TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጤፍ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስለ #ጤፍ ...

" አጠቃላይ የኑሮ ውድነቱን በተመለከተ የኛን መስሪያ ቤት #አይመለከትም " - ወ/ሮ በላይነሽ ረጋሳ (የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር)

🗣 ወ/ሮ አረጉ ጥፍጤ፦

" የጤፍ ዋጋ በጣም ጨምሯል፤ በወፍጮ ቤቶች ጤፍ የለም። በአንዳንድ ወፍጮ ቤቶች ቢገኝም እንደጤፉ ዓይነት እስከ 8 ሺ 500 መቶ ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።

25 ኪሎ ጤፍ በሁለት ሺህ ብር ገዝቻለሁ ነገር ግን ዋጋው በዚህ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ጤፍ ገዝቼ እንጀራ የምበላ አይመስለኝም።

በዜህ ዋጋ ለመግዛት እንኳን ምርቱን ማግኘት አልተቻለም ፤ ስለሆነ መንግሥት ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ ሊያየው ይገባል። "

🗣 አቶ መሀመድ ጀማል ፦

" በገበያው ላይ በቂ ጤፍ ባለመኖሩ ኅብረተሰቡ ሳያልቅ እንግዛ እየተባባለ ነው።

በወፍጮ ቤት ተቀጥሬ መስራት ከጀመርኩ አምስት ዓመት አልፎኛል። ነገር ግን የጤፍ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ምክንያት ቤተሰቤን ለማስተዳደር እንደዚህ የተቸገርኩበት ወቅት የለም።

ይህ ጉዳይ ሥር ሳይሰድ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተወካዮች ችግሩን በአስቸኳይ ሊፈቱት ይገባል።

🗣 አቶ አብርሃም ዳኜ ፦

" ኅብረተሰቡ ለዕለት ፍጆታ የሚውሉ ምርቶችን በአቅራቢያው በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያገኝ ይገባል፤ እየታየ ያለው የገበያ ዋጋ ግን የሚቀመስ አልሆነም።

በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማኅበረሰብ የዋጋ ጭማሪውን መቋቋም አልቻለም።

የዋጋ ጭማሪ ለዕለት ተዕለት በሚውሉ ምርቶች ላይ መደረግ የለበትም። የአገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን መሠረት ያደረገ አይደለም።

መንግሥት ለዕለት ተዕለት ፍጆታዎች የዋጋ ተመን አውጥቶ ሕግ የሚተላለፉ አካላት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል። "

🗣 በልደታ ክ/ከተማ የወፍጮ ቤት ባለቤት አቶ ሰለሞን ባይሳ (ስማቸው የተቀየረ) ፦

" የጤፍ አቅርቦት ችግር እና የዋጋ ጭማሪው ከኅብረተሰቡ ጋር ያለመተማመን ሁኔታ ውስጥ ከቶኛል። ወፍጮ ቤቴን ለአራት ቀን አልከፈትኩም።

ለኅብረተሰቡ የምሸጠው ጤፍ ስለሌለ ኅብረተሰቡ ጤፍ የደበቅኩ እየመሰለው ነው። ስለሆነም ከኅብረተሰቡ ጋር ላለመጋጨት ጥቂት ጤፍ ያላቸው ነጋዴዎችን ተለማምጬ ለኅብረተሰቡ ጤፍ አምጥቻለሁ።

የኅብረተሰቡ አቅም እና የገበያው ሁኔታም የሚጣጣም አይደለም። ስለዚህ መንግሥት ጉዳዩን በትኩረት ሊያስብበት ይገባል። "

🗣 የእህል በረንዳ ነጋዴ የሆኑት አቶ አማን ይሁን (ስማቸው የተቀየረ) ፦

" መንግሥት የንግድ ዘርፉን እንዲቆጣጠሩ ኃላፊነት የሰጣቸውን አካላት በዘርፉ ምን እየሠሩ እንደሆነ መመርመር ያለበት ሲሆን በኬላዎች አካባቢ እየተሠራ ያለውን ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ከሥር ነቅሎ ማጥፋት አለበት።

ወቅቱ ከፍተኛ ምርት ያለበት እና ኢትዮጵያ ሰላም የሆነችበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅት በተለየ ሁኔታ የእህል ዋጋ እንደ ሰማይ እየራቀ በመምጣቱ ዜጎችን ይበልጥ እያስጨነቀ ነው።

ስለሆነም ይህንን ጉዳይ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ መፍታት አለበት።

🗣 የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ ረጋሳ ፦

" አጠቃላይ የኑሮ ውድነቱን በተመለከተ የኛን መስሪያ ቤት #አይመለከትም። ጉዳዩ ዘርፈ ብዙ ተዋንያን ያሉት ነው።

ዋጋ ባልወጣበት ነገር ላይ ኃላፊነት መውሰድ አይቻልም።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሁን ለተፈጠረው የጤፍ ዋጋ ኃላፊነት 'ማንዴት' የለውም። የንግድ ሥርዓቱን በተመለከተ አጥንተን በቀጣይ ምላሽ የምንሰጥበት ይሆናል።

🗣 የአዲስአበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ፦

" በከተማ አስተዳደሩ በኩል ግብረኃይል ተቋቁሟል የተደረሰበትን በቀጣይ እናሳውቃለን "

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
#ሩስያ

ሩስያ ላልተወሰነ ጊዜ ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ወደ ውጭ መላክ አቆመች ፤ ይህ ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅእኖ ይኖራል ተብሎ ተሰግቷል።

ሩስያ ፤ " የሀገር ውስጥ ገበያን ለማረጋጋት እንዲሁም የሀገር ውስጥ የነዳጅ ፍላጎትን ለማሻሻል " በሚል ከአራት የቀድሞ የሶቪየት ሕብረት አባላት ውጭ ወደ #ሁሉም_ሀገራት የነዳጅ ምርቶችን ቤንዚን እና ናፍጣ መላክን ለጊዜው አግዳለች።

እገዳው ፦
- ቤላሩስ ፣
- ካዛኪስታን ፣
- አርሜኒያ እና ኪርጊስታን #አይመለከትም ተብሏል።

እገዳው " ጊዜያዊ ነው " የተባለ ሲሆን እስከመቼ እንደሚቆይ ሩስያ ያለችው ነገር የለም።

ሩሲያ ወደ ውጭ የምትልከው የናፍጣ ነዳጅ በቀን ወደ 900,000 በርሜል እንደሚገመት እና ሀገሪቱ በየቀኑ ከ60,000 እስከ 100,000 በርሜል ቤንዚን ወደ ውጭ እንደምትልክ የመንግስት የዜና ወኪሉ " ታስ " ዘግቧል።

የሩስያ የነዳጅ እገዳን ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅእኖ ሊያሳድር እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ስለ ትውልዱ ግድ ይለናል የምትሉ ኃላፊዎች መፍትሄ ስጡን " - ተማሪዎቹ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፤ " መፍትሄ የሚሰጠን አጥተን ያለ ትምህርት ቤታችን ቁጭ ብለናል ፤ ጊዜያችንም እየተቃጠለ ነው " ሲሉ አማረዋል። የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ የ2016 ዓ/ም የ1ኛ ዓመት እና የሬሚድያል ተማሪዎች ወደ ግቢ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጎላቸው በኃላም መራዘሙ ይታወሳል። ነገር ግን እስካሁን ምንም አይነት ጥሪ…
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተከታተሉ ተማሪዎች ጥሪ አደረገ።

በዚህም በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ Freshman ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስትከታትለው ቆይተው የማለፊያ ውጤት በማምጣት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደበ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ከመጋቢት 26 እስከ 28/2016 ዓ.ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታውም ፦
➤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሰላም ግቢ
➤ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በግሽ አባይ ግቢ ነው ተብሏል።

በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን አቋርጠው ለአንደኛ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላቸውና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞሉ ተማሪዎች ምዝገባ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ያወጣው ጥሪ በማካካሻ መርሐ ግብር (Remedial Program) በ2016 ዓ/ም አዲስ የተመደቤ ተማሪዎችን #አይመለከትም ተብሏል።

Via @tikvahuniversity