትን፣ መረጋጋት የጎደላቸውን ሀገራት እና በረኀብ የተጠቁ ሕፃናትንና አዋቂዎችን ማየት እንደሚጀምር አስጠንቅቋል።

የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ዴቪድ ቤስሊ ባለፈው ዐርብ  ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር።

ቤስሊ ምን አሉ ?

- ለረሃብ የተጋለጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመመገብ #በቢሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ካልተቻለ በሚቀጥሉት ከ12 እስከ 18 ወራት ውስጥ ዓለም፥ የጅምላ ስደትን፣ መረጋጋት የጎደላቸውን ሀገራት እና በረሃብ የተጠቁ ሕፃናትንና አዋቂዎችን ማየት ይጀምራል።

- ባለፈው ዓመት፣ ከአሜሪካና ከጀርመን የተገኘውን ተጨማሪ ድጋፍ ይደነቃል ፤ ቻይና፣ የባሕረ ሠላጤው ሀገራት፣ ቢሊየነር ባዕለ ጸጋዎች እና ሌሎችም ሀገራት፣ ከምንጊዜውም በላይ አሁን ድጋፋቸውን ሊያፋጥኑ ይገባል።

- በ49 ሀገራት ውስጥ አስቸኳይ የሆነ #የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸውን 350 ሚሊዮን ሰዎች ለመርዳት 23 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ይህ ገንዘብ ላያገኝ ይችላል ፤ ይህ ደግሞ በከፍተኛ ኹኔታ አስጨንቆኛል።

- አሜሪካ የምትሰጠውን የገንዘብ ርዳታ ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር ወደ 7.4 ቢሊዮን አሳድጋለች፤ በተመሳሳይ ጀርመንም ከ350 ሚሊየን ዶላር ወደ 1.7 ቢሊዮን ከፍ አድርጋለች ፤ በዓለም ሁለተኛ ትልቁ የሆነውን ኢኮኖሚ የያዘችው ቻይና ባለፈው ዓመት ለተቋሙ የሰጠችው ገንዘብ 11 ሚሊየን ዶላር ብቻ በመሆኑ ድጋፏን ልታሳድግ ይገባል።

- #የነዳጅ_ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ከመጨመሩ ጋራ ተያይዞ የባሕረ ሠላጤው ሀገራት የበለጠ እገዛ ሊያደርጉ ይችላሉ። በተለይ ከምሥራቅ አፍሪካ፣ ከሰሐራ እና ከሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ጋራ ግንኙነት ያላቸው የሙስሊም ሀገራት የተሻለ አስተዋፅኦ ማድረግ ይችላሉ።

- ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው በአፍሪካ የሳሕል ክልል የሚገኙ ሀገራትና ምሥራቅ ሶማሊያ ፣ ሰሜናዊ ኬንያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣  #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ይገኙባቸዋል።

- የዓለም መሪዎች፣ ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋትን ሊያስከትሉ የሚችሉ የሰብአዊ ርዳታ ክፍተቶች ለአሉባቸው ሀገራት ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባል።

ዴቪድ ቤስሊ በዓለም ትልቁ ሰብአዊ ርዳታ ሰጪ በሆነው ተቋም የነበራቸውን ሥልጣን በመጪው ሳምንት ለአሜሪካ አምባሳደር ሲንዲ ማኬይን ያስረክባሉ።

#VOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ስጋት ፈጥሮብናል " - ኤምባሲዎቹ ሰሞነኛውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚገኙት ፦ - የካናዳ፣ - የፈረንሳይ፣ - የጀርመን፣ - የጣሊያን፣ - የጃፓን፣ - የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ኤምባሲዎች የጋራ አጭር መግለጫ አውጥተዋል። በዚህም ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ " #አወዛጋቢ " በሆኑት አካባቢዎች ከሰሞኑን የተፈጠረው ግጭት " ስጋት ፈጥሮብናል " ብለዋል። ሁሉም ወገኖች የታጣቂ…
#Raya #UNOCHA

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት 29,000 ሰዎች ከአላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው ፦
° በቆቦ / በሰሜን ወሎ
° ሰቆጣ / በዋግኽምራ በሚገኙ መጠለያዎች መጠለላቸውን ገልጿል።

23,000 ሰዎች ወደ ቆቦ ሰሜን ወሎ እንዲሁም 5,980 ሰዎች ወደ ሰቆጣ ዋግኽምራ ዞን ነው የተፈናቀሉት።

በአካባቢው ያለው ሁኔታ ሲታይ የተፈናቃዮች ቁጥር ከዚህ ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል።

ከተፈናቀሉት ዜጎች በዋነኝነት 70 በመቶዎቹ ህጻናትና ሴቶች ሲሆኑ ቀሩት ደግሞ አዛውንቶችና ታዳጊዎች ናቸው።

እንደ UN OCHA ሪፖርት ፦

🔘 ተፈናቃዮች ባሉበት ከበድ ያለ #የምግብ እና የውሃ እጥረት በመኖሩ አስቸኳይ የሆነ የህይወት አድን እርዳታ ያስፈልጋል።

🔘 ክፍት በሆኑ ቦታዎች ላይ የተጠለሉ ቤተሰቦች አስቸኳይ መጠለያ ያስፈልጋቸዋል።

ኦቻ ድጋፍ በሚያደርጉ #አጋር_አካላት የግብዓት እጥረት ምክንያት በጣም ተጋላጭ ለሆኑት የምግብ እና ውሃ ድጋፍ እየተደረገ ያለው መደበኛ ባልሆነ መንገድ በህብረተሰቡ ነው ብሏል።

ተጨማሪ ፦

🛑 እስከ ትላንት ድረስ በራያ አላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ አንዳንድ መጠነኛ #ግጭቶች መከሰታቸውን ቢቀጥልም በአላማጣ ፣ ቆቦ ፣ ወልዲያ ከተሞች የጸጥታ ሁኔታው ​የተረጋጋ ነው።

⭕️ በአላማጣ እና በቆቦ መካከል ያለው መንገድ ተከፍቶ የንግድ ትራንስፖርት የቀጠለ ሲሆን እንደ ባንኮች ያሉ የህዝብ አገልግሎቶች ቀስ በቀስ ቀጥለዋል።

@tikvahethiopia