TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

ሮይተርስ ባወጣው የምርመራ ሪፖርት " በሺሕዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች፣ ያለፍርድ በጊዜያዊ እስር ቤቶች ተይዘው ይገኛሉ " ብሏል።

እንደ ምርመራ ሪፖርቱ በአሁኑ ወቅት ላይ 9‚000 የሚኾኑ ተወላጆች በእስር ቤቶቹ ሲገኙ፣ ቢያንስ 17 እስረኞች ለኅልፈት ተዳርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የሚካሔደው ጦርነት 19 ወራትን በአስቆጠረበት ኹኔታ፣ 3‚000 የሚሆኑ እስረኞች፣ በሚዛን ተፈሪ ከተማ በሚገኙና በእጅጉ በቆሸሹ 18 የእስር ቤት ክፍሎች ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ ብሏል ሪፖርቱ።

በተመድ (UN) እንደተገመተው መንግሥት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ ከኅዳር እስከ የካቲት ባሉት ወራት 15,000 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች ተይዘዋል።

ሮይተርስ ምርመራ ሪፖርት በበኩሉ ከ17 የቀድሞ እስረኞች እና በሳተላይት ፎቶ ተደግፎ ባደረገው ማጣራት፣ ያለፍርድ ተይዘዋል ያላቸው እስረኞች ብዛት ተመድ ከሚገምተው ቢያንስ በ3‚000 እንደሚበልጥ ተመልክቷል።

ሪፖርቱ ፤ መንግሥት አብዛኞቹ እስረኞች ተለቀዋል ቢልም 9,000 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች አሁንም ታስረው ይገኛሉ።

አብዛኞቹ የእስር ቦታዎች ለሌላ ተግባር የተሠሩ፣ ጠባብና የቆሸሹ ናቸው ይላል የምርመራው ሪፖርት ። ሪፖርቱ በመቀጠል የእስረኞቹ አያያዝም ዓለም አቀፍ ሥርዓትን ያልተከተለ ነው ብሏል።

ያንብቡ

#አማርኛhttps://telegra.ph/Reuters-Amh-06-18

#እንግሊዘኛhttps://www.reuters.com/investigates/special-report/ethiopia-conflict-prisoners/

@tikvahethiopia
#Amaharic #Russia

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በሞስኮ የሚገኙ ት/ቤቶች የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማስተማር ይጀምራሉ ተባለ።

በዚህም የአማርኛ ቋንቋ አንዱ ሆኖ ይሰጣል።

የሞስኮ ትምህርትና ሳይንስ ክፍልን ዋቢ በማድረግ ስፑትኒክ እንደዘገበው ፤ ሩሲያ ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ #አማርኛ እና #ስህዋህሊ ቋንቋዎችን በሞስኮ በሚገኙ በአራት ት/ቤቶች ማስተማር እንደምትጀምር ባሳወቀችው መሰረት ትምህርቱ መሰጠት ይጀምራል።

እንደ ዘገባው ከሆነ " 1517 " የተሰኘው የፔዳጎጂ ትምህርት ቤት ስዋህሊ ቋንቋን ሁለተኛው የውጭ ቋንቋ አድርጎ ያስተምራል።

" 1522 " የተሰኘው ትምህርት ቤት ደግሞ አማርኛ ቋንቋን እንደሚያስተምር ተገልጿል።

ሩሲያ የአፍሪካ እና ሞስኮን ወዳጅነት ለማጠናከር በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብላለች።

ሩሲያ በቀጣይ በምዕራብ አፍሪካ ሰፊ ተናጋሪ ያለው ዩርባ ቋንቋን ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻለች።

በመቀጥልም #ሶማልኛ እና የዙሉ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው።

ሌላኛዋ ሀገር ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ማስተማር እንደምትጀምር ከዚህ ቀደም መግለጿ ይታወቃል።

አማርኛ ቋንቋ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ሆኖ ይሰጣል ተብሏል።

መረጃው የ #አልዓይን (ስፑትኒክ) ነው።

ስፑትኒክ አፍሪካ ፦ https://www.facebook.com/100091796831512/posts/pfbid02Zf2NYdkBuBFDA8UDxBbtf5ZBGbRVPjYGUWzgeLVL365qBrKQgthGS622GJqo2PNul/?app=fbl

@tikvahethiopia