TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ታምሩ ገምበታን ጨምሮ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች መታሰራቸው ተሰምቷል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ታምሩ ገምበታን ጨምሮ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰሞኑን መሆኑንና አቶ ታምሩ ገምበታ ግን ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. መሆኑ ተገልጿል።…
#Update

42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለፀ።

እንዚህ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት ፦
- ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣
- ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ
- ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተውጣጣ ግብረ-ኃይል ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ከቆየ በኃላ ነው ተብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ ፤ ተገልጋዮች በመደበኛ የመንግሥት ስርዓት የሚፈልጉትን የፓስፖርትና መሰል አገልግሎቶችን በአፋጣኝና በአነስተኛ ዋጋ ማግኘት ሲችሉ የፈጠሯቸው የተንዛዙና እና የተወሳሰቡ አሠራሮች ዜጎችን ለከፋ እንግልት ዳርገዋል ተብሏል። በተጨማሪ ላልተገባ ወጪ እንደዳረጉ ተመላክቷል።

ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቅ በሙስና ተግባር ተሰማርተው የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ ነበር ተብሏል።

የተሰጣቸውን ስልጣንና ኃላፊነት በመተው  ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ፦

- በዜግነት ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣

- በወንጀል ተከሰው የጉዞ ሰነዳቸው ለታገደባቸውና ሐሰተኛ የማንነት መገለጫ ላላቸው ሕገወጦች ጭምር የፓስፖርት፣ ሊሴፓሴና ቪዛ አየር በአየር በመሸጥና በማስተላለፍ መንገደኞች በሌሉበት ጉዞ እንዳላቸው በማስመሰል እንዲሁም የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ተለያዩ ሀገራት እንደተዘዋወሩ የሚገለፅ ማሕተም በማዘጋጀት ተግባር ተሰማርተው መገኘታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ተመልምለው ያለፉ እንደሆኑ በማስመሰል ግለሰቦች ባልተገባ መንገድ ለሥራ ወደ ተለያዩ የዓረብ ሀገራት እንዲወጡ በማድረግ እንዲሁም የሕጋዊ ግለሰብን ፓስፖርት ፎቶግራፍ በመቀየር ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽሙ ተደርሶባቸዋል ተብሏል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች የጥቅም ትስስር  በመዘርጋት ሙስና  ሲፈጽሙ እንደቆዩ ተገልጿል።

ሐሰተኛ የማንነት መታወቂያዎችን በማዘጋጀትም ተግባር ላይ ተሰማርተው ከነበሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ጋርም ግንኙነት በመፍጠር የወንጀል ተግባር ሲፈፅሙ ቆይተዋል ተብሏል።

ይህን ተከትሎም በተደረገ ክትትል ከ200 በላይ የሚሆኑ በሕገወጥ መንገድ የተዘጋጁ #ፓስፖርቶች እንዲመክኑ መደረጉና የወንጀል ድርጊቱም መንግሥትን በሚሊየን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ እንዳሳጣው ተገልጿል።

በዚህም ፦
- በአዲስ አበባ ከተማ፣
- ኦሮሚያ፣
- አማራ፣
- ሲዳማ፣
- ሶማሌ፣
- ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በወንጀሉ የተሳተፉ  በኢሚግሬሽንና ዜግነት  አገልግሎት ሲያገለግሉ የነበሩ ከከፍተኛ አመራርነት እስከ ባለሙያ ያሉ 42 ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

በወንጀል ድርጊቱ ተሰማርተው ከተገኙና በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል ፦

- የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ አዋልሶ
- ዘመድኩን ጌታቸው፣
- ከድር ሰዒድ ስሩር፣
- አስቻለው እዘዘው፣
- አብዱላሂ አሊ መሀመድ (አብዱላሂ ጃርሶ)፣
- ቴዎድሮስ ቦጋለ፣
- ጌትነት አየለ፣
-  ጀማል ገዳ፣
- ሙላት ደስታ፣
- ጅላሎ በድሩ፣
- ገነት ኃ/ማርያም፣
- ደገፋ ቤኩማ ፣
- ወንድይፍራው ሽመልስ ገ/ሰንበት እና ሌሎችም ይገኙበታል።

በተያዙት ተጠርጣሪዎች ዙሪያ ምርመራ ይቀጥላል የተባለ ሲሆን  በግለሰቦቹ ዙሪያ ተጨማሪ  መረጃ ያላቸው ዜጎች ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ #ጥቆማ_መስጠት ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia