TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ባህርዳር #ጎንደር

ባህር ዳር ከተማ ከትላንት ለሊት ጀምሮ ዝምታ ሰፍኖባት እንደምትገኝና ዛሬ የሟቾች ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም እንደነበር ነዋሪዎቿ ተናግሩ።

ባለፉት ቀናት በከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ስትናጥ የነበረችው ባህር ዳር ከተማ ከለሊት ጀምሮ ፀጥ ብላ መዋሏን ነዋሪዎች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ በባህር ዳር በግጭቱ የሞቱ ሰዎች ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም መዋሉን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።

ትላንት በቀበሌ 13 ፣ 14 እና 16 በነበረ ውጊያ በርካታ ሰዎች #መሞታቸው እና #መጎዳታቸው ተነግሯል። እነዚሁ ሟቾች ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ በተለያዩ ስፍራዎች ሲፈፀም ውሏል።

ነዋሪዎቹ በጦርነቱ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈው አብዛኞቹ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች መሆናቸውን ገልጽዋል።

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) ያነጋገራቸው ሁለት ዶክተሮች በውጊያው ሰላማዊ ሰዎች ስለመገደላቸው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ የባህር ዳር ነዋሪዎች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ሬድዮ በሰጡት ቃል ከከተማው ማረሚያ ቤት 2 ሺህ የሚጠጉ ታራሚዎች ሲወጡ መመልከታቸውን ጠቁመዋል።

በጎንደር ዳግሞ ዛሬ ከሰሞኑን የተሻለ መረጋጋት እንዳለ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የመንግሥት ጦር በከተማው ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የተደረደሩ ድንጋዮችን ሲያነሱ መዋላቸውን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia