#እንድታውቁት
Computer Vision Syndrome(CVS)
- ለረጅም ሰዓት ኮምፒውተር ወይም ዲጂታል ስክሪን ላይ መመልከት (ጊዜ ማሳለፍ) ዓይናችን ላይ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ጫና ያሳድራል፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተለያዩ ችግሮች አብረው ይከሰታሉ፡፡
እነዚህ ችግሮች የሚከሰተቱትም ፦
▪️ሳያቋርጡ ለረጅም ሰዐት መጠቀም
▪️የክፍላችንና የስክሪናችን ብርሀን ሳይመጣጠን ሲቀር
▪️ስክሪናችን ከዓይናችን የተመጠነ ርቀት ላይ ሳይቀመጥ ሲቀር
▪️ልክ ያልሆነ አቀማመጥ
▪️ያልታከመ የዕይታ ችግር ካለ
ምልክቶቹ ፦
- ብዥ ማለት
- የዓይን መድረቅ፣የዓይን መቅላት
- ከዕይታ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የራስ ምታት(Eye strain)
- ዓይን መድከም (eye fatigue)
- የአንገትና ትከሻ ህመም
ምን እናድርግ ?
- ስክሪናችንን ከዓይናችን ቢያንስ ከ40-50cm(በክንድ ርቀት) ላይ ማስቀመጥ
- ክፍላችን በቂ ብርሃን እንዲኖረዉ ማድረግ
- የዕይታ ችግር ካለ ወደ ህክምና በመሄድ መታከም
- የአንገትና የትከሻን ህመም ለመከላከል አቀማመጣችንን ማስተካከል
- ከስክሪን ጨረር የሚከላከሉ መነፅሮችን እንደ(Blue cut, Anti-reflective coating) መነፅሮችን መጠቀም
- በየመሀሉ ዕረፍት መውሰድ (በየ20 ደቂቃው ዓይን ዘና እንዲል ለ20 ሰከንድ ያህል ከስክሪኑ ራቅ ወዳሉ ነገሮች መመልከት)
- ዓይን ማርገብገብ (እንባ በደንብ እንዲሰራጭና ዓይናችን ለብዙ ሰዐት ትኩረት ከማድረግ የተነሳ የሚመጣውን የዓይን ድርቀት ይከላከላል፡፡)
▫️በዚህ ጊዜ የአብዛኞቻችን ህይወት ከዲጂታል ስክሪን ጋር የተቆራኘ ነውና የዓይናችን ጤንነት ግድ ሊለን ይገባል።
#AmericanOptometricAssociation
@tikvahethiopia