#ሲፌፓ
ሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።
አሁን ሀገር ካለችበት ሁኔታና ከተደቀነባት ፈተና ችግር አንፃር የተወሰኑ አስቻይ ሁኔታዎች ተፈጥሮ ሀገራዊ ምክክር ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ገልጿል።
ፓርቲው ፤ በየአከባቢው የሚደረጉ ጦርነቶችና ግጭቶች ቆመው ችግሮች በምክክርና በውይይት ብቻ መፈታት እንዳለበት አቋም መያዙን አሳውቋል።
ለዚህም የራሱን አስተዋፅዖ ለማድረግ ከውሳኔ ላይ መድረሱን ገልጿል።
በተጨማሪ የሲዳማን ህዝብ ፍላጎት በመወከል በሀገራዊ ምክክር መድረክ ላይ የሚሳተፍ ጠንካራ ፖለቲካ ፓርቲ የለም ያለው ሲፌፓ " በምክክር ሂደቱ ውስጥ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የህዝቡን ፍላጎት ማንፀባረቅ እንዳለብን አምንናል " ሲል አሳውቋል።
በመሆኑንም ፓርቲው በምክክር ሂደት ላይ ከወረዳ አንስቶ እስከ ሀገር ድረስ በበቂ ሁኔታ መሳተፍ የሚችልበት አግባብና በተለያዩ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በመነጋገር መስከረም 29/01/2016 ከኮሚሽኑ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊዉ አቶ ገነነ ሀሳና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት መረጃ እንደገለጹት ስምምነቱ በርካታ ችግሮችን ለመቅረፍና የንግግርና የዉይይት መድረክ በመክፈት ክልላዊም ሆነ ሀገራዊ ክፍተቶችን ለማስተካከል እንደሚረዳ አመልክተዋል።
ስምምነቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ በሲዳማ ክልል በሚያደርገዉ የዉይይት መድረክ የበኩሉን ለማበርከት በወረዳ በዞን እንዲሁም ክልል ደረጃ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia