TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " በጦርነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ አምራች አርሶ አደሮች፣ ሃኪሞችን ጨምሮ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰውተዋል " - ጊዜያዊ አስተዳደሩ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በትግራዩ ደም አፋሳሽ ጦርነት ስለ ተሰው ታጋዮች " እንደ ተራ ነገር የሚነገረው ቁጥር የሃቅ መሰረት ስለሌለው ትርጉም አንሰጠውም " አሉ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ።…
" ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል " - ቅዱስነታቸው
ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በትግራይ ክልል በተካሔደው ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች እየተከናወነ ያለውን የኀዘን ሥነ ሥርዓት በማስመለክት አባታዊ የማጽናኛ መልእክት አስተላለፉ።
ከቅዱስነታቸው መልዕክት የተወሰደ ፦
" ዛሬ በትግራይ ክልል እየተዘከሩ ስላሉ ወገኖች በእጅጉ ማዘናችንን እንገልጣለን ።
ይህ እንዳይመጣ ብዙ ተማጽኖ ስናቀርብ የነበረ ቢሆንም ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል።
ዛሬ በትግራይ ክልል የማይለቀስበት ቤት የለም። የተሰዉት ልጆቻችን በሕይወተ ሥጋ ኖረው ቢሆን ብዙ ታሪክ መሥራት ይችሉ የነበረ ቢሆንም እነዚህ የቤተሰብና የቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የሀገር ተስፋዎች በእሸት በመቅረታቸው በኀዘን በተሰበረ ልብ ሁነን ለነፍሳቸው ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንዲሰጥልን እንጸልያለን።
በኀዘን የተጎዳችሁ አባቶችና እናቶችም ይህ ቢሆን ኖሮ እያላችሁ ራሳችሁን እንዳትጎዱ፤ የእናንተ መጎሳቆል የሞቱትን ቀና አያደርግምና ልባችሁን እንድታበረቱ እናሳስባለን ምክንያቱም መቃብር መጨረሻችን ያልሆነ የትንሣኤ ሕዝብ ነን፡፡
በምድር ላይ ስንኖር ማንም ለራሱ መከራን አያቅድምና የታቀዱ ቀኖችንም ለማለፍ ሕገ ተፈጥሮ አይፈቅድልንምና በሆነውና በሚሆነው ነገር ሁሉ ' እንደ ፈቃድህ ይሁን ' እያሉ ልብን ማሳረፍ ይገባል በማለት እንመክራለን፡፡ "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia