TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፖሊስ አባላቱ ላይ ክስ ተመሰረተ‼️

#ቂሊንጦ_ማረሚያ_ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሰረተ።

ተከሳሾች ኦፊሰር ገብረማርያም ወልዳይ አብርሃ፣ ሱፐር ኢንተንደንት አስገለ ወልደጊዮርጊስ ወልደማርያም፣ ዋና ሱፐር ኢንተንደንት  አሰፋ ኪዳኔ ተድላ፣ ሱፐር ኢንተንደንት ገብረእግዚአብሄር ገብረ ሃዋርያት፣ ሱፐር ኢንተንደንት ተክላይ ሀይሉ ተክለ ሃይማኖት፣ ሱፐር ኢንተንደንት አቡ ግርማ ወልደሚካኤል፣ ሱፐር ኢንተንደንት አዳነ ሀጎስ ህሻ እና ሱፐር ኢንተንደንት ገብራት መኮንን ገብሩ ናቸው።

ተከሳሾች በፌደራል ማረሚያ ቤቶች የቂሊንጦ፣ የዝዋይ እና የሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት በተለያየ የሃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውም ተገልጿል።

የክሱ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ከነሀሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ቂሊንጦ ማረፊያ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት ከኃላፊዎች በተሰጠው ትዕዛዝ ማንነታቸው ባልተለየ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት በተተኮሰ ጥይት በታራሚዎች ላይ ከባድ አካላዊ ጉዳትና ህይወታቸው እንዲያልፍ ተደርጓል።

በማረሚያ ቤት ቃጠሎ ምክንያት ከ400 በላይ የሚሆኑ ታራሚዎችን ወደ ሸዋሮቢት ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት እንዲወሰዱ በማድረግ የነበራቸውን ንብረት በመቀበል በባዶ እግራቸው በቁምጣ ብቻ በመኪና ላይ እንዲጫኑ በማድረግ፤ ሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ሲደርሱም በመስመር በማሰለፍና በማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላት በዱላ በመደብደብ፣ 175 የሚሆኑ ታራሚዎችን ደግሞ ባዶ ቤት የሴሚንቶ ወለል ላይ እንዲተኙ በማድረግ፣ ለሁለት ለሁለት በካቴና በማሰር ለረዥም ጊዜ በማቆየት፤ በካቴና እጃቸውን ሁለት ሁለት እያደረጉ በማሰር በባዶ እግራቸው ሽንት ቤት እንዲጠቀሙ በማስደረግ፣ እጃቸውን ሳይታጠቡ ምግብ እንዲመገቡ እና ህክምና በመከልከል እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ አድርገዋል ይላል ክሱ።

ከዚህ በተጨማሪም ምርመራ ጨርሰው ወደ ሌላ ክፍል ሲዘዋወሩ ለ42 ቀናት ከአልጋ ጋር ለ24 ሰዓት በካቴና በማሰር፣ 37 የሚሆኑ ተበዳዮች ፍርድ ቤት ረበሻችሁ በማለት ከ3 እስከ 6 ወር እጃቸውን በካቴና አስሮ ጨለማ ቤት ውስጥ በማሰር፣ ግለሰቦች የለበሱትን ልብስ በማስወለቅ በቲሸርትና በቁምጣ በማስለበስ እና በፌሮ ብረት እንዲደበደቡ በማድረግ ኢ- ሰብአዊ ድርጊት እንዲፈጸምባቸው ያደረጉ በመሆኑ በፈጸሙት ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ወንጀል ተከሰዋል።

የተከሳሽ ጠበቆች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር የተከራከሩ ቢሆንም የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት የሚያስከለክል በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም።

ተከሳሶችም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ዐቃቤ ህግ የመሰረተባቸው ክስ በችሎቱ ተነቦ ለቀረበባቸው ክስ መልስ ይዘው ለመቅረብ ለየካቲት 27 ቀን 20011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙን ከፌደራል ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 12/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን 82ኛ ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። መታሰቢያ ስነ ስርዓቱ በተለይ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰማእታት አደባባይ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው የተካሄደው።
.
.
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጣልያኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ኤሬአ ጋር የነበረውን ስምምነት ቀይሮ ከእንግሊዙ አምብሮ ኩባንያ ጋር የአራት አመት የትጥቅ ልብስ ማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የክልሉ መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ #ጥረት_ኮርፖሬሽን የ10 ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
.
.
ግሎባል አልያንስ ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር #ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር #መለገሱን አስታውቋል።
.
.
በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር #ለድርድር እንደማይቀመጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታውቋል። ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን #ያአበሎ_ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
.
.
“ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” የሽኝት መርሃ ግብር ከነገ በስቲያ በይፋ እንደሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
.
.
ከነገ በስቲያ/ሀሙስ የካቲት 14/2011 ዓ.ም. የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በሀዋሳ ከተማ የጠራው #ሰላማዊ_ሰልፍ በመንግስት ፍቃድ አግኝቷል።
.
.
ጥቅምት 4/2011 ዓ/ም ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (#ቴዲ_አፍሮ) በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ደረጃውን በጠበቀ የድምፅ እና የምስል ጥራት #በዲቪዲ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16 ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።
.
.
#የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት #ከሀዋሳ_ከተማ ነዋሪዎች ጋር #ተወያይተዋል
.
.
ድሬዳዋ ውስጥ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ፋብሪካ #ሊገነባ መሆኑን የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ተገልጿል።
.
.
#ቂሊንጦ_ማረሚያ_ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሁለተኛ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ አስታውቀዋል።
.
.
የሱማሊያ ጫት ነጋዴዎች ከኬንያ ጫት ማስገባታቸውን ትተው #የኢትዮጵያን_ጫት ለመግዛት መወሰናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል፡፡
.
.
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር #አላስቴይር_ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።
.
.
የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን መኖሪያቤቶች ማፍረስ ጀምሯል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦነግ አባላት ህዝቡን #እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዞኑ፣ መነ ሲቡ ወረዳ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
.
.
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋራ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia