TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሻኪሶ ከተማ ሞቶ በሦስተኛው ቀን አስክሬኑ የተገኘው ወጣት ጉዳይ !

#ዋና_ነጥብ

- በሻኪሶ ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት ተወዳጅ ታምራት (ጆኒ) ከሞተ በሦስተኛው ቀን አስክሬኑ ተገኝቷል።

- በሟች ግድያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት ጓደኞቹ ፍርድ ቤት የዋስ መብት ፈቅዶላቸዋል።

- ወደ ስምንት የሚሆኑ የሟች ቤተሰቦች " ሁከት ፈጥራችኋል " ተብለው ከታሰሩ 10 ቀን ሞልቷቸዋል። ፍርድ ቤት ግን አልቀረቡም።

#ዝርዝር_ጉዳይ

በጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ የባጃጅ ሹፌር የሆነው ወጣት ተወዳጅ ታምራት (ጆኒ) ሚያዚያ 29 በአንድ ሰርግ ላይ ተገኝቶ ምሽት ላይ ከታየ በኋላ ሊገኝ አልቻለም።

ጓደኞቹ ጋር ይሆናል ተብሎ ቢታሰብም በ2ኛው ቀን ግን ከጓደኞቹ " ጆኒን አይታችሁታል " የሚል ጥያቄ ለወንድሞቹ ቀረበ።

በዚህ ጊዜ ታናሽ ወንድሙ ወደሚያድርበት ቤት ሄዶ የጆኒ ክፍል የተባለውን ቤት ከአንድ ጓደኛው ጋር ሰብሮ ይገባሉ። ጠፋ የተባለው ወንድሙም በአልጋው ላይ ህይወቱ አልፎ ያገኘዋል። በወቅቱ ፖሊስ ደርሶ አስክሬኑን ለምርመራ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ይልካል።

ፖሊስ ለሆስፒታሉ በጻፈው ደብዳቤ ሟች በሰው እጅ በመደብደቡ ከሞተ በኋላ ቤት ውስጥ በማስገባት ከተደበቀ በጥቆማ አስክሬኑ ተገኝቷል ሲል ድብደባ መፈጸሙን ይገልጻል።

የዓይን እማኞችም አስክሬኑ ላይ የምት እንዲሁም በቤቱ የደም ምልክት መመልከታቸውን ጉዳዩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያስረዱት ቤተሰባችን ጠቁመዋል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ለፖሊስ በጻፈው የውጤት ሪፖርት አስክሬኑ ለምርመራ የቀረበው በከፍተኛ ደረጃ በመስበስ ላይ እንዳለ መሆኑን ይጠቅሳል። በአስክሬኑ ላይ ተለይቶ የሚታይ ጉዳት የለም ያለው ሪፖርቱ " የደረሰ ውስጣዊ ጉዳትም የለም " ሲልም አካቷል።

አክሎም የልብ የደም መጋቢ ቧንቧ ወደ ወስጣዊ የልብ ክፍል ሰርገው መግባታቸው የሞት መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሞ፤  " ከአስክሬን የምርመራ ውጤት በመነሳት የሞቱን መንስኤ መወሰን አልቻልንም፤ ስለሆነም መርማሪ ፖሊስ አደጋ የተከሰተበት የምርመራ ውጤት ከሁኔታው ጋር ተያያዥነት ያላቸው ማስረጃዎችን እና ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎችን በመጠቀም ድምዳሜ ላይ እንዲደርስ ምክራዊ ሀሳባችንን እንገልጸለን " ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በግድያ ወንጀል የተጠረጠሩት ሁለት ጓደኞቹ እና የአንደኛው ተጠርጣሪ ልጅ እናት እና አባት በጊዜው በቁጥጥር ሥር ቢውሉም የዋስ መብታቸው በፍርድ ቤት መፈቀዱን የሰሙት የሟች ቤተሰብ " ይህ እንዴት ይሆናል " ብለው ለመጠየቅ በሄዱበት ለድብደባ እና ለእስር መዳረጋቸውን ሁኔታውን ካስረዱን ቤተሰባችን እንዲሁም ከተላኩልን የምስል ማስረጃዎች መመልከት ችለናል።

የሟች ወላጅ እናት እና አባት፤ 2 ታላላቅ ወንድሞቹ እንዲሁም የሟች አጎት ጨምሮ ወደ 8 ሰዎች " ሁከት በመፍጠር እና እስረኛ ለማስመለጥ " ተጠርጥራችኋል ተብለው ከታሰሩ ዛሬ 10ኛ ቀናቸው መሆኑን ሰምተናል። የሟች ቤተሰቦች እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡም ሰምተናል።

በሟች ግድያ የተጠረጠሩት ጓደኞቹና የአንደኛው ተጠርጣሪ ልጅ እናት እና አባት በእስር ላይ ይገኛሉ።

ጉዳዩን በሚመለከት ከአከባቢው ፖሊስ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

በጉዳዩ ላይ ፖሊስ የሚሰጠው ማብራሪያ ካለ የምናቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia