TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ሃይልና በአየር የታገዘ የፖሊስ ቡድን እሰከማቋቋም የደረሰ የአደረጃጀት ማስተካከያ አደረገ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል #እንዳሸው_ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ የኮሚሸኑ ተቋማዊ ሪፎርም ሂደት እና የደረሰበትን ደረጃ አብራርተዋል።

የሰው ሃይል፣ ቴክኖለጂ፣ ስልጠና፣ ሎጅስቲክስ እና ከባለደርሻ አካላት ጋር የሚኖር ግንኙነት ላይ መሰረት ያደረገው #ሪፎርም በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በረፎርሙ መሰረት የፌዴራል ፖሊስ ሰራዊት አሰፋፈር እና አደረጃጀት #መከለሱን እንዲሁም በአራት አቅጣጫ በአራት ክላስትሮች እንዲከፋፈል መደረጉን ነው የገለፁት። ክላስተሮቹም፥ ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምእራብ እና ማእከላዊ ክላስተር ናቸው።

በሪፎርሙ መሰረት የከተማ ልዩ የፌደራል ፖሊስ ሃይል እና #በአየር የታገዘ ክትትል ለማድረግም የፌራል ፖሊስ የአየር ሃይል ክንፍ ( AIR WING ) #ይደራጃልም ብለዋል ኮምሽነር ጀነራሉ።

የጦር መሳሪያ ትጥቅን በተመለከተም የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊስ እና ልዩ ሃይል እንዲሁም ሚሊሻዎች ምን አይነት መሳሪያ ሊታጠቁ ይገባል የሚለውን የሚመልስ አዋጅ በመዘጋጀት ላይ ነው።

የሪፎርሙ አካል የሆነ የምርመራ ስርኣትን በሚመለከትም የምርመራ ማንዋል ተዘጋጅቶ በቅርቡ ወደ ትግባራ እንደሚገባ ተነግሯል።

#ፌዴራል_ፖሊስ ካሁን ቀደም ከምርመራ ጋር የተያያዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቀረት ካሜራ የተገጠመላቸው፣ በመስታውት የተከለሉ፣ ሶስተኛ ወገን ምርመራውን መከታተል የሚችልባቸው የምርመራ ክፍሎች መዘጋጀታቸውም በመግለጫው ተነስቷል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia