TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION

" በቦረና ዞን የተከሰተው ድርቅ ወደ ምሥራቅ ባሌ ዞን እየተስፋፋ ነው " - የኦሮሚያ አደጋ ስጋትና የተነሽዎች ልማት ኮሚሽን

በቦረና ዞን የተከሰተዉ ድርቅ ወደ ምሥራቅ ባሌ ዞን እየተስፋፋ በመሆኑ ቀጣይነት ያለዉ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የኦሮሚያ አደጋ ስጋትና የተነሽዎች ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።

የኦሮሚያ አደጋ ስጋትና ተነሽዎች ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሺነር ገረሙ ኦሊቃ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፤ ቶሎ መፍትሔ ካልተበጀለት በስተቀር በቦረና ዞን የተከሰተዉ ድርቅ በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ምሥራቅ ባሌ ዞንና ሌሎች ኦሮሚያ ዞኖች እየተስፋፋ ነው።

በቦረና ዞን የተከሰተዉ ድርቅ በመንግሥት፣ በባለሀብቱና በኀብረተሰቡ በተደረገዉ ጥረት በሰዉ ሕይወት ላይ ጉዳት ሳያደርስ መከላከል ተችሏል ብለዋል።

እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ ምዕራብና ምሥራቅ ጉጂ፣ ምዕራብ ሀረርጌና ምሥራቅ ባሌ ዞኖች በቅርቡ ድርቅ ከታየባቸዉ አካባቢዎች ዉስጥ ይጠቀሳሉ።

ችግሩን ለመፍታት የክልሉና ፌዴራል መንግሥት ባለሀብቱና ኅብረተሰቡ በተለመደ መልኩ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

የምግብና ዉሃ ችግርን ለመቅረፍ 25 ሺህ 330 ኩንታል እህልና 38 ቦቴዎችን በማቅረብ ችግሩን ለመቀነስት ጥረት እየተደረገ ነዉ።

የክልሉ መንግሥት ችግሩን ለመቅረፍ ከያዘዉ መቶ ሚሊዮን ብር በተጨማሪ ድርቁ በተስፋፋባቸዉ አካባቢዎች ለምግብና ለዉሃ አቅርቦት የሚዉል ተጨማሪ በጀት መመደቡን ተናግረዋል።

ችግሩ ሰፊና ዉስብስብ በመሆኑ በመንግሥት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ሌሎች አካላትም ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

#EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲን አስጠነቀቀች። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እንዲሁም ድርጅቶች የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት መቀጠላቸውን የኢትዮጵያ መንግስት አስታውቋል። ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ ተከባለች የሚል መረጃን ያሰራጩ እንደነበር ያስታወሰው መንግስት አሁን ደግሞ የሽብር ጥቃት ይፈፀማል የሚል ሀሰት መቀጠሉን ገልጿል። ኤምባሲው እና የአሜሪካ መንግስት የሀሰት መረጃዎችን ከማስተላለፍ እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ…
የአሜሪካ ኤምባሲ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቀማት ላይ ጫና በማድረግ ከአዲስ አበባ ለቀው እንዲወጡ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንግስት አስታውቋል።

በተለይም በህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ጥያቄ ያላቸውን ሀገራት በማስተባበር የአፍሪካ ህብረት መቀመጫን ከአዲስ አበባ ወደሌላ ሀገር እንዲዛወር ግፊት በማድረግ ላይ መሆኑንም መንግስት ገልጿል።

ኤምባሲው ከነዚህ እና ተመሳሳይ ተግባሮቹ እንዲታቀብ መንግስት አስጠንቅቋል። - #EPA

@tikvahethiopia
#ቅዱስ_ገብርኤል

• " ምንም የጸጥታ ስጋት አይኖርም " - የኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ

• " የሀዋሳ ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ ነው ያለው " - የሀዋሳ ፖሊስ መምሪያ

ነገ የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ እና የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አሳውቀዋል።

በዓሉ በተለይ በቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ በርካታ እንግዶች የሚታደሙበት እንደመሆኑ ያለምንም የጸጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው እንደ ክልል በቂ ዝግጅት በመደረጉ ምንም የጸጥታ ስጋት አይኖርም ብሏል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በበኩኑ የቅዱስ ገብርኤል በዓል በከፍተኛ ድምቀት በሚከበርባት ሀዋሳ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተጠናቋል ሲል አሳውቋል።

የከተማው ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ መሆኑንም አረጋግጧል።

በአሁኑ ወቅት ኅብረተሰቡ አካባቢውን በመጠበቅ እና መረጃ በመለዋወጥ ትልቅ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

ከዚህ በተጨናሪ በጠ/ሚኒ ዐቢይ አሕመድ ጥሪ ከውጭ አገራት የሚመጡትን እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት መደረጉን ሀዋሳ ፖሊስ አሳውቋል።

የእንግዶችን ሰላም ለማስጠበቅ የጸጥታ ኃይሎች አስተማማኝ ዝግጅት ማድረጋቸው ተጠቁሟል። እንግዶች ምንም ዓይነት የጸጥታ ስጋት ሊኖራቸው አይገባም ተብሏል።

ነጋዴዎች በተለይ ሆቴሎች አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ጠንካራ ቁጥጥር እንደሚደረግ እና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ለእንግዶች መኪና ማቆሚያ እንደተዘጋጀ የሀዋሳ ፖሊስ አሳውቋል።

#Kulubi #Hawassa #EPA

@tikvahethiopia
" መንግስት አጥፊዎችን ተከታትሎ ለህግ ማቅረብ ይገባዋል " - የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን ድርጊት እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታውቋል።

ጉባኤው ሃይማኖቶች የትህትና፣ የሰላምና የአንድነት፣ የፍቅርና መከባበር መሠረቶች ናቸው ብሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የሰላም መሠረት ሆና ዘልቃለች ያለው የጉባኤው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን አጥብቀን እንቃዎማለን ሲልም ገልጿል።

ጉባኤው ፤ ጥር 12/2014 ዓ.ም በቡራዩ ከተማ አስተዳደር በሕግ ማስከበር ሽፋን በቤተክርስቲያኗ ላይ የተቃጣው ድርጊት ፍጹም ሕገ ወጥ ነው ያለው መግለጫው መንግሥት አጥፊዎችን ተከታትሎ ለሕግ እንዲያቀርብም ጠይቋል።

መንግሥት የሃይማኖትን እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቀው ጉባኤው የሕይዎት፣ የአካልና የመንፈስ ስብራት በደረሰባቸው ወገኖች የተሠማንን ጥልቅ ሐዘንም በተሰበረ ልብ እንገልፃለን ብሏል።

#EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፈው ዓርብ በሃይማኖት አባቶች ፀሎትና ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በተውጣጡ የአገር ሽማገሌዎችና እናቶች ምርቃት የተከናወነበት የሥራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አከናውኗል። የምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርዓያ በወቅቱ ባሰሙት ንግግር፤ በኢትዮጵያ እርስ በርስ የማያግባቡ ጉዳዮችን ነቅሶ በማውጣት፣ በመነጋገርና በመደማመጥ " የሕዝብ ለቅሶና ዋይታ መርገብ…
#ETHIOPIA

ፕ/ር መስፍን አርዓያ (የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር) ፦

" ... የምክክር ኮሚሽኑ አመቻች እንጂ አደራዳሪም ሆነ እርቅ አስፈጻሚ አይደለም።

ኮሚሽኑ የድርድር ሥራ እንደማይሰራ፤ ዕርቅ እንደማያስፈጽም ሕዝብ ሊያውቅ ይገባል።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮችና አባላትን ለምክክሩ የሚረዱ መድረኮችና አጀንዳዎችን በማመቻቸት አስፈላጊው ሥራ ለማከናወን የተመረጥን መሆኑን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል።

የኮሚሽኑ ሥራ አጀንዳ ነቅሶ ሕዝብን ለውይይት መጋበዝ ነው። ለሕዝብ ከሚቀርቡት አጀንዳዎች ውስጥ መግባባት ላይ የሚያደርሰውን መንገድ እናመቻቻለን።

በዚህ አካሄድ ኮሚሽኑ አመቻች ሲሆን ዋናው ወሳኙ ሕዝብ ነው።

ምክክሩ ወደ ' ብሔራዊ እርቅ ' የሚወስድ ከሆነም በእራሱ አሰራርና አካሄድ መሰረት ወደ እርቅ ይሄዳል እንጂ ኮሚሽኑ ሽምግልና እና አሊያም ብሔራዊ እርቅ ማስፈጸም ውስጥ አይገባም።

አንዳንድ ጊዜ በተሳሳተ መንገድ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን አሸማጋይ አሊያም አደራዳሪ አድርጎ የሚያይ ካለም የተሳሳተ ነው። የኮሚሽኑ ኃላፊነት አካታች በሆነ መንገድ ሁሉንም ጉዳይ አለኝ የሚል ወገንን በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ እንዲመክር ማድረግ ነው። "

#EPA

@tikvahethiopia
#ከፍተኛ_የደም_እጥረት_ተከስቷል !

በብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ዘርፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ተመሥገን አበጀ ፦

" በአገሪቱ ያሉት የሁለቱ ትላልቅ ሃይማኖቶች ተከታዮች ፆም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ በመላ አገሪቱ ከፍተኛ የደም እጥረት ተከስቷል።

በአገሪቱ ያለውም የመጠባበቂያ ደም ክምችት ከ5 ቀናት የማይበልጥ ነው።

በአገር ደረጃ ሲታይ ከፆም በፊት በዚህ ዓመት የነበረው የደም ክምችት አመርቂ የሆነበት ዓመት ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል።

የዐቢይና ረመዷን አፁዋማት ከገቡ በኋላ የመደበኛ ደም ለጋሾችም ሆነ ሌሎች ለጋሾች ቁጥር አሽቆልቁሏል።

ይህም የደም ክምችት ላይ ከፍተኛ እጥረት እንዲፈጠር አድርጓል።

በተለይ እንደ ፕላትሌት የደም ተዋፅዖ እና ‘ኦ’ የደም ዓይነት ክምችቶች እጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ፕላትሌት የሚባለው የደም ተዋፅዖ ለካንሰር ታማሚዎች እና የደም መፍሰስ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የሚሰጥ የደም ዓይነት ነው፤ ክምችቱ ለአንድ ቀን ብቻ ሲሆን ‘ኦ' የተባለው የደም ዓይነትም በዛ ቢባል ለ2 ቀናት የሚሆን ክምችት ነው ያለው "

ያንብቡ : https://telegra.ph/EPA-04-19-2

#EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሀገራችን በተለይ በአዲስ አበባ እጅግ በጣም ሙስና ስር ከሰደደበት አንዱ የመሬት ዝውውር ጉዳይ ነው። በዚህ ሂደት አንዳንድ የአስተዳደሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ደላላ ሆነው የተገኙበት ጊዜ መኖሩ ተጠቁሟል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ " " በመሬት ጉዳይ…
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ከመሬት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ከተናግሩት ፦

" ... በአዲስ አበባ ከተማ በእጅ መንሻ፣ በዝምድናና በተለያዩ ህገወጥ አካሄዶች ጉዳዮቻቸው #በፍጥነት የሚፈጸምላቸው ሰዎች አሉ። በአንጻሩ ደግሞ ህግን ተከትሎ የሚመጣው ደንበኛ ሲንገላታ ይስተዋላል። ችግሩ በተለይ በክ/ከተሞችና ወረዳዎች ላይ ሰፊውን ህዝብ ለእንግልት እየዳረገው ነው። በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ አፋጣኝ ማስተካከያዎችን እየወሰደ ይገኛል። "

#EPA

@tikvahethiopia
🤔

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃደኛ አለመሆን የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማጣራት እያደረግኩት ባለው ጥረት ላይ እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ማስታወቁን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስነብቧል።

የቢሮ ኃላፊ አቶ አሥራት አዳሮ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፦

" በክልሉ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ #ባለሙያዎችንና #ኃላፊዎችን የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን በመያዝ ትምህርታቸውን ባጠናቀቁበት ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ በመሄድ ማስረጃዎቹ ሐሰተኛ ናቸው ወይስ አይደሉም የሚለውን ለማጣራት ሙከራ ብናደርግም የግል ትምህርት ተቋማት ፈቃደኞች አይደሉም፡፡

ከ5 እና 6 ወር በኋላ ተመልሳችሁ ኑ የሚል ምላሽ ስለሚሰጡን ወደ ትምህርት ተቋማቱ የምንልካቸው ባለሙያዎች ለእንግልት እየተዳረጉ ነው።

ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የትምህርት ጥራትን ከመጉዳትም ባሻገር የተማረ የሰው ኃይል በተፈለገው ቦታ ላይ እንዳይሠራና ጥራት ያለው አገልግሎት ለኅብረተሰቡ እንዳይሰጥ የሚያደርግ ነው።

በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተቀጥረው በሥራ ላይ በሚገኙ #አመራርና #ባለሙያዎች ሕዝቡ ትክክለኛ አገልግሎት እንዳያገኝ ሲያደርጉ ነበር ፤ ክልሉ የሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የትምህርት መረጃን አጣርቶ በሚያገኘው ውጤት መሠረት ከሥራ እና ከደመወዝ ከማገድ ባሻገር በሕግ እንዲጠየቁ ይደረጋል።

የማጣራቱን ውጤት ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ6ቱም ዞኖች የተጠቃለሉ መረጃዎችን በማደራጀት ምን ያህል አመራርና ባለሙያ በሐሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ተቀጥሮ ሲሠራ እንደነበር ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል።  "

#EPA

@tikvahethiopia
#MoE

106 ሺህ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ የትምህርት ፕሮግራም ተካተዋል፡፡

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው #ከ50_በመቶ በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለአራት ወራት ያህል በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ይሳተፋሉ፡፡

#Remedial ፕሮግራሙ ከአ/አ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እና ፕሮፌሰሮች ኮሚቴ በማዋቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉት የትምህርት አይነት ይዘቶችን መለየቱን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዘኛ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ሂሳብ የትምህርት አይነቶችን የሚወስዱ ሲሆን፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ እንግሊዘኛ፣ ማህበራዊ ሳይንስና ሂሳብ ትምህርት አይነቶችን እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ይዘቶቹን መሰረት አድርጎ በተቋማት የሚዘጋጅ (ከ30 በመቶ) እና በማዕከል የሚዘጋጅ (ከ70 በመቶ) የሚያዝ ፈተና በመፈተን በድምሩ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚያገኙ ተማሪዎች መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል ይችላሉ ብለዋል፡፡ #EPA

More : @tikvahuniversity
የሰራዊቱ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ እየተቀየረ መሆኑ ተነግሯል።

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አዲስ የተሸከርካሪ ሰሌዳ በማዘጋጀት በአገልግሎት ላይ እያዋለ መሆኑን አሳውቋል።

ሰራዊቱ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረውን የተሸከርካሪ ሰሌዳ በአዲስ ሠሌዳ የቀየረ ሲሆን ከነሃሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተሸከርካሪዎች ላይ በመለጠፍ አገልግሎት መጀመሩ ተገልጿል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሁሉም የተቋሙ ተሸከርካሪዎች አዲስ ሰሌዳ እንደሚደርስ ይፋ ሆናል።

የሰሌዳ / ታርጋ ቅያሪ የተደረገው በተለያየ ምክንያት የተቋሙ በርካታ ሰሌዳዎች ከተቋሙ እውቅና ወጪ በሌሎች እጅ በመገኘቱ ነው ተብሏል።

በመሆንም እነዚህ ከተቋሙ እውቅና ውጭ በሌሎች እጅ የገቡ ሰሌዳዎች ለህገ-ወጥ ተግባር እንዳይውሉ ለመከላከል ታሳቢ ተደርጎ ሰሌዳው መቀሩን ሚኒስቴሩ አስረድቷል።

የተቀየሩት ሰሌዳዎች የሠራዊቱን ተልዕኮ እና ግዳጅ መነሻ አድርጎ በሚሰጡት አገልግሎት መሰረት #በኮድ ተለይተው የተዘጋጁ ናቸው ተብሏል። #EPA

@tikvahethiopia
#ICS

የሕዝብ ተ/ም/ቤት የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን የ9 ወር አፈጻጸም ትላንት ገምግሟል።

ኮሚቴው ከዚህ ግምገማ በፊት ማለትም ሚያዚያ 3/2016 ላይ #ድንገተኛ ምልከታ አድርጎ ነበር።

ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ?

- ምንም እንኳ የተጀመሩ ሥራዎች ጥሩና ተስፋ ሰጪ ቢሆኑም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን እና የተገልጋይን ቅሬታ መፍታት አልተቻለም።

- ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት ብለው በሚደርስባቸው እንግልትና ስቃይ ምክንያት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ በድንገተኛ ምልከታ መመልከት ተችሏል።

- በዋና መ/ ቤቱ ተገልጋይ በተቋሙ ሠራተኞች ፦
➡️ #መሰደብ
➡️ #መመናጨቅ
➡️ #መገፍተር_ጭምር የሚደርስበት በመሆኑ ተገልጋይ በሥነ ምግባር መስተናገድ አለበት።

- በአዲስ አበባ " ካሳንቺስ አካባቢ " የሚገኘዉ የውጪ ዜጎች አገልግሎት ተቋም የሚሰጠው አገልግሎት ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ምቹ ያልሆነ እና የንጽህና ጉድለት ያለው ነው። ይህ መታረም አለበት።

- ዋናው መስሪያ ቤት ለአገልግሎት ምቹ ያልሆነ፣ ሕንፃው የቆየ እና አስፈላጊዉን የማሻሻያ ጥገና ያላገኘ ነው። ሕንፃው ከተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ባህሪ ጋር የማይጣጣም ስሪት ያለው ነው።

- በዋና መስሪያ ቤት ያለው መጨናነቅ እንዲቀንስ በአዲስ አበባ ከተማ ከአምስት ያላነሱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች እንዲከፈቱ የመፍትሔ ሃሳብ ቢሰጥም አልተፈጸመም። በተለይ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የማስፋፋት ሥራዎች መሠራት አለበት።

- የደላላ ሰንሰለት በመለየት ማቋረጥ ያስፈልጋል።

- አሁንም ከደላሎች ጋር የሚመሳጠሩ የተቋሙ #ሠራተኞች በመኖራቸው ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት።

- የሠራተኛ ባጅ አለመኖሩም ሊታሰብበት ይገባል።

በምክር ቤቱ የተገኙት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/EPA-04-27-2 #EPA

@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹

" ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በቅርበት ትከታተላለች አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ተገቢውን ምላሽ ትሰጣለች " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ፥ " የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለጎረቤት ሀገራት ልዩ ትኩረት ይሰጣል " ሲሉ ጠቁመዋል።

" ኢትዮጵያ መርህን መሠረት ያደረገ በበጎ መንፈስ የተቃኘ ዘላቂ ዲፕሎማሲ ላይ አተኩራ ትሰራለች "ም ብለዋል።

" የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ የሚደረግ እንቅስቃሴም ሊቆም ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በቅርበት እንደምትከታተልና አስፈላጊ በሆነበት ጊዜም ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጥ ገልፀዋል።

አምባሳደር ነቢያት ፥
➡️ ከአውሮፓ ህብረት፣
➡️ ከአሜሪካ
➡️ ከተመድ ልዩ መልዕክተኞች ጋር ውይይቶች መካሄዳቸውን ጠቁመዋል።

" ለሁሉም መልዕክተኞች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ሆኖ የኢኮኖሚ ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል " ብለዋል። #EPA

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ🚨

" ሰሞኑን የተከሰተው ጉንፋን መሰል በሽታ ለመከላከል ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት " - የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ

ሰሞኑን በስፋት የሚስተዋለውን ጉንፋን መሰል በሽታ ለመከላከል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡

ቢሮ ለኢፕድ እንደገለጸው " ከሰሞኑ በስፋት የተከሰተው የጉንፋን በሽታ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነው " ብሏል።

በሽታውን ለመከላከልና እንዳይስፋፋ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ሲልም አሳስቧል።

የተከሰተው ጉንፋን መሰል በሽታ በዋነኝነት በተለይ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረሶች አማካኝነት የሚከሰት መሆኑን ገልጾ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም ፦
- አፍንጫን፣
- ጉሮሮን
- የአየር መተላለፊያ ባንቧን እንደሚያጠቃ ቢሮው አመልክቷል።

ከወቅታዊው የቅዝቃዜና ደረቅ የአየር ፀባይ ጋር ተያይዞ ለቫይረሶች ምቹ የመራቢያ ወቅት በመሆኑ በስፋት የሚሰራጭ መሆኑ ተጠቅሷል።

ትምህርት ቤቶችና ክረምቱን ተከትሎ የሚዘጉ የሥራ ተቋማት በመከፈታቸው የሰዎች ግንኙነት ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ ስርጭቱ የጨመረ መሆኑ ተመላክቷል።

° ሳል፣
° ትኩሳት፣
° ራስ ምታት፣
° ጉሮሮን መከርከር፣
° ማስነጠስ፣
° የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣
° ከፍተኛ ድካም፣
° ብርድ ብርድ ማለት፣
° የትንፋሽ ማጠር እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ምልክቶች ናቸዉ ተብሏል።

ቫይረሱ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በቫይረሱ የተጠቃ ግለሰብ በሚያስልበት እና በሚያስነጥስበት ጊዜ ከሚወጡ ጠብታዎች  ጋር ንክኪ፣ ቫይረሱ ያረፈበትን ቁሳቁስ ንክኪ ማድረግ ዋነኛ መተላለፊያ መንገዶች ናቸው።

በመሆኑም ፦
🔴 የእጅና የቁሳቁስ ንጽህናን በመጠበቅ፣
🔴 ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል በማድረግ፣
🔴 ስፖርታዊ እንቅስቃዜን ማዘወትር፣
🔴 መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር ማድረግ
🔴 በቂ የጸሀይ ብርሀን ማግኘትና አትክልትና ፍራፍሬ በመመገብ በሽታውን መከላከል እንደሚገባ ቢሮው ገልጿል።

በሽታው በሁሉም ሰው ላይ የሚከሰት ቢሆንም በተለይም እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት፣ አዛውንቶችና እና ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ የሚጠነክር በመሆኑም በትኩረት መከላከልና ከተያዙ አስፈላጊው ክትትልና የህክምና ድጋፍ ሊያገኙ ይገባል ሲል አሳስቧል።

በመከላከያ መንገዶች ላይ ትኩረት ማድረግ በሽታውን ከመከላከል ጀምሮ በህመሙ ከተያዙ በቤት ውስጥ ከሚደረጉ ክትትሎች እና ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማግኘት ይገባል ተብሏል።

#EPA

@tikvahethiopia