TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶክተር አሚር አማን⬆️

"ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር #በመተባበር የድሮን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መሰረታዊ የሆኑ መድሃኒቶች፣ የክትባት መድሃኒትና ደምን ለማጓጓዝ በጋራ እየሰራን ሲሆን ዛሬ ሙከራ አድርገናል፡፡ ድሮንውኑ በማንኛውም የአየር ፀባይ የሚሰራ፣ እስከ 5ኪ.ግ ክብደት መሸከም የሚችል፣ በደርሶ መልስ 300 ኪ.ሜ መሸፈን የሚችልና እስከ 5000 ሜትር ከፍታ የሚነሳ ሲሆን ለዚህም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩርያን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መ/ቤት ስም አመሰግናሁ፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech🔝

TIKVAH-ETH ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር #በመተባበር እያደረገ የሚገኘው የStop Hate Speech እንቅስቃሴ ቀጥሎ በዛሬው ዕለት #የሁለተኛው_ቀን መድረክ ተካሂዷል። በዛሬው እለት ከዩኒቨርሲቲ አመራሮች መካለል አቶ #እሸቱ ተገኝተው መልዕክት አተላልፈዋል። አቶ እሸቱ እንደተናጋሩት ተማሪዎች ከየትኛውም አይነት #የጥላቻ_ንግግር እና አንደንዛዥ አስተሳሰቦች #ሊርቁ ይገባል ብለዋል። በተጨማሪ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን ላይክ እና ሼር ባለማድረግ ለሀገራቸው #ሰላም ዘብ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፤ ከዚህ ባለፈም ስለግቢያቸው #ሀሰተኛ መረጃ ሲሳራጭ #ሲመለከቱም እውነታውን መፃፍና እውነቱን ብቻ ማጋራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። አቶ እሸቱ ከወራት በፊት በግቢው በተሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ የተፈጠረውን ክስተት አንስተው ተማሪው እውነቱን በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራት ላሳየው ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።

•በዛሬው ምሽት ቆይታ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በአካል ተገናኝተው አጭር ቆይታ አድርገዋል፤ በርካታ ስራዎችን በቀጣይ ለመስራትም አጭር ውይይት ተደርጓል። እንዲሁም TIKVAH-ETH በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እንደ ማህበር የሚቋቋምበት መንገዶች ላይ በቀጣይ ሰፊ ውይይት ለማድረግ እቅድ ተይዟል።

ምሽቱ ልክ እንደትላንቱ #በትሩ_ላይፍ የኪነ ጥበብ ቡድን ታጅቦ አልፏል። #TrueLife

በነገው ዕለት የ3ኛውና የመጨረሻው ቀን መድረክ የሚኖር ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር #ታከለ ተገኝተው መልዕክት ያስተላልፋሉ።

በቀጣይ፦

አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

#StopHateSpeech
#TIKVAH_ETH

ፎቶ፦ @odansiif (ዱሬሳ-TIKVAH-ETH)

የሀሳቡ ደጋፊዎች፦ 0919 74 36 30

@tsegabwolde @tikvahethiopia