TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ።

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ዛሬ በሰሜን ሸዋ " መሀል ሜዳ " ላይ በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።

የአቶ ግርማን ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል። " ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ የግድያውን ሁኔታ በተመለከተ #ዝርዝር_መረጃ ባይሰጡም " ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው " ሲሉ ገልጸውታል።

" ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው። " ሲሉ አክለዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia