TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Raya እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ሪፖርት መሰረት ከራያ አላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ በልጧል። 42 ሺህ ዜጎች ቆቦ ፤ 8,300 ሰዎች ሰቆጣ ይገኛሉ። የተፈናቀሉት ከራያ አላማጣ፣ ዛታ፣ ኦፍላ ነው። አብዛኞቹ ህጻናት ፣ ሴቶች ፣ ወጣቶች እና በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ናቸው። #UNOCHA @tikvahethiopia
🔈 #የተፈናቃዮችድምጽ

ሚያዚያ ወር በተቀሰቀሰው ግጭት ከኮረም፣ ኦፍላ፣ ዛታ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ዞን ይገኛሉ።

እነዚህ ወገኖች ላለፉት ሶስት ወራት ያለ በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ በመቆየታቸው የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

አጠቃላይ ተፈናቃዮች ከ22 ሺህ ይልቃሉ።

ተፈናቃዮች ምን አሉ ?

- አሳሳቢ የምግብ እና የመጠለያ ችግር አለ።
- እያንዳንዱ በሰው ቤት ተጠግቶ ነው ያለው።
- ቤተዘመድ እያገዛቸው እንጂ ለ3 ወር የከፋ ችግር ላይ ወድቀው ነው የሚገኙት።
- በ3 ወር ምንም የተደረገ ድጋፍ የለም።
- ዋግኽምራ ዞን የተቻለውን ቢያደርግም ከአቅሙ በላይ ነው። ብዙ ሰው ነው ያለው።
- አብዛኛው በረዳ ወቅዷል።
- ዘመድ ያለውም ዘመዱ ጋር ተቸግሮ ነው የሚኖረው።
- እየለመ የሚበላ አለ፣ ጉልበት ያለውም ተቀጥሮ የሚሰራ አለ።
- አንዳንድ እናቶች መጠለያ ተሰጥቷቸው ነበር ግን ልጆቻቸው ሲታመሙ ቤት ተከራይተው ወጥትተዋል። በዚህ ኑሮ ውድነት መኖር አልቻሉም።
- ተፈናቃዮቹ በቄያቸው ቤት እና ስራ ነበራቸው።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ምን አለ ?

° ከ11 ሺህ ተፈናቃዮች ነው ያሉት።
° አሁን ባለንበት ሁኔታ መጠለያ ማዘጋጀት አንችልም። ድንኳንም የለንም።
° የምንመግበውን ተቸግረን በመጡ ጊዜ ለአንድ ሰው 25 ኪ/ግ ነው  የሰጠነው። ከመጠባበቂያ !
° የሰላሙ ሁኔታ አለ፣ መንገድ ዝግትግት ያለ ነው ሌላ አካል ድጋፍ ላምጣ ቢል እንኳን።
° አካባቢው ዝናብ አጠር ነው። በድርቅ ይጠቃል። የዓምናው ድርቅም ጉዳቱ እንዳለ ነው። ብዙ ሰው ተጎድቷል። አሁን ተፈናቃይ ተጨምሮ ይቅርና በፊትም ብዙ ችግር አለ።
° በህጻናት አድን ድርጅት ካሽ 14 ሺህ በሁለት ዙር ለመስጠት ልየታ እየተደረገ ነው።
° ያሉት ተፈናቃዮች ከኦሮሚያ፣ ከመተማ፣ በሰሜን ጦርነትም ተፈናቅለው ያልሄዱ አሉ።

በአሁኑ ወቅት እርሳቸውም ተፈናቃይ መሆናቸውን የገለጹትና ኮረም ከተማን ለሁለት ዓመት በከንቲባነት የመሩት አቶ ብርሃኑ ኀይሉ፣  የተፈናቀለው ሕዝብ ብዛት ከ22 ሺሕ እንደሚበልጥ ገልጸው ፥ የምግብ አቅርቦቱ እጥረት አሳሳቢ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

" እርዳታ ጠይቀናል። ለ3 ወራት ተከታታይ እርዳታ የለም።  ክልሉ የሰጠን ነገር የለም፤ ጭራሽ አላነገረንም " ብለዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን " መረጃ አለን ፤ ለተፈናቃዮቹ የምግብ አቅርቦት ጥያቄ በቅርቡ ምላሽ ይሰጣል ፤ እርዳታም ይጓጓዛልም " ሲል ገልጸዋል። #ቪኦኤ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM