TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbeba #Lyon

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከፈረንሳይዋ ሊዩን ከተማ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ኬሚልፊልድ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በአዲስ አበባ እና በሊዬን ከተማ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን በተለያዩ መስኮችም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

ማስታወሻ!

በነገው ዕለት (ታህሳስ 02/2012) ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የሚደረገው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ባሉት ግራና ቀኝ መንገዶች ላይ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ማቆም የተከለከለ ነው።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ እንድትጠቀሙ፦

• ከኡራኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ

• ከቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ

• ከቦሌ ኤድናሞል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ

• ከብሔራዊ ቤተ-መንግስት፤ ከፍል ውኃ፤ ከለገሀር፤ ከካሳንችስ፤ ከሳንጆሴፍ ትምህርት ቤት፤ ከስታዲየምንና ከሃራምቤ ሆቴል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ዝግ ይሆናሉ።

የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት እና መረጃ ለመስጠት የምትፈልጉ በስልክ ቁጥሮች ፡-
011-1-11-01-11
011-5-52-40-77
011-5-52-63-02
011-5-52-63-03 ወይም በነጻ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም ይቻላል፡፡

(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

@tikvahethiopiaBot @tikvagethiopia
#MekelleUniversity #AddisAbeba

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን የምክክር መድረክ በሀርሞኒ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩ "የAlmuni ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ውጤት" በሚል ርእስ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።ከ200 በላይ የቀድሞ ምሩቃን፣ መምህራን እንዲሁም የአሁን ተማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

(ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ የሚገኙ የቆዩ ላዳ ታክሲዎች በአዳዲስ ታክሲዎች እንዲተኩ እንደሚደረግ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናገሩ። ለዚህም የታክሲ ባለቤቶችን ከባንክ ጋር የማስትሳሰር ስራ እንደሚሰራም ኢ/ር ታከለ ገልጸዋል። የአዲስ አበባ የታክሲና የሀይገር ባስ ማህበራት ለተገልጋዩ ክብርን በመስጠት ለማገልገል የሚያስችል መርሐ ግብር ይፋ ማድረጊያ መድረክ ተከናወናል። በመርሀ ግብሩ ላይ 13 የታክሲ እና ሶስት የሀይገር ባስ ማህበራት ተሳትፈዋል። መርሐ ግብሩ በተለይ ለአረጋውያን፣ ለነፍሰጡሮች እና ለአካል ጉዳተኞች በተሻለ መንገድ ለማገልገል የሚያግዝ ነው። በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት ኢ/ር ታከለ ኡማ አነስተኛ ታክሲዎችና ሀይገር ባሶች ለነዋሪው እየሰጡ ላሉት አገልግሎት አመስግነዋል።

(EPA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የጥምቀት ክብረ በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ መድረክ በሚሌኒየም አዳራሽ ተካሂዷል። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የጥምቀት በዓል አከባበርን ከመስቀል በዓል፣ የገዳ ስርዓት እና የፍቼ ጨምበላላ ክብረ በዓላትን ተከትሎ አራተኛው የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወስ ነው፡፡

(Mayor Office of AA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ የላዳ ታክሲ ባለንብረቶች ጋር በመነጋገር በዝቅተኛ ወለድ የረጅም ጊዜ ብድር አመቻችቶ አዳዲስ ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት  እየተሰራ መሆኑን የከተማ መስተዳድሩ የትራንስፖርት ባለስልጣን  አስታውቋል።

የትራንስፖርት ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮማንደር አህመድ መሐመድ እንዳሉት፤  አሮጌ ላዳዎችን በአዳዲስ ተሽከርካሪዎች የመቀየር ስራው የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ና የተገልጋዩን ምቾት ከመጠበቅ ባሻገር ለቱሪዝም መስህብነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል።

መቀየር አለባቸው ተብለው ተመዝግበው የሚገኙ ያገለገሉ ላዳ ታክሲዎች ምን ያህል ቁጥር እንዳላቸው የማጣራት ስራ መጠናቀቁን የጠቀሱት ኮማንደር አህመድ፤ ለጊዜው 8 ሺህ 95  ላዳዎች የተመዘገቡ ሲሆን አዳዲሶቹን በአንድ ግዜ ማስገባት ስለማይቻል በተለያየ ግዜ ወደ ሀገር  ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል ነው ያሉት።

አሮጌ ላዳዎቹን የመቀየር ስራ በአጭር ጊዜ እንደሚጀመር ገልጸው፤ ከናፍጣ በሚወጣው ጭስ የሚፈጠረውን የከተማዋን የአየር ብክለት ለመቀነስ አዳዲስ የሚገቡት በኤሌክትሪክ እንዲሰሩ ለማድረግ  እየተሰራ እንደሆነም ገልጸዋል።

(ENA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Hawassa #AddisAbeba #Wolkite

በሞጣ ከተማ የተፈፀመውን የመስጂዶችና የንብረት ቃጠሎ የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። በጅማ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ህዝብ በጅማ ከተማ ስታዲየም ተገኝቶ ድርጊቱን አውግዟል። በሃዋሳ ከተማ በመስጂደ-ራህማ ፣ በወልቂጤ ፣ በአሰላ ፣ በአዲስ አበባ ኑር መስጂድ፣ በኢሊባቡር እና ሌሎች ከተሞች ህዝበ መስሊሙ "ድምፃችን ይሰማ" በሚል የተቃውሞ ድምፁን አሰምቷል።

በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ ህዝቡ መንግስት አጥፊዎችን በአስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርብ፤ የንብረትም ሆነ ሌላ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸውና በክልሉ መንግሥት ይቅርታ እንዲጠየቁ፣ የተቃጠሉ መስጂዶችን በአፋጣኝ በማስገንባት የዘወተር አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ እንዲደረግ ተጠይቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን...

#AddisAbeba

የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን በበአላት መዳረሻ ወቅት የሚፈፀሙ ወንጀሎችንና ህገ - ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ባከናወነው ኦፕሬሽን ህገ- ወጥ የጦር መሣሪያዎችን እና ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ጨምሮ በርካታ የወንጀል ፍሬዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል፦

- 11 ሽጉጦች ከ1600 በላይ መሰል የሽጉጥ ጥይቶች እንዲሁም ሀሰተኛ የብር ኖቶች ከማተሚያ ማሽን ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

- ቅዳሜ ታህሣስ 25/2012 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 አካባቢ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው ኒያላ ሞተርስ ጀርባ ወንጀል የፈፀሙ 6 አባላት ያሉት አንድ የዘረፋ ቡድን በህብረተሰቡ ትብብር በሰዓታት ልዩነት ተጠርጣሪዎቹን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

- በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መርካቶ ሸክላ ተራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከበርበሬ ጋር ባዕድ ነገር ቀላቅለው ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 6 ተጠርጣሪዎች ከነ-ኤግዚቢቱ ሊያዙ ይችለዋል።

- ከተለያዩ ተሽከርካሪዎች ላይ 8 ተጠርጣሪዎች ከሰረቁት 331 ስፖኪዮ፤ የዝናብ መጥረጊያ እና ሌሎች የተሽከርካሪ አካላት፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ፣ላፕቶፕ ኮምፒውተር ፣ ቴሌቪዥን ፣ የቤት እና የግንባታ ዕቃዎች እንዲሁም ግራሙ ያልታወቀ አደዛዠ እፅ በተደረገ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ ይሰጥ የነበረውን የትራፊክ ክፍያ አገልግሎት ሌሎች አራት ባንኮችን በመጨመር በአምስት ባንኮች የክፍያ አገልግሎት መሠጠት ይጀምራል። ኢንጂነር ታከለ ኡማ የትራፊክ ክፍያን በዘመናዊ መንገድ ለመቀየር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከዘርፉ ባለሞያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

የትራፊክ ክፍያዎች የ"ለሁሉ" አገልግሎት ከተቋረጠ በኃላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ይህም አሽከርካርዎች እንዲጉላሉ እና ረዥም ወረፋ እንዲጠብቁ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህም ክፍያ ለመክፈል ያለውን መጉላላት ለመቀነስና ጊዜያቸውን ለመቆጠብ አሸከርካሪዎች የትራፊክ ክፍያዎችን በአቅራቢያቸው ባሉ፦

- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣
- የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ፣
- የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ፣
- የአቢሲኒያ ባንክ እና የዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች በመሄድ ክፍያ መፀጸም ይችላሉ፡፡

(Mayor Office Of AA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ዻዻስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዘንድሮውን በዓለ ጥምቀት ጃን ሜዳ ተገኝተው ቡራኬና መልዕክት አስተላልፈዋል፦

- ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዋደድን አስተምሯል። እንደ ጥምቀት ያሉ በዓላት የአንደነትና ፍቅር አስተምሮት ያዘሉ በመሆናቸው ለአገር አንደነትና ነፃነት ጉልህ ሚና አበርክተዋል ብለዋል፡፡

- በዓለ ጥምቀቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንሰና የባህል ድርጅት በማይዳሰስ ቅርስነት በተመዘገበ ማግስት በመከበሩ የዘንድሮውን በዓል ልዩ ያደርገዋልም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

- በዓሉ ከኢትዮጵያም አልፎ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ትልቅ ኩራት መሆኑን በመግለፅ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

- ቤተክርስቲያን በአገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ አፍራሽ ድርጊቶችንም በፅኑ እንደምታወግዝ አስታውቀዋል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፍቅር ተሳስቦ፣ እርቅና ሠላም የሰፈነባት አገር እንድትኖር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

- የመንግስት አካላትም በመላ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ መቻቻልና አንድነት እንዲጠነክር፣ እኩልትና ፍትህ እውን እንዲሆን በትጋት እንዲሠሩም ጠይቀዋል፡፡

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia