TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EthiopianAirlines #EthioTelecom

" የትም መሄድ ሳይጠበቅባችሁ እና ሳትንገላቱ የበረራ ትኬታችሁን በቴሌ ብር መግዛት ትችላላችሁ " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ / ኢትዮ ቴሌኮም

ከዚህ በኃላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች የበረራ ትኬታቸውን በ 'ቴሌ ብር ' አማካኝነት መግዛት ይችላሉ ተብሏል።

ዛሬ ኢትዮ-ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋር ሊሰሩ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን የአየር መንገዱ ደምበኞች የበረራ ትኬት ክፍያ በቴሌ ብር አማካኝነት መፈፀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

የተደረገው ስምምነት የአየር መንገዱ ደንበኞች የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው እና ሳይንገላቱ ባሉበት ሆነው በሞባይል ስልካቸው አማካኝነት ትኬት መግዛት እና ክፍያ ለመፈፀም እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፥ ለሀገር ውስጥ ሆነ ለውጭ ሀገር በረራ እስከ 30 ሺህ ብር የሚያወጡ የአየር መንገዱን ትኬቶች የትም መሄድ ሳያስፈልግ ካሉበት ሆኖ መግዛት ይቻላል ብሏል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን ገለፀ።

ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ ነው የተካሄደው።

ትላንህ ጉባኤው በማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኪያ ለማ፣ በአየርመንገዱ የሰዉ ሀብት ም ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘነበወርቅ ገ/ጻድቅ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የማህበሩ የስራና የኦዲት ሪፓርቶች፣ የማህበሩ የ2022/2023 በጀትና እቅድ ውይይትና ማጽደቅ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።

የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው ውሎ ከድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውና ከፍተኛ የማኔጅሜንት አባላት ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከሰራተኞች በተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ምላሽ ተሰቶባቸዋል።

ጠቅላላ ጉባኤው ለተለያዩ የሰራተኛ ተወካዮች ፣ የተመሰገኑ የስራ መሪዎችን የምስጋና የምስክር ወረቀት የሰጠ ሲሆን ፤ የአየርመንገዱ ሰራተኞች የማህበሩን ፕሬዝዳንት ኢ/ር ተሊላ ዴሬሳን በማህበሩ ላስመዘገቡት ለውጥ ከፍተኛ ሽልማት እንዲሁም የአየር መንገዱን ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክቷል።

በሌላ በኩል ጉባኤው ታግዷል ፣ አልተካሄደም በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩት መረጃዎች ውሸትና አሉባልታ ናቸው ያለው ማህበሩ ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ ነው የተጠናቀቀው ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ሀዋሳ #ድሬዳዋ #ባህርዳር

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የማለዳ በረራ ጀመረ።

አየር መንገዱ ከሀዋሳ ፣ ከድሬዳዋ እና ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ማለዳ 1:00 የሚነሱ እለታዊ በረራዎች መጀመሩን አሳውቋል።

#EthiopianAirlines

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

በአፍሪካ ግዙፉና በደህንነቱ አስተማማኝ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽልማት ተበረከተለት።

አየር መንገዱ " Global Travel Magazine " ከመንገደኞች ባሰባሰበው ድምፅ መሰረት " የ2022 ዓ.ም ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ " ሽልማትን ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ " SKYTRAX 2022 " የዓለም አየር መንገድ ሽልማት ላይ በ4 ዘርፎች ተሸለመ።

አየር መንገዱ 11 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም ምርጥ 100 አየር መንገዶች 26ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ተገልጿል። ደረጃው በዓለም ዙሪያ ባሉ የአየር መንገድ ደንበኞች በተሰጠ ድምጽ ነው።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሸለማቸው ሽልማቶች የትኞቹ ናቸው ?

🇪🇹 የ2022 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ ለ5 ተከታታይ ዓመታት ፤

🇪🇹  የ2022 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ደረጃ አየር መንገድ፣ ለ4 ተከታታይ ዓመታት

🇪🇹 የ2022 የአፍሪካ ምርጥ ኢኮኖሚ ክላስ ደረጃ ፤ ለ4 ተከታታይ ዓመታት

🇪🇹 በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ ምግብ አቅራቢነትን ሽልማት አሸንፏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ካፒታሉን ወደ 300 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ማቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

አየር መንገዱ አሁን ያለውን 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ለማሳደግ ያቀረበው ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ቦርድ ቀርቦ እየታየ ሲሆን ቦርዱ ተወያይቶ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ " አሁን ያለንን 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማሳደግ የፈለግንበት ምክንያት፣ ወሮታችን ከፍ እያለ በመምጣቱ ሲሆን፣ በቅርቡ ያፀድቁልናል ብለን እናስባለን " ሲሉ ተናግረዋል።

የአየር መንገዱ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ቦርድ ቀርቦ እየታየ እንደሚገኝ ጋዜጣው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ማረጋገጡን አመልክቷል።

አቶ መስፍን የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄውን ምክንያት በተመለከተ፤ " የምናንቀሳቅሰው ገንዘብ እያደገ በመምጣቱና የካፒታል ማሻሻያ ከሌለ ትክክለኛ የፋይናንስ አያያዝ ለመፍጠር ስለሚያስቸግር " ነው ብለዋል።

" በተጨማሪም አሁንም አዳዲስ አውሮፕላኖች እያስመጣን ነው፡፡ በምናስመጣበት ወቅት የዕዳና ካፒታል ምጣኔ መመጣጠን አለበት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአውሮፕላን የሚገዛው በብድር ስለሆነ አበዳሪዎቹ ጋ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፍ ያለ የሀብት መጠን መድረስ አለበት። ብለዋል፡፡

የዕዳ እና ካፒታል ምጣኔ ተቋሙ ካለው ካፒታል አንፃር ሲታይ ምክንያታዊ ካልሆነ አበዳሪዎቹ ለማመን እንደሚቸገሩ አቶ መስፍን መግለፃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ50 ሚሊዮን ዶላር ዘመናዊ የኢ-ኮሜርስ የጭነት አገልግሎት ማዕከል እያስገነባ ሲሆን ይኸው ማዕከል በቅርቡ ስራ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ ፤ አየር መንገዱ በካርጎ አገልግሎት ከአፍሪካ ትልቁና በዓለም ተወዳዳሪነቱን ለማስጠበቅ ዘመናዊ አሰራርን ይከተላል ብለዋል።

በዓለም ላይ የዲጂታል ግብይት እያደገ በመምጣቱ የመደበኛው ካርጎ አገልግሎት እየቀነሰ በአንጻሩ የኢ-ኮሜርስ የካርጎ አገልግሎት እየሰፋ መምጣቱን አንስተዋል።

አዲሱን የካርጎ አገልግሎት ማዕከል እውን ለማድረግ እውቀትና የአሰራር ስርዓት በአግባቡ ተዘርግቶለት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

አሰራሩ ከዚህ ቀደም ከነበረው የካርጎ አገልግሎት በእጅጉ የሚለይ ነው ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው ዕቃ ከውጭ ተጭኖ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ይወስድ የነበረውን እስከ 7 ቀን በአዲሱ አሰራር እንደሚቀረፍ ተናግረዌ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያስገነባ ያለው የኢ-ኮሜርስ ማዕከል በ15 ሺህ ስኩዌር ሜትር ላይ ሲሆን 50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ይሆንበታል።

ማዕከሉ በመጪው የፈረንጆቹ 2023 አጋማሽ ላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ኢዜአ አየር መንገዱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወጣቶች እንዳይንቀሳቀሱ የማድረግ ዓላማ የለንም " - የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን ፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ " የኢትዮጵያ መንግስት ሆነ የትግራይ ክልል ወጣቶች  #እንዳይንቀሳቀሱ_የማድረግ_አላማ_የላቸውም " ሲል የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን ፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቀ። ቢሮው ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን እስከ 4 ጊዜ በረራ በማድረግ አገልግሎት…
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ #ከመቐለ በረራ ጋር በተያያዘ መግለጫ አውጥቶ ነበር።

ምን አለ ?

- ወደ መቐለ በረራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እና ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ መንገደኞችን እያገለገለ መሆኑን ገልጿል።

- አየር መንገዱ ቲኬት ገዝተው ወደ ቼክኢን ካውንተር የሚመጡ ተጓዦችን በአግባቡ እያስተናገደ መሆኑን አመልክቷል።

- የመቐለ በረራ በቀን አንድ ጊዜ የነበረ ሲሆን አሁን በየእለቱ የሚደረገው በረራ ወደ ሶስት ከፍ ማለቱን አሳውቋል።

- እለታዊ የበረራ ብዛት ቀንሷል የሚለው የተሳሳተ መረጃ ነው ብሏል፡፡ ወደፊትም የሚኖረውን የበረራ ፍላጎት እየታየ የበረራውን ብዛት ለመጨመር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

- #ከአዲስ_አበባ  ወደ  #መቐለ የሚጓዙ መንገደኞች የአየር መንገዱን የጥሪ ማእከል እና ቲኬት ቢሮዎች በመጠቀም ቲኬት መግዛት የሚችሉ ሲሆን ከመቐለ የሚነሱ ተጓዦች ደግሞ ከመቐለ የአውሮፕላ ማረፊያ የሽያጭ ቢሮ ቲኬቱን መግዛት ይችላሉ፡፡

በተጨማሪ ፦

የበረራ ቲኬቱን አ/አበባ በሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በኩል መግዛት የሚፈልጉ ደግሞ ቦሌ በሚገኘው " የኢትዮጵያ ኤርፖርት ኢንተርፕራይዝ ህንጻ " የምድር ወለል ከሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰአት እስከ ከሰአቱ 11፡00 ሰአት ድረስ መግዛት ይችላሉ ብሏል።

- አየር መንገዱ ባለፉት ስምንት ወራት የመቐለ በረራን ጨምሮ በሌሎች የሃገር ውስጥ በረራዎች ቲኬት ዋጋ ላይ ጭማሪ እንዳላደረገ ገልጿል።

- የኢትዮጵያ ዜግነት ላላቸው ተጓዦች እና የኢትዮጵያ የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸው የውጭ ሃገር ዜጎች የመቐለ በረራ የቲኬት ዋጋ ለመሄጃ ብቻ ከ3450 ብር ጀምሮ ሲሆን፣ የደርሶ መልስ ቲኬት መነሻ ዋጋ ደግሞ 6895 ብር ነው፡፡ 

- " ሻንጣን " በተመለከተ #ከገና_በዓል ጋር ተያይዞ የተጓዦች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ የሻንጣ አገልግሎት ላይ መለስተኛ መጨናነቅ ተፈጥሯል።  በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ ተጨማሪ (ትርፍ) ሻንጣዎችን ለመቀበል ተቸግሮ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን የካርጎ በረራ በመመደብ ችግሩን መፍታት ስለተቻለ ተጨማሪ ሻንጣ መቀበል ጀምሯል፡፡

Credit : Ethiopian Airlines

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊው የ " SKYTRAX " ውድድር ላይ በ5 ዘርፎች ሽልማት ተቀዳጀ።

አየር መንገዱ አሸናፊ የሆነባቸው ዘርፎች ፦

🇪🇹 " Best Airline in Africa 2023 " ለተከታታይ 6ኛ ግዜ፣

🇪🇹 " Best Business Class Airline in Africa 2023 " ለተከታታይ 5ኛ ግዜ፣

🇪🇹 " Best Economy Class Airline in Africa 2023 " ለተከታታይ 5ኛ ግዜ፣

🇪🇹 " Best Business Class Onboard Catering in Africa 2023 " ለተከታታይ 2ኛ ግዜ

🇪🇹 " Cleanest Airline in Africa 2023 " ዘርፎች ናቸው።

አየር መንገዱ ሽልማቶቹን በፈረንሳይ ፓሪስ በተዘጋጀው " Paris Air Show " መርሐ ግብር ላይ ተቀብሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
#Axum #EthiopianAirlines

የአክሱም ኤርፖርትን ለመጠገን የእቃዎች ግዥ መጀመሩ ተነግሯል።

ትግራይ ባስተናገደችው አስከፊው ጦርነት ወቅት ክፉኛ የወደመው የአክሱም ኤርፖርት እስካሁን ተጠግኖ ወደስራ አልተመለሰም።

የአክሱም ህዝብ ኤርፖርቱ ባለመጠገኑ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ነው።

በተለይም የተለያዩ አልባሳትን፣ ባህላዊ ጌጦችን እያዘጋጁ የሚሸጡ፣ ከቱሪዝም ገቢ የሚያገኙ ወገኖች ኤርፖርቱ ስለሌለ ስራ መስራት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

በንግድ ዘርፍ ላይ ያሉ ወገኖች ብዙ ደክመው የሚያዘጋጇቸውን ቁሳቁሶች እና ባህላዊ አልባሳት የሚገዛቸው እንዳጡ አመልክተዋል።

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዑክ ከኣክሱም ነዋሪዎች ጋር ምክክር አድርጎ ነበር። በዚህም ወቅት የአክሱም ኤርፖርት ጥገና ዋነኛው አደጀንዳ እንደነበር ታውቋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መ/ቤት የክልሎች የጥገና ሂደት አስተባባሪ አቶ ተወልደ ግርማይ ፤ አየር መንገዱ ለኤርፖርቱ ጥገና የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶች መገብየት እንደጀመረ አሳውቀዋል።

አቶ ተወልደ ፤ " ምን አለ ? ምን ቀረ ? የሚለውን ለይተን ኤርፖርቱን ለመጠገን የሚያስፈልጉን መሳሪያዎች በመግዛት ላይ ነን። በግዢ ሂደት ላይ ያሉ አሉ። " ብለዋል።

ጥገናው ለህዳር ጽዮን በዓል ይደርሳል ?

ጥገናው ለህዳር ጽዮን ማርያም በዓል አይደርስም ተብሏል።

በየአመቱ ኣክሱም ከተማ የሚከበረው የህዳር 21 ጽዮን በዓል በተለይም ከጦርነት በፊት እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎች ከሀገር እና ከውጭ ይገኙበት እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ላይ ያለው የሰላም ሁኔታም እጅግ በርካታ ሰዎች ወደ ከተማው በብዛት እንዲገቡ እድል የሚፈጥር ነው።

ነገር ግን እስከ በዓሉ ድረስ ያሉት ውስን ቀናት ስለሆነ የኣክሱም ኤርፖርት ተጠግኖ የመጠናቀቅ እድል የለውም ተብሏል።

አቶ ተወልደ ግርማይ ፤ " የህዳር ጽዮን በዓልን ለማድመቅ የሽረ እንደስላሰ ኤርፖት አስፈላጊ በሆነ መሳሪያዎች እንዲሁም የቦይንድ አውሮፕላን የሚያርፉባቸው ስፍራዎች ለማስተካከል፣ ለማጠናከር እና ለማስፋፋት ባለሞያዎች ተሰማርተዋል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቴሌቪዥን ትግራይ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EthiopianAirlines🇪🇹

" የችግሩን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ የበረራ ቁጥሩ " ኢቲ106 " የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ " አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ " ችግር እንዳጋጠመው ይታወቃል።

ይህ በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን አለ ?

- የአውሮፕላኑ በረራ ቁጥር ET106/18 ነው።

- ከአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት የተነሳው ቀን 6:30 ላይ ነው።

- ክስተቱ ያጋጠመው በአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ከቀኑ 8 ስአት አካባቢ ነው። በሚያርፍበት ወቅት ከመንደርደሪያው መንገድ ተንሸራቶ ወጥቷል።

- ሁሉም ተሳፋሪዎችና የበረራ ቡድን አባላት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ወጥተዋል።

- ችግሩ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ / የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

በተፈጠረው ችግር መጉላላት ለደረሰባቸው መንገደኞችም #ይቅርታ ጠይቋል።

Video Credit - Tigrai Television

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

" የአየር መንገዳችንን ሰራተኛ ተግባር ህገወጥ አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ አሳዝኖናል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትናንት ጀምሮ የአየር መንገዱን ዩኒፎርም የለበሰ ሰራተኛን የራሱን ሻንጣ በማስተካከል ላይ ሳለ የሚያሳይ ምስል ከተሳሳተ መረጃ ጋር በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በመዘዋወር ላይ እንዳለ ገለጸ።

ይህን ተከትሎ ፦
* በምስሉ ላይ የሚታየው ግለሰብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ባልደረባ (Ethiopian Aircraft Technician) መሆኑን

* የአየር መንገዱ ዓርማ የታተመበት ሻንጣም የሰራተኛው መሆኑን፤

* በምስሉ ላይ የሚታየው ቦታ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ሰራተኞች የግል ንብረቶቻቸውን እና ለስራ የሚገለገሉባቸውን ቁሳቁሶች የሚያስተካክሉበት አካባቢ መሆኑን ግልጿል።

ሌሎቹ ቦርሳዎችም በምስሉ ላይ ያልተካተቱ የሌሎች ሰራተኞች ቦርሳዎች ናቸው ብሏክ።

" ይህ ስፍራ የመንገደኞች ሻንጣ ሊገኝበት የማይችል ለሰራተኞቻችን ብቻ የተከለለ ቦታ ነው " ያለው አየር መንገዱ በተጨማሪም ሳምንቱን ሙሉ ለ24 ሰዓት በደህንነት የካሜራ ዕይታ ውስጥ የሚገኝ እንደሆነ አመላክቷል።

በስራ ገበታው ላይ የሚገኝ የአየር መንገዱን ሰራተኛ ተግባር ህገወጥ አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ አሳዝኖኛል ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ በምስሉ ላይ የሚታየው የአየር መንገዱ ሰራተኛ የአየር መንገዱ ባልደረባና የሚያስተካክለው ሻንጣም የራሱ መሆኑን አስገንዝቧል።

ደንበኞቹም ከሚዘዋወረው ምስል ጋር ተያይዞ ምንም ስጋት እንዳያድርባቸው አሳስቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች ሆነ ለንብረቶቻቸው ደህንነት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ሰራኞቻችንም ደረጃውን የጠበቀ የደንበኛ አገልግሎት ለመስጠት ትጉህ መሆናቸውን አመልክቷል።

በተሳሳተ መረጃ የብሔራዊ አየር መንገዱን ስም ለማጥፋት ሆን ተብሎ ኃላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከሚሰራጩ የሀሰት መረጃዎች እንድትጠበቁ ሲልም መክሯል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

" ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ናቸው ፤ ሰራተኞቹም በቁጥጥር ስር ውለዋል " - አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰሞነኛና በአየር መንገዱ እንቅስቃሴ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች አየር መንገዱን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ተቀባይነት የለውም " ብለዋል።

በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከአየር መንገዱ በተጨማሪ፦
- ኢሚግሬሽን ፣
- የጉምሩክ ፣
- የብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ የራሳቸው ድርሻ አላቸው ሲሉ ገልጸዋል።

በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስናና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እንጅ የአየር መንገዱ ሰራተኞች አይደሉም ብለዋል።

" ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም " ሲሉ የነበሩት አካላት የጉምሩክ ክፍል ሰራተኞች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

አቶ መስፍን ፤ ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም የተባሉት ደንበኛ ጉዳይ ዋነኛው ቅሬታ እንደነበር አስታውሰው " ድርጊቱን የፈፀሙ የከስተም ወይም የጉምሩክ ክፍል ሰራተኞች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ግለሰቦቹን በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ተናግረዋል።

በቀጣይም አየር መንገዱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን የማይታገስ መሆኑንና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ የደህንነት ካሜራዎች እንዳሉም ተሰምቷል።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም እና WMCC ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት #AddisAbaba በመንገድ ኮሪደር ልማትና በአስፓልት የማንጠፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ መዚህ መሰረት ፡- - ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ - ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አየር መንገድ - ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ…
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ ኤርፖርት የሚመጡ ሁሉ የመንገድ መዘጋቱን ታሳቢ እንዲያደርጉ አሳሰበ።

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በመንገድ ኮሪደር ልማትና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ወደ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስዱ አንዳንድ መንገዶች በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም መንገደኞች ለበረራ ወደ ኤርፖርት በሚሄዱበት ወቅት ይህን ታሳቢ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል መዘግየት ራሳቸው እንዲጠብቁ አሳስቧል።

የሚዘጉት መንገዶች #የትኞቹ_ናቸው ? በዚህ ሊንክ ይመልከቱ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/88048

#EthiopianAirlines

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ክብርን ተቀዳጀ።

በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ' የአቪዬሽን ኦስካር ' ተብሎ በሚጠራው የስካይትራክስ መድረክ ነው ይህን ክብር የተቀዳጀው።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት፣

🏆 በአፍሪካ የኢኮኖሚ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በመባል ተደራራቢ ድልን ተጎናጽፏል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ተገኝቷል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በመግለጫው ባለፈው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ማግኘቱንና ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጿል። ይህ ገቢ በኢትዮጵያ ብር ሲቀመጥ 402 ቢሊዮን…
#EthiopianAirlines🇪🇹

" የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለን ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው " - " አቶ መስፍን ጣሰው

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ምን አሉ?

" ከቅርብ ወራት በፊት ከኤርትራ ሲቪል አቬሽን ቅሬታ ቀርቦልን ነበር፤ ይህም ከተሳፉሪዎች ሻንጣ ተያይዞ ወደኋላ እየቀረ ነው በሚልየቀረበ ነበር።

የተነሳውም የትራንስፖርቴሽን መዘግየትና የሻንጣ ዘግይቶ መድረስ ጋር የተያያዘ ነው። ይህ የተፈጠረው ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ብዙ ሻንጣ ይሸከማሉ፤ ሁሉንም ማስተናገድ ባለመቻላችን በሚቀጥለው በረራ ሻንጣዎችን እንልክ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በፊት የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከ737 አውሮፕላን ውጪ ከፍ ያለ የመንገደኞች ማመላለሻ እንዳንጠቀም እግድ ጥሎብን ነበር። በተጨማሪም በሳምንት ከ10 በረራ ውጪ እንዳናደርግ ተደርጎ ነበር።

መጋቢት ላይ ነው ይኼ የሆነው። ይህን ተከትሎ የኤርትራ ተጓዦች ከሻንጣቸው ጋር እንዲጓዙ ለማስቻል የተሳፋሪዎችን ቁጥር በመቀነስ ተጓዦች ከሻንጣዎቻቸው ጋር እንዲጓዙ አድርገናል። ከዚያ በኋላ ይህ ነው የሚባል ቅሬታ አልሰማንም ነበር።

ይህን ተከትሎ ሰኔ መጀመሪያ ላይ ሌላ ደብዳቤ ተቀብለናል። ይህም የነበሩ በረራዎችን ወደ 15 እንድናሳድግና የምንጠቀመው አውሮፕላን ላይ ነበረው ገደብም መነሳቱን ተገልጾልን ነበር።

ይህንን ግን ወዲያው ተግባራዊ ማድረግ አልቻልንም፤ የአውርፕላን እጥረቶች አሉብን። በዚህ ምክንያት ይኽን ደብዳቤ ከተቀበልን በኋላ በነበረው አሰራር ቀጥለናል።

አሁን ላይ የወጣው ደብዳቤ ግን ከመስከረም 30/2024 በኋላ በረራ እንዳይደረግ የሚገልጽ ነው። ይህን ተከትሎም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ክስ ቀርቦብናል፤ በዚህ በጣም አዝነናል።

ይህ ሁሉ ሲሆን እንደ ዓለም አቀፍ አሰራር ቅሬታዎቹ ላይ እንወያይ ተብሎ ጥያቄ አልቀረበልንም፤ የነበሩ ችግሮች ላይ ቀደም ብለን መፍትሔ ሰጥተናል።

አሁንም የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን እንዲያጤነው እንጠይቃለን፤ ይህን የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ግን ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው። "


#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

ዛሬ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከለሊቱ 09፡00 ሰአት ጀምሮ በነበረው ከፍተኛ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት አብዛኞቹ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ የነበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሊያርፉ ባለመቻላቸው በአቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ ኤርፖርቶች ተመልሰው እንዲያርፉ መገደዳቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

ይህ የአየር ሁኔታ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም-አቀፍ የጠዋት በረራዎች ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ አመልክቷል።

አየር መንገዱ ፥ " የመንገደኞቻችን ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብሎ " ከዚህ ጋር ተያይዞ በተሳፋሪዎቻችን የጉዞ ዕቅዶች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ መስተጓጉሎችን ለመቅረፍ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረግን እንገኛለን " ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞች ላጋጠማቸው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines🇪🇹 " የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለን ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው " - " አቶ መስፍን ጣሰው የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው…
#EthiopianAirlines

ወደ አስመራ የሚያደርገው በረራ ከነገ ጀምሮ ይቋረጣል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በረራውን የሚያቋርጠው በኤርትራ ውስጥ አገልግሎቱን ለመስጠት ባጋጠመው ከአቅም በላይ በሆነ የአሰራር ችግር እንደሆነ ገልጿል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር ትኬት የቆረጡ መንገደኞች ያለምንም ተጨማሪ ወጪ በሌሎች አየር መንገዶች ጉዟቸውን እንዲያደርጉ ጥረት እንደሚያደርግ አሳውቋል።

" የትኬት ገንዘብ ይመለስልን " የሚሉ ካሉም ለቲኬታቸው ሙሉ ገንዘብ ተመላሽ እንደሚያደረግ ገልጿል።

በበረራው መቋረጥ ምክንያት ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “ Best Overall in Africa award ” ሽልማት ማሸነፉን አሳውቋል።

አየር መንገዱ ፦
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ መስተንግዶ፣
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ አገልግሎት፣
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት፣
🛫 በምርጥ የአውሮፕላን ውስጥ መቀመጫ ምቾት
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸልሟል።

ይህ በ “ Airline Passenger Experience Association ” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት ነው።

በአቪዬሽን ኢንደስትሪውም ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ እንደሆነ አየር መንገዱ ገልጿል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia