#ለጥንቃቄ
ቴሌግራም ላይ ከተለያዩ ሰዎች አጭር ጹሑፍና ሊንክ እየተላከሎት ነው ?
ቴሌግራም ላይ ከተለያዩ ሰዎች ጹሑፍና ሊንክ ያለው መልዕክቶች እየተላኩ ነው። ብዙዎች ይህ ጉዳይ በተደጋጋሚ እየደረሳቸው እንደሆነና የጥንቃቄ መልዕክቱን እንድናስተላልፍ ጠይቀውናል።
በመልዕክት የሚላከው ሊንክ ምንድን ነው?
በመልዕክቱ አብሮ የሚደርሶት ሊንክ የቴሌግራም አካውንቶን ለመጥለፍ የተዘጋጀ ቴሌግራምን የሚመስል ድረ-ገጽ ነው። ሊንኩን ሲከፍቱት ስልክ ቁጥር አስገብተው ወደ ቴሌግራም እንዲገቡ ይጠይቆቃል።
ቁጥሮን አስገብተው የሚመጣው ሌላኛው ገጽ በቴሌግራሞት የተላከሎትን አጭር የማረጋገጫ ቁጥር እንዲያስገቡ የሚጠይቅ ነው።
የተላከሎትን የማረጋገጫ ቁጥር ካስገቡ የእርሶን ቴሌግራም በቀጥታ ይህን ወጥመድ ያዘጋጁ ሰዎችም መጠቀም ይጀምራሉ። በዚህም መልዕክቶችን ለሌሎች መላክና እርሶ እንደላኩት አድርገው ማቅረብ ይችላሉ።
ይህ ገጽ ልክ ቴሌግራምን እንዲመስል ተደርጎ የተሰራ ሲሆን የሚያስገቡት መረጃ ግን ወደ ቴሌግራም ሳይሆን ይህንን ወደ ሚቆጣጠሩት ሰዎች የሚላክ ነው። ይህ አይነቱ ማጭበርበር ማጥመድ (Phishing) በመባል ይታወቃል።
ምን ማድረግ እችላለሁ ?
ይህ ችግር ካጋጠሞት ቀጥታ ቴሌግራሞት ላይ Setting ላይ በመግባት #Device የሚለውን በመጫን የእርሶ አካውንት በምን በምን ስልኮች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ማየት ይችላሉ። በዚህም ከእርሶ ቁጥጥር ውጪ ያሉ ስልኮችን በሙሉ ማስወጣትና እርሶ የሚጠቀሙበትን ብቻ ማስቀረት ይችላሉ።
ሁለተኛው መንገድ ይህ ችግር ከተመፈጠሩ በፊት የሚያገለግል ሲሆን ሁለተኛ ዙር የደኅንነት ማረጋገጫ (Two-Step verification ) መጠቀም ድንገት ለእንደዚህ አይነት ችግሮች ብንጋለጥ ተጨማሪ የደኅንነት ማረጋገጫ ይሆነናል። (ስለዚህ ዝርዝር ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ)
Via👋 @TikvahethMagazine

Via
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
" አኲርፈው የተለዩትን በጠባይ ወደ እኛ እናምጣቸው ፤ እኛም ኲርፊያን ከሚያስከትል ድርጊት እንራቅ " - ቅዱስነታቸው የጥቅምት ወር 2016 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተከፈተ። ምልዓተ ጉባኤው የተከፈተው ፥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ነው። ቅዱስነታቸው…
#Update
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ባለፉት ቀናት የጥቅምት መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች እንዲሁም ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያኗ እና ለሀገራም ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ተገልጿል።
ከተላለፉት ውሳኔዎች መካከል ፦
- ስለ ሀገር ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸምና መላው ሕዝበ ክርስቲያንም በአንድነትን በሕብረት ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት የበረከቱና የሥርዓተ ጸሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
- በአዲስ እንዲደራጁ ተጠንተው የቀረቡትን የአህጉረ ስብከት ይደራጅልን ጥያቄዎችን በመመርመር ፡-
➤ የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣
➤ የሰሜን ጎጃም ዞን ሀገረ ስብከት
➤ የጎፋና ባስኬቶ ዞን ሀገረ ስብከት
➤ የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሀገረ ስብከት እራሳቸውን ችለው ሀገረ ስብከት ሆነው ተደራጅተው እንዲቀጥሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
- በ2016 ዓ.ም. የበጀት ዓመት በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ፣ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ደብረ ታቦር ከተማ ላይ ሁለት መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲቋቋሙ፣ በማዕከላዊ ጐንደር ሀገረ ስብከት ርእሰ ከተማ ውስጥ ለሚገኙት የምስክር ጉባኤ ቤቶች በኮሌጅ ደረጃ በጀት እንዲመደብላቸው እና በከንባታ ሐድያ ስልጤ ሀገረ ስብከት ሆሣዕና ከተማ ላይ አንድ የካህናት ማሠልጠኛ እንዲከፈት ጉባኤው ወስኗል፡፡
- ቤተ ክርስቲያኗ ከውስጥና ከውጭ እየደረሱባት ያሉት ከፍተኛ የሆኑ ፈተናዎችን ተቋቁማ ሕልውናዋን አስከብራ መቀጠል ትችል ዘንድ ፡-
👉 ውስጣዊ ችግሮቻችን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በጠበቀ በውይይት እንዲፈቱ፣
👉 ውጫዊ ችግሮችንና የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ በችግሮቹ ዙሪያ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመነጋገር ችግሮቹ እንዲፈቱ እና የቤተ ክርስቲያኗ መብትና ሕልውና ተጠብቆ እንዲቀጥል እንዲደረግ፣
👉 ለቤተክርስቲያን ሕልውና አደጋ የሆኑና ሊሆኑ የሚችሉ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎችን አስመልክቶ በአግባቡ ተጠንተውናበማስረጃ ተተንትነው ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
- ወጣቱ ትውልድ በእምነቱ ጸንቶና በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ በእውቀትና በሥነምግባር ይታነጽ ዘንድ በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር እና አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡
(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ባለፉት ቀናት የጥቅምት መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች እንዲሁም ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያኗ እና ለሀገራም ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ተገልጿል።…
#ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ ያሉ ችግሮች በውይይት እና በስምምነት እንዲፈቱ በድጋሚ ጥሪ አቀረበች።
ይህ ጥሪ የቀረበው ቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት 2016 ዓ/ም ጉባኤውን ካጠናቀቀ በኃላ ባወጣው መግለጫ ነው።
ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " ትላንት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት ከደረሰብን ሐዘን እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ሳንጽናና ዛሬም በሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ አካባቢዎች የተከሰቱት ጦርነቶች፣ ግጭቶችና አለመግባባቶች እያስከተሉት ያለው የንጹሐን የሰው ሕይወት መጥፍትና የንብረት ውድመት በእጅጉ አሳዝኖናል " ብሏል።
በመሆኑም ችግሩ በውይይትና በስምምነት እንዲፈታ የፌዴራልን የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም በግጭቱ ተሳትፎና ድርሻ ያላቸው በሁሉም አካባቢ የምሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ የበኩላቸው ሚና በመወጣት እናት አገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟና አንድነቷ ተጠብቆ ይቀጥል ዘንድ ከአደራ ጭምር በድጋሚ ጥሪውን አቅርቧል።
ከዚህ በተጨማሪ ስለ ሀገር ሰላም እና ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም ተወስኗል።

#አሁን #ሲዳማ የሲዳማ ክልል ም/ ቤት አስቸኳይ ጉባዔ በሀዋሳ እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው እያካሄደ ያለው። ለአንድ ቀን ብቻ ይካሄዳል በተባለው በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ በሶሰት የተለያዩ አጃንዳዎች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል። - ለጉባኤው ሞሽን ቀርቦ ይጸድቃል። - የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ለምክር ቤቱ አቅርበው…
#Update
ቀናት በፊት በቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስረኞች ማቆያ እንዲገቡ የተደረጉት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ።
የሲዳማ ክልል መንግስት ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ 3 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ማቶ ማሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል ያሏቸውን ፦
- ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ፣
- አቶ አበራ አሬራ
- አቶ ተሰማ ደንጉሼ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ማብራሪያ መሰረት ም/ ቤቱ ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ በህግ እንዲጠየቁ ውሳኔ አሳልፏል።
ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከቀናት በፊት ወደ ሀገር ሲገቡ ቦሌ ኤርፖርት ላይ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በሀዋሳ በሚገኝ የእስረኞች ማቆያ ውስጥ እንደሆኑ የክልሉ ፖሊስ ማሳወቁ አይዘነጋም።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በክልሉ አራት ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች እንዲቋቋሙ በቀረበለት ሞሽን ላይ ተወያይቶ አፅድቋል። የፍ/ቤቶቹ መቀመጫም በአለታወንዶ፣ በበንሳ፣ ይርጋለምና ሀዋሳ ከተሞች ላይ እንዲሆን ወስኗል።
ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ የቀረበለትን የተለያየ ሹመት አፅድቋል።
- አቶ ጎሳዬ ጎዳና የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ፣
- አቶ ወሰንየለህ ሰለሞን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ፣
- ወይዘሮ ሰላማዊት መኩሪያ የንግድ ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

#አማራ : ለወራት የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ዐውድ እና አሉታዊ የሰብአዊ መብቶች እንድምታው
" ተፋላሚ ኃይሎች ሲቪል ሰዎችንና ንብረቶችን፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን እና መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ከማድረግ ሊቆጠቡ፣ መንግሥት የማኅበራዊ አገልግሎቶች እዲቀጥሉ አስቻይ ሁኔታ ሊፈጥር ይገባል። "
በአማራ ክልል ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
መግለጫው በክልሉ በተለያዩ ጊዜ በድሮን / አየር ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ፣ በርካታ ሰዎች ግጭት ሽሽት አካባቢያቸውን ጥለው መሸሻቸውን፣ ከፍርድ ውጭ የሚፈፀመው ግድያ መቀጠሉን፣ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ግድያም መፈፀሙን ያስረዳል።

#አማራ : ለወራት የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ዐውድ እና አሉታዊ የሰብአዊ መብቶች እንድምታው " ተፋላሚ ኃይሎች ሲቪል ሰዎችንና ንብረቶችን፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን እና መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ከማድረግ ሊቆጠቡ፣ መንግሥት የማኅበራዊ አገልግሎቶች እዲቀጥሉ አስቻይ ሁኔታ ሊፈጥር ይገባል። " በአማራ ክልል ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል። መግለጫው በክልሉ በተለያዩ…
#አማራ
በአማራ ክልል ለወራት ከቀጠለው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ በርካቶች በድሮን ጥቃት መገደላቸው እና በክልሉ ከፍርድ ውጭ ግድያዎች መቀጠላቸውን ዛሬ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተላከልን መግለጫ መረዳት ችለናል።
ከኢሰመኮ በደረሰን መግለጫ ፤ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ የአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ የትጥቅ ግጭት ተካሂዶባቸዋል።
በተጨማሪም እነዚህ አካባቢዎችና ወረዳዎች በአንድ ወቅት ላይ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሌላ ወቅት ደግሞ በታጣቂው ቡድን (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚታወቀው) በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የትጥቅ ግጭቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በከባድ መሣሪያ እና አልፎ አልፎ በአየር / ድሮን ድብደባ ጭምር የታገዘ ነው።
በግጭቱ ዐውድ ውስጥ #የአየር /#ድሮን መሣሪያን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት የተነሳ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ፣ ሰዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል።
ለምሳሌ ፦
- በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በረኸት ወረዳ፣ ' መጥተህ ብላ ' ከተማ ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የአንድ ዓመት ከሰባት ወር ሕፃንን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች #ተገድለዋል፤ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
- በደብረ ማርቆስ ከተማ ጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ቢያንስ 8 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።
- በደንበጫ ከተማ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በከባድ መሣሪያ ድብደባ ምክንያት ሲቪል ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል።
ኮሚሽኑ እነዚህን መረጃዎች ያገኘው የአካባቢውን ነዋሪዎች እና የዓይን ምስክሮችን በማነጋገር ነው።
በአንዳንድ አካባቢዎች ጥቃትን አልያም ግጭትን በመሸሽ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ከቀያቸው ተፈናቅለው በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል።
በምንጃር ወረዳ ውስጥ የአውራ ጎዳና ጎጥ ነዋሪዎች ከመስከረም 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከቀያቸው ተፈናቀለው ቢያንስ 3ዐዐዐ የሚሆኑት አሞራ ቤቴ ቀበሌ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤትና ክፍት ሜዳ ላይ (በዛፍ ሥር) ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ ሌሎች ቁጥራቸው ያልታወቀ መተሃራና አዋሽን ጨምሮ ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዋል።
ለተፈናቃዮች የተወሰነ ድጋፍ በማኅበረሰቡና እና በአንድ ተራድዖ ድርጅት የተደረገ ቢሆንም፣ በቂ ባለመሆኑ በአሳሳቢ ሁኔታ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።
የነዋሪዎችን መፈናቀል ተከትሎ ሰብላቸው እንደወደመ፣ ንብረታቸው እንደተዘረፈ፣ የቤቶቻቸው ጣራያ እና በር እየተነቀለ እንደተወሰደ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ቤቶቻቸውን ከአጎራባች ክልል በመጡ ኃይሎች በኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ጭምር ማፍረስ እንደተጀመረ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግሥት ኃላፊዎች አስረድተዋል።
በመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት የሚፈጸሙ ከሕግ ውጪ የሆኑ ግድያዎች አሁንም መቀጠላቸውን ኢሰመኮ ተዓማኒ መረጃዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ ገልጿል።
ግጭቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ሲቪል ሰዎች ውስጥ ፦
- " ፋኖን ትደግፋላችሁ "
- " ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ "
- " መሣሪያ አምጡ "
- " የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ " በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ተዓማኒ መረጃዎች ተገኝተዋል።
እንደማሳያ ፦
▪️በባሕር ዳር ሰባታሚት አካባቢ መስከረም 29 እና 30 ቀን 2016 ዓ.ም. #ሦስት_ወንድማማቾችን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።
▪️በሰሜን ጎጃም ዞን፣ አዴት ከተማ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ፍልሰታ ደብረ ማሪያም የሚኖሩ 12 የአብነት ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።
▪️ በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ አማኑኤል ከተማ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢያንስ 8 ሲቪል ሰዎች በቤት ለቤት ፍተሻ እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።
▪️በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ፣ ግንደወይን ከተማ ሞጣ በር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም. አንድ በጥይት የቆሰለን ግለሰብ እናቱና እህቱ በባጃጅ አሳፍረው ወደ ሕክምና ተቋም በመውሰድ ላይ እያሉ፣ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ባጃጁን አስቁመው ሁሉንም ተሳፋሪዎች ካስወረዱ በኋላ " የቆሰለው እኛን ሲዋጋ ነው " በሚል ምክንያት የባጃጅ አሽከርካሪውን ጨምሮ አራቱን ሰዎች በጥይት እንደገደሏቸው ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አስረድተዋል።
በባሕር ዳር፣ በፍኖተሰላም፣ በጎንደር እና በወልድያ ከተሞች በትጥቅ ግጭቱ ቆስለው ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ የተወሰኑ ሲቪል ሰዎች እና የታጣቂ ቡድኑ አባላት በመሆን በመንግሥት የጸጥታ አካላት የተጠረጠሩ ሰዎች ሕክምናቸው እዲቋረጥ ተደርጎ #ወዳልታወቀ_ስፍራ ከተወሰዱ በኋላ ፣ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ወደ ሕክምና ተቋማቱ ሲመለሱ ቀሪዎቹ ያሉበት ሁኔታ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ማረጋገጥ አልተቻለም።
በሌላ በኩል በየደረጃው የሚገኙ ሲቪል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች፣ ግድያዎችና እገታዎች በታጠቁ ኃይሎች ተፈጽመዋል።
ለምሳሌ ፦
▫መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከባሕር ዳር ወደ ደብረ ታቦር ሲሄዱ ' አለምበር ከተማ ' አካባቢ በታጣቂዎች ተገድለዋል።
▫በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች እንዲያመልጡ ተደርጓል።
ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ፤ በተለይም ከመንግሥት ተቋማት ጭምር በሚደርሱት መረጃዎች መሠረት በግጭቱ ዐውድ የሚፈጸሙ የአስገድዶ መድፈር ድርጊቶች በጣም አሳሳቢ እና በአፋጣኝ ተገቢው ምርመራ ተደረጎ አርምጃ ሊወሰድበት የሚገባው ነው፡፡
የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት በተለያዩ የጤና ተቋማት መድረስ የቻሉትን ተጎጂዎች ቁጥር ብቻ መሠረት በማድረግ ከሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ መግለጫ እስከ ወጣበት ጊዜ ድረስ ቢያንስ #2ዐዐ_የአስገድዶ_መድፈር ተጎጂዎች በጤና ተቋማት ተመዝግበዋል፤ ከተጎጂዎች መካከልም የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሴቶች እና የጤና ባለሞያ ሴቶች ጭምር ይገኙበታል።
ከትጥቅ ግጭቱ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ፦
🔹ሲቪል ሰዎች እና የሲቪል የንግድ እና የመሠረተ ልማት ተቋማት ላይ ዝርፊያ ተፈፅሟል።
🔹የማሳ ላይ ሰብል ውድመት ጨምሮ በሲቪል ሰዎች፣ በሕዝብ እና በመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል።
🔹ሕፃናት ከትምህርት ውጪ ሆነዋል በአንዳንድ አካባቢዎች የትምህርት ተቋማት ለወታደራዊ አገልግሎት ውለዋል። ይህ ደግሞ አፋጣኝ ትኩረት የሚሻ ነው።
በክልሉ ውስጥ በተለየ ሁኔታ ከተፈቀደላቸው ተቋማት በስተቀር ይህ መግለጫ እስከ ወጣበት ጊዜ ድረስ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን፣ በተለይም በግጭት ላይ ባሉ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎትም ጨምሮ ተቋርጧል።
(ዛሬ ከ #ኢሰመኮ የተላከል ሙሉ መግለጫ በዚህ ታገኛላችሁ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/82609?single)

የፌስቱላ ሕሙማን ከጦርነት ማግስት (በኢዮብ ትኩዬ) https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-29-2
Telegraph
Tikvah-Ethiopia
ልጓም ያጣው የመደፈር ጥቃት በግጭት ቀጠናዎች (በኢዮብ ትኩዬ) የአስገድዶ መደፈር ጥቃቶች በይበልጥ የሚፈጸሙት የጸጥታ መደፍረስ በሚታይባቸው አካባቢዎች መሆኑን በየወቅቱ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጥቃቱ ከጦርነት ማግስት እንደቆመና እንዳልቆመ፣ በታጣቂዎች ተገደው የተደፈሩ ሰዎች ለመጋፈጥ የተገደዱትን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ጫናዎችን፣ በጦርነት፣ በግጭት ሳቢያ የጤና ተቋማት ላይ የደረሰው…