TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮጵያ ለግብፅ ጫና ትንበረከክ እንደሁ ይለያል!

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሀ አሞላል ላይ ከነገ እሁድ መስከረም 4 2012 አ.ም ጀምሮ እስከ ሰኞ ድረስ የግብጽ ; የሱዳንና የኢትዮጵያ ውሀ ሚኒስትሮች በካይሮ ይወያያሉ።የኢትዮጵያ የውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለም ለዚሁ ጉዳይ ወደ ካይሮ የሚያቀኑ ይሆናል። ሱዳንም አዲስ ባገኘችው የውሀ ሚኒስትር ያሲር አባስ መሀመድ ተወክላ የኢትዮጵያን ጨምሮ ከግብጹ የውሀ እና መስኖ ሚኒስትር መሀመድ አብደል አቲ ጋር ነው ውይይቱ የሚደረገው።

የካይሮው ስብሰባ ምናልባትም በህዳሴው ግድብ የውሀ አሞላል ላይ የስምምነት ፊርማ ሊካተትበት እንደሚችል ምንጮቻችን ነግረውናል።ሆኖም ኢትዮጵያን የወከሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ቢቻል በግድቡ ውሀ አሞላል ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብር አዲስ ሀሳብ ቢያቀርቡ ካልሆነ ደግሞ አሁን ለውይይት የተያዘው አጀንዳ ላይ በፍጹም ከስምምነት መድረስ የለባቸውምም ብለውናል።

ነገ በካይሮ በህዳሴው ግድብ ውሀ አሞላል ላይ ውይይት የሚደረገው የግብጹ የውሀ ሚኒስትር መሀመድ አብደል አቲ ከወር በፊት የሀገራቸውን እቅድ ካቀረቡ በሁዋላ ነው። አብደል አቲ በዚህ ባቀረቡት ሰነድ ውስጥ ኢትዮጵያ ግድቡን በሰባት አመት እንድትሞላ የሚጠይቅና ሌሎች ሀሳቦችም የተነሱበት ነው። በኢትዮጵያ በኩልም እነዚህ የካይሮ ፍላጎቶች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን የሚያሳዩ ምላሾች ተሰጥቷቸዋል። እነዚህ በእንዲህ እያሉ ነው የነገው የሶስትዮሽ ውይይት የሚካሄደው።

#ዋዜማ_ሬድዮ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-14-8