TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AmharaBank

አማራ ባንክ ስራውን ለመጀመር ከጫፍ መድረሱን አስታውቋል።

ባንኩ ትላንት በላከልን መግለጫ ፤ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና ለባንክ ኢንዱስትሪው እድገት ተጨማሪ ጉልበት ለመፍጠር በሚያስችል ደረጃ ስራው ለመጀመር ጫፍ መድረሱን ገልጿል።

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ " የባንክ ስራ ፍቃድ " (Banking Business License) ካገኘ በኃላ ለተለያዩ የባንኩ የስራ ክፍሎች እንዲሁም ቅርንጫፎች ብቃት ያላቸውን ሰራተኞችን በመመደብ የቅድመ ስራ ጅማሮ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጿል።

በተጨማሪ የባንክ አገልግሎቱን በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ የቅርንጫፍ ቦታ መረጣ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠሉን አሳውቋል።

ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የኮር-ባንኪንግ ቴክኖሎጂ በዘርፉ ስመ-ጥር እና ታዋቂ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ጋር ውል በማሰር የቴክኖሎጂ ኩባንያው ወደ ስራ መግባቱን ገልጿል።

አማራ ባንክ ፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋርም ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማዕከል አገልግሎት ስምምነት ከቀናት በፊት መፈራረሙን አሳውቋል።

ባንኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቀላጠፈ እና እጅግ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አብስሯል።

የአማራ ባንክ አ.ማ ከ190,000 በላይ በሆኑ ባለአክሲዮኖች የተመሰረተ ፤ ከፍተኛ መነሻ ካፒታል ማሰባሰብ የቻለና በአንጋፋነት የተመሰረተ ባንክ መሆኑን በተላከልን መግለጫ ላይ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#AmharaBank

የአማራ ባንክ ነገ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ ይጀምራል።

ባንኩ ነገ በይፋ ስራ የሚጀምርበትን የምረቃት ስነስርአት ከጥዋት 3:00 ጀምሮ ለገሃር በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ያካሂዳል።

ነገ ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያካሂደውን የምርቃ ስነስርዓት በማስመልከት በልዩ ሁኔታ ለአዲስ አበባ እና ዙሪያው #አንበሳ አውቶቡስ ተጠቃሚዎች በሙሉ የሙሉ ቀን (ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3፡ዐዐ ሠዓት) የጉዞ ክፍያን ሸፍኗል።

የአዲስ አበባ እና የዙሪያዋ የአንበሳ አውቶቡስ ተጠቃሚዎች በነጻ ወደሚፈልጉባቸው ቦታዎች መጓጓዝ ይችላሉ።

በተጨማሪም ባንኩ በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች በተመረጡ ሆስፒታሎች ለሚወልዱ እናቶች በባንኩ ስም " የእንኳን ደስ አላችሁ " ስጦታ የሚያበረክት ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ አማራ ባንክ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ሥራውን በይፋ ጀምሯል። የባንኩ የምረቃ እና ስራ ማስጀመሪያ ሰነ ስርዓት ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ነው የተካሄደው። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ፦ - የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ፣ - የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ - የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት…
#AmharaBank

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ዛሬ በዛሬው የአማራ ባንክ ይፋዊ ምረቃና ስራ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የተናገሩት ፦

" አማራ ባንክ ወደ ገጠሩ ማህበረሰብ በመድረስና ከፍተኛ የአክስዮን ድርሻን በመሸጥ እንዲሁም ከፍተኛ የተከፈለ ካፒታል ይዞ የባንክ ኢንዱስትሪውን በመቀላቀል ቀዳሚው ነው።

በቴክኖሎጂ እና በአገልግሎት አሰጣጥም ተወዳዳሪ በመሆን ቀዳሚ መሆን እንዲችል ራሱን ሊያዘጋጅ ይገባል።

ይህ ከሃገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ከሚታሰቡ የውጭ ባንኮች ጋር ጭምር ለመወዳደር ያስችላል።

ወደ ሀገር እንደሚገቡ ከሚጠበቁት የውጭ ባንኮች ጋር ለመወዳደር ትልቅ ዝግጅት ይጠብቀናል። ለዚህም አማራ ባንክን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ባንኮች ራሳቸውን ሊያዘጋጁ ይገባል።

አማራ ባንክ ይህን የሚያደርግና የቁጠባ ገንዘብ አቅሙን ለማሳደግ የሚችል ከሆነ በአጭር አመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል።

... 60 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን የተንቀሳቃሽ ስልክ (ሞባይል) ተጠቃሚ ናቸው ፤ አማራ ባንክ የተፋጠነ የሞባይል አገልግሎትን በየደረጃው ለመስጠት መስራት አለበት።

የሞባይል አገልግሎት የሚሰጡ የውጭ ተቋማት በቅርብ ጊዜ የአገልግሎት ፈቃድ ሊያገኙ ይችላሉ፤ በአሁኑ ወቅት ቴሌ ብር ብቻ ነው አገልግሎቱን እየሰጠ የሚገኘው በመሆኑም አማራ ባንክ ቅርንጫፎችን ከመክፈት በዘለለ በቴክኖሎጂ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ወደ ከፍታ ሊወስደው እንደሚችል አስባለሁ "

#ALAIN

@tikvahethiopia
#አማራ_ባንክ

እንኳን ደስ አላችሁ! አማራ ባንክ አንድ ዓመት ሞላው! በዚህ አንደኛ ዓመት በዓላችን በውስጥ አቅም የበለጸገውን የሞባይል ባንክ መተግበሪያ ወደ እናንተ ስናቀርብ በደስታ ነው፥ ABa Mobile Banking ከፕሌይ ስቶር በማውረድ የባንካችንን ዲጂታል ዓለም ይቀላቀሉ።

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች
Website: https://amharabank.com.et/
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Telegram: https://t.iss.one/Amhara_Banksc
Instagram: https://instagram.com/amhara_bank
Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/
YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g

#አማራባንክ #AmharaBank
#አማራ_ባንክ

አማራ ባንክ የኅብረተሰቡን የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀም ልምድ እና ፍላጎት ላይ ያተኮረ ጥናት እያደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እርስዎም ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጫን ይህን መጠይቅ እንዲሞሉ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

https://docs.google.com/forms/d/1oGb8jFYvXVn5Z4GHxYjljGs9F4anGLrBiuZ1CaNgEhs/edit

እናመሰግናለን!

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Telegram: https://t.iss.one/Amhara_Banksc
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1
Website: https://amharabank.com.et/

#አማራባንክ #AmharaBank