" በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት እየተሰቃየን ነው " - ነዋሪዎች
በመተከል የተለያየ ወረዳ ያሉ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ካገኙ ከ2 አመት በላይ እንደሆናቸው ገለፁ።
በመተከል ዞን ቡለን፣ ድባጤ እና ወንበራ ወረዳዎች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት በቋሚነት ካገኙ ከ2 አመት በላይ እንደሆናቸው በመግለፅ በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በወንበራ ወረዳ የሚኖሩ የጤና ባለሙያ እንደነገሩን ከሆነ በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት ምክንያት የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እጅግ አዳጋች እንደሆነባቸው አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወንበራ ቡለን እና ድባጤ ወረዳ ያሉ የተለያዩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ነዋሪዎችን ያናገረ ሲሆን በቋሚነት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ካገኙ ከ2 አመት በላይ እንደሆናቸው አመልክተው በመሃል ለጥቂት ወራት አየተቆራረጠ መምጣቱን በመግለፅ በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ገልፀዋል።
በእነዚህ ወረዳዎች የሚገኙ ያናገርናቸው ነዋሪዎች ማታ ማታ ሻማ የሚጠቀሙ እንደሆነ ሲገልፁ የእሌክትሪክ አገልግሎት ማጣታቸው የህይወት እንቅስቃሴአቸውን እያከበደው እንደሚገኝ በማስረዳት ከሚዲያ እንዲርቁ እንዳደረጋቸውና ተንቀሳቃሽ ስልኮቻችውን 15 ብር ከፍለው ጀነሬተር ባለባቸው ቦታዎች ሃይል እያስሞሉ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
ጉዳዩን አስመልክተን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ ካሳሁን ከበደን ያናገርን ሲሆን አቶ ካሳሁን ከዳዝባጉና እስከ ዲባጤ ባለው 43 ኪ.ሜ ርቀት ቦታ የመስመር ጥገና እንደሚያስፈልግ ገልፀው የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው አካባቢዎች መጋቢ መስመር ይህ መሆኑን በማስረዳት አካባቢው ላይ ባለ የፀጥታ ችግር ምክንያት መስመሩን መጠገን እንዳልተቻለ አመልክተዋል።
አቶ ከበደ በተጠቀሱት ወረዳዎች የኤሌክትሪክ የአገልግሎት መቋረጡን ያረጋገጡ ሲሆን ፥ ቲክቫህ ለዋና ስራ አስፈፃሚው "ይሄ የኤሌክትሪክ መቋረጥ ችግር መች ይፈታል?" ብሎ ለጠየቃቸው ጥያቄ "እኛ አናውቅም" የሚል መልስ ሰጥተው በአካባቢው ለመንቀሳቀስ የፀጥታ አካላት ትብብርና እጀባ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኝት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዲስትሪቢውሽንና ሜንተናንስ ሀላፊ የሆኑትን አቶ የኔጌታን ያናገርን ሲሆን በአካባቢው ለ3 አመት የተቋረጠው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በጥር 2015 ዓ/ም ጀምሮ እንደነበር አስረድተው ከዛ በኋላ ስላለው አገልግሎት መቆራረጥ ተጨባጭና ትክክለኛ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል።
ኃላፊው ከወረዳው የየኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ ሃላፊዎች ጋር ተነጋግረው መረጃ እንደሚሰጡ ለቲክቫህ ቃል ቢገቡም ከዛ በኋላ እርሳቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
የመተከል ዞን መስተዳድር ከወረዳዎች ጋር በመተባበር አስፈላጊውን የፀጥታ ትብብርና ድጋፍ በማድረግ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚጀመርበት ሁኔታ እንዲመቻች የየወረዳው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
@tikvahethiopia

#አማራ
በአማራ ክልል፤ ሰሜን ጎንደር ዞን ፤ የተከሰተውን አስከፊ ድርቅ ተከትሎ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ የመሆን ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን የዞኑ አመራሮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የዞኑ አደጋ መከላከልንና ምግብ ዋስችና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰላምይሁን ሙላት በገለጹት መሠረት፣ " ድርቅ ባለባቸው አካባቢዎች ወደ 105 የትምህርት ተቋማት ወደ 51 ሺሕ ለሚሆኑ ተማሪዎች ምገባ ይሰጥ ነበር " ብለዋል።
" ነገር ግን ከወራት በፊት 202 ሺሕ ዜጎች የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብለው ተለይተው ነበር። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ድጋፍ ተደራሽ እየተደረገ ያለው ቅድሚያ ለሚያስፈልገው የማኅበረሰብ ክፍል ነው" ያሉት ኃላፊው፣ " ለተማሪዎች እገዛ ማድረግ ያስፈልጋል፣ ነገር ግን ድጋፍ ተጠናክሮ ካልቀጠለ ምግብ ካላገኙ ሊማሩ አይችሉም " ሲሉ አስረድተዋል።
አክለውም፣ " የትምህርት ተቋማት ችግር ላይ ነው ያሉት፣ ቁሳቁስ ያስፈልጋቸዋል። የጤና ተቋማት መድኃኒት ያስፈልጋቸዋል። እስከ 2017 የምርት ዘመን 452, 950 የሚሆኑ ዜጎች እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ለግብርናው ዘርፍም የማዳበሪያና የዘር ድጋፍ ያስፈልጋል " ብለዋል።
አቶ ሰላምይሁን ዞኑ ተደራራቢ ችግር እንዳለበት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ " በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ተፈናቅለው ከነበሩት ሰዎች መካከል ከ104 ሺሕ በላይ ዜጎችን ወደየቄያቸው መልስናል። ነገር ግን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከትግራይና ከኦሮሚያ ክልሎች የመጡ ከ41 ሺሕ በላይ፣ ከሱዳን የተመለሱ ከ4ሺሕ በላይ፣ ከ20ሺሕ በላይ የኤርትራ ተፈናቃዮች በዞኑ አሉ። እነዚህ ከድርቁ ጋ በተያያዘ ችግሩን ክብደት የሰጡት ጉዳዮች ናቸው " ነው ያሉት።
የሰሜን ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ክቡር አሰፋ በበኩላቸው፣ " በተለያዩ አካላት የተጀመሩ ድጋፎች አሉ፣ በዚህ ካልቀጠለ 51, 336 ተማሪዎች ትምህርት ያቋርጣሉ " ብለዋል።
" በሦስት ወረዳዎች ማለትም ጃንአሞራ፣ በየዳና ጠለምት አካባቢዎች አንደኛ ደረጃ ላይ ወደ 105፣ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሰባት ትምህርት ቤቶች፣ በአጠቃላይ ከ51 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ለድርቁ ተጋላጭ ናቸው " ሲሉ አብራርተዋል።
አክለውም፣ " ተማሪዎች በመጀመሪያ የመምጣት አዝማሚያ ነበራቸው፣ ድርቁ በጣም በባሰባቸው አካባቢዎች (ለምሳሌ ጃን አሞራ ወረዳ 13 ቀበሌዎች አሉ፣ ከእነዛ ውስጥ ወደ ሰባት ቀበሌዎች ላይ ድርቁ የከፋ ነው " ብለዋል።
ድጋፍ ካልተደረገ ተማሪዎች ወላጆቻቸው ጋር ይፈናቀላሉ የሚል ሥጋት እንዳለ የተናገሩት ኃላፊው፣ " ድርቅ ባለባቸው አካባቢዎች ያሉት ተማሪዎች እርግጠኛ ነኝ ትምህርት ቤት ይመጣሉ የሚል እምነት የለንም " ነው ያሉት።
በመሆኑም፣ መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም ድጋፍ አድራጊዎች ለወላጆች የኢኮኖሚ፣ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፋቸውን በመቀጠል ትምህርት እንዳይቋረጥ ከፍተኛ ሚና እንዲጫዎቱ ጠይቀዋል።
አቶ ሰላምይሁን በበኩላችሁ፣ ከ104 ሺሕ ሕጻናት መካከል በጠለምት 49 በመቶው የከፋ ችግር ላይ እንደሆኑ፣ ጃንአሞራ 33 በመቶ የሕመም ችግር እንዳለባቸው፣ የድጋፍ ችግር ያለባቸው እናቶች የምግብ ፍላጎት ወደ 30 በመቶ እየደረሰ መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም መንግሥት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሁሉም ሚዲያዎች በቦታው በመገኘት እንዲዘግቡ፣ ድጋፍም እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ዘገባው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

#ኮንታ
" እናትን ጨምሮ ሁለት ልጆች ህይወታቸውን አጥተዋል "
በመሬት መንሸራተት አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ በኦፓላሸ ቀበሌ በግምት በሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
የመሬት መምሸራረት አደጋው ሰሞኑን የጣለ ከባድ ዝናብ ተከትሎ እንደደረሰ የተነገረ ሲሆን በአደጋው እናትን ጨምሮ ሁለት ልጆች ህይወታቸውን አጥተዋል።
ሟቾች የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ተማሪ አግኔ አሉላ፣ ታናሽ ወንድሟና የ6ኛ ክፍል ተማሪ አማኑኤል አሉላ እና እናታቸው ወ/ሮ ዳምአሌ ደስታ ናቸው።
በደረሰው አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ በኦፓ ላሸ እና በኮዳ ማጂ ቀበሌ 25 አባዎራዎችና 175 የቤተሰብ አባላት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በቀበሌ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።
በአደጋው አምስት የቤት እንስሳት መሞታቸውንና በ5 ነጥብ 5 ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ ሰብል መውደሙም ተጠቁሟል
የዚህ መረጃ ባለቤት የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

#NBE
በቅርቡ በብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚሰት አቶ ፈቃዱ ደግፌ ተፈርሞ ለሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በተላከ ደብዳቤ አገልግሎቱ የወለድ ክፍያ ያለበትን የብድር ውል ማዋዋል እንደማይችል ተገልጿል።
" የወለድ ክፍያ ያለበትን ብድር ማበደር የሚችለውና ገንዘብ መሰብሰብ የሚችለው ባንክና ማይክሮ ፋይናንስ ብቻ በመሆኑ፣ ግለሰቦች ወለድ በማስከፈል ማበደር አይችሉም " ሲሉ አቶ ፈቃዱ ደግፌ አስረድተዋል፡፡
በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ግለሰቦች ወይም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ ያሉ የንግድ ድርጅቶች፣ በመካከላቸው የሚያደርጉትን የወለድ ክፍያ ያለበትን ብድር ማዋዋል እንደሚቻልና እንደማይቻል ብሔራዊ ባንክን ጠይቆ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በዚህም መሠረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ የባንክ ወይም የአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ፈቃድ ካልተያዘ በስተቀር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የባንክ ወይም አነስተኛ የፋይናንስ ሥራ መሥራት በሕግ የተከለከለ ተግባር ነው ሲል በደብዳቤው ተገልጿል፡፡
የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 እንደሚገልጸው፣ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ከሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ውጪ፣ ቁጠባ እንዲሰበስቡና ብድር እንዲሰጡ በልዩ ሕግ የተፈቀደላቸው የኅብረት ሥራ ማኅበራት ናቸው፡፡
ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ፈቃድ በተሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ሥራ በሕገወጥ መንገድ እንዲሰማሩና ሕገወጥ የፋይናንስ ሥርዓት ለመፍጠር የወጣ ሕግ አለመሆኑን፣ አገልግሎቱ ለብሔራዊ ባንክ የላከው ደብዳቤው ይገልጻል፡፡
ብሔራዊ ባንክም ከሕግ ድንጋጌዎች ውጭ በብድር መልክ ገንዘብ መሰብሰብና የብድር ተመን አውጥቶ በወለድ ማበደር፣ በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ሥራ ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በተመሳሳይ መንገድ ገንዘብ የሚያበድሩ ግለሰቦች በወንጀል የሚያስቀጣቸው ተግባር በመሆኑ፣ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ማንኛውም የወለድ ክፍያ ያለበት የብድር ውል ማዋዋል እንደሌለበት ብሔራዊ ባንክ ገልጿል፡፡
ከዚህ በፊት በወለድ ሲያበድሩ የነበሩ ግለሰቦች በምን ዓይነት መንገድ ሊጠየቁ እንደሚችሉ አቶ ፈቃዱ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡
የዚህ መረጃ ባለቤት " ሪፖርተር ጋዜጣ " ነው።

የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያዎን
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እና በሲቢኢ ብር
ባሉበት፣ በየትኛውም ሰዓት፣ በማንኛውም የስልክ አይነት መቾትዎ እንደተጠበቀ
በቀላሉ ይክፈሉ!
አሊያም በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የሲቢኢ ብር ወኪል ዘንድ በመሄድ መክፈል ይችላሉ፡፡
**********************
የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ካልሆኑ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉ ሲሆን፣ የሲቢኢ ብር አገልግሎት መጠቀም ካልጀመሩ ደግሞ
• ወደ *847# በመደወል፣ ወይም
• የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ተመዝግበው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ነጻ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ።
የሲቢኢ ብር መተግበሪን ለማውረድ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#መክሰስTime መሆኑን እንዴት እንውቃለን? የምንወደውን ስናይ እና ስንሰማ - ከ #ሰንቺፕስ ጋር #ሰኒሞመንትስ #መክሰስTime
When do you know that it is time? Time for #SnackTime - with #SUNChips and #SunnyMoments.
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
እልፍ ተስፋ የሰነቁ በጦርነት ወቅት የተደፈሩ ሰዎች (በኢዮብ ትኩዬ) https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-26
Telegraph
Tikvah Ethiopia
የፌስቱላ ሕሙማን ከጦርነት ማግስት (በኢዮብ ትኩዬ) በፌደራሉ መንግሥትና በሕወሓት ታጣቂዎች መካከል በተካሄደው ጦርነት ሳቢያ የሕክምና አገልግሎት ተቋርጦበት በነበረው ትግራይ ክልል የፊስቱላ ሕሙማን ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ሕክምና ማግኘት እንዳልቻሉ ኃላፊዎችና በበሽታው የተያዙ ሰዎች ገልጸዋል። በተለይም በታጣቂዎች የአስገድ መደፈር ጥቃት የደረሰባቸውና ሌሎች ኬዞች ያሉባቸው ሴቶች የሕክምና አገልግሎት…
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
🔹" ችግር ላይ ላለዉ መምህር ተገቢ ያልሆነ መልስ ነው የተሰጠን " - መምህራን
🔸 " ችግሩን ለመፍታት መግባባት ላይ ተደርሶ ወደስራ የሚያስገቡ እንቅስቃሴዎች አሉ ፤ ከሰኞ ጀምሮ ወደአካባቢዉ እናቀናለን " - የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ
በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሃዲያ ዞን የባዳዋቾ ወረዳና የሾኔ ከተማ ትምህርት ቤቶች አሁንም አለመከፈታቸዉ ተሰምቷል።
በባዳቾች ወረዳና ሾኔ ከተማ ያሉ የጤና ባለሙያዎችና መመህራን " ደመወዝ አልተከፈለንም " በሚል ለወራት የዘለቀ ተቃዉሞና የስራ ማቆም አድማ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ይሁንና ለጤና ባለሙያዎች የነሀሴ ወር ደሞዝ መከፈሉን ተከትሎ በተደረሰ ስምምነት ወደስራ ቢመለሱም መምህራን ጋር ስምምነት ላይ ባለመደረሱ ግን አሁንም ትምህርት አልተጀመረም።
ከሰሞኑ በዚህዉ ጉዳይ ወደክልሉ መቀመጫ ሆሳዕና ያቀናዉ የመምህራን ተወካዮች ቡድን ወይይት ለማድረግ አስቦ ቢጓዝም ሁኔታዎች ባሰቡበት ልክ መሄድ አለመቻሉም ተገልጿል።
ከዚህዉ ጋር በተያያዘ አስተያዬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት አቶ ደሳለኝ ከበደ መምህራኑን ወክለዉ ቡድኑን በመምራት ወደክልል አመራሮች መሄዳቸዉን በማንሳት የክልሉን ርእሰ መስተዳድርም ሆነ ተወካያቸዉን ማግኘት ካለመቻላቸዉ በላይ ከክልሉ ወንጀል መከላከልና አድማ ብተና ዉክቢያ እንደደረሳቸዉ በመግለጽ በመጨረሻ የክልሉ ብልጽግና ፖርቲ ጽህፈት ቤት ተቀብሎ እንዳነጋገራቸዉ ገልጸዋል።
ዉይይቱ ተስፋ ሰጭ አለመሆኑንና መንግስት ጥያቄዎቻቸዉን ከመመለስ ይልቅ " ደሞዛችሁ በቅርቡ ይከፈላል " ማለቱ ችግር ላይ ላለዉ መምህር ተገቢ ያልሆነ መልስ መሆኑን አንስተዋል።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያነሳንላቸዉ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ ዶክተር ኪባሞ ዲታሞ በበኩላቸዉ ችግሩን ለመፍታት መግባባት ላይ ተደርሶ ወደስራ የሚያስገቡ እንቅስቃሴዎች መኖራቸዉንና ከሰኞ ጀምሮ ወደአካባቢዉ እንደሚያቀኑ ገልጸዉ ለጊዜዉ ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
* ተጨማሪ ፦ አንድ የቤተሰባችን አባል የትምህርት ሥራ ቆሞ ያለው በባዳዋቾ ዙሪያ ወረዳ ብቻ ሳይሆን በሀዲያ ዞን በአብዘኛዎቹ ወረዳዎች ነው ብለዋል። ለምሳሌ:- ሶሮ ወረዳ፣ ጎምቦራ ወረዳ፣ ዱና ወረዳ፣ ግቤ ወረዳ እና ሚሻ ወረዳም የመስከራም ወር ደመወዝ ስላልተከፈላቸው አልተጀመረም ሲሉ ገልጸዋል።

#ትግራይ #ዓዲግራት
" ብርጌድ ንሓመዱ " የተባለው የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣቶች እንቅስቃሴ በትግራይ ኢትዮጵያ ተቋቋመ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ " ምምስራት ብርጌድ ንሓመዱ ጨንፈር ትግራይ መላእ ኢትዮጵያ " ማለትም ' የብርጌድ ንሓመዱ መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ምስረታ ' በሚል ርእስ በተለይ ኤርትራውያን በሚጠቀሙባቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲዘዋወር ያገኘው የጥሪ ደብዳቤ በመያዝ #ሃቀኝነቱን ለማረጋገጥ ጥረት አድርጓል።
በትግርኛ ቋንቋ የተፃፈውና በማህበራዊ ትስስር ገፆች የተሰራጨው ማህተምና ፊርማ የሌለው በመላ ኢትዮጵያ ለሚኖሩ ኤርትራውያን የተፃፈው ደብዳቤ ሙሉ ቃል እንዲህ ይላል።
"... ይፋዊ ምስረታ 'ብርጌድ ንሓመዱ ' መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ።
'ብርጌድ ንሓመዱ ' የተባለ የኤርትራውያን ህዝባዊ ማዕበል እንቅስቃሴ ለማጠናከር በምናካሂደው ህዝባዊ ስብሰባ እንድትሳተፉ በክብር ጥሪ እናቀርባለን።
የስብሰባ ቦታ ዓዲግራት ትግራይ !!
ሕጊ ይንገስ
ምልኪ ይፍረስ !!
ህግ ይንገስ
አምባገነንነት ይፍረስ "
የጥሪ ደብዳቤውን በመከተል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል እሁድ ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም ከመቐለ ወደ ዓዲግራት ተጓዘ ።
ስብሰባ ይካሄድበታል ወደ ተባለ ቦታ በመሄድ ከአስተባባሪዎች ተገናኘ። አስተባባሪዎቹ ለድህንነታቸው ሲባል ስማቸው ምስላቸውና በኤርትራ የየት አከባቢ ነዋሪዎች እንደነበሩ ለመጥቀስ ፍቃደኞች አይደሉም።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከአስተባባሪዎቹ በመሆን ስብሰባ ወደ ተጠራበት ሰፊ አዳራሽ ይደርሳል። በሰፊ አዳራሹ ቁጥራቸው አነስተኛ ተሰብሳቢዎች ተገኙ።
አስተባባሪዎቹ ለጥንቃቄ ሲባል ፎቶ ማንሳትም ሆነ ድምፅ መቅረፅ አይፈቀድም ባሉት መሰረት የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ሪፓርተር የተባለውን በመቀበል ሰብሰባውን ተከታትሏል።
ይኸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል እንደረጋገጠው 'ብርጌድ ንሓመዱ 'የተባለው የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣቶች እንቀስቃሴ ' ብርጌድ ንሓመዱ ጨንፈር ትግራይ መላእ ኢትዮጵያ ' ማለት የ 'ብርጌድ ንሓመዱ ' የመላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በይፋ በዓዲግራት ተቋቁመዋል። እንቅስቃሴው የሚያስተባብሩ አመራሮቹም መርጠዋል።
የእንቅስቃሴው አስተባባሪዎች እንዳሉት ፤ " ከ30 ዓመታት በላይ ያለ ህዝባዊ ምርጫ በአምባገነንነት ተቀምጠዋል " ያሉትን የኤርትራ መንግስት ለመጣል በመላ ዓለም በሚኖሩ ኤርትራውያን ወጣቶች እየተደረገ ያለው ትግል በመደገፍና በመቀላቀል ትግሉ በመላ ኢትዮጵያ በሚኖሩ ኤርትራውያን ተቀባይነት እንዲያገኝ አበክረው ይሰራሉ።
የ ' ብርጌድ ንሓመዱ መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ' በሚል የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣት ኤርትራውያን እንቅስቃሴ በይፋ የተመሰረተባት የትግራይዋ ዓዲግራት ከተማ ከኤርትራ ደንበር በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት ትገኛለች ሲል ቲክቫህ ኢትጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከዓዲግራት ዘግቧል።

#ሳፋሪኮም_ኢትዮጵያ
እስከነገ ድረስ ያልተገደበ የድምፅ ደቂቃ ቢኖሮት ለማን ይደውሉ ነበር?
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

#አሁን #ሲዳማ
የሲዳማ ክልል ም/ ቤት አስቸኳይ ጉባዔ በሀዋሳ እያካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው እያካሄደ ያለው።
ለአንድ ቀን ብቻ ይካሄዳል በተባለው በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ በሶሰት የተለያዩ አጃንዳዎች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።
- ለጉባኤው ሞሽን ቀርቦ ይጸድቃል።
- የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ለምክር ቤቱ አቅርበው ያፀድቃሉ።
- የምክር ቤቱ አባላት #የህግ_ከለላ ማንሳት ላይ ተወያይተው ውሳኔ ይሰጣሉ።
#ኢዜአ