TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" 3 የኤጀንሲው ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል "

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ 3 የኤጀንሲው ሰራተኞች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን አስታወቀ።

ኤጀንሲው ፤ የህትመት ስርጭት እና አጠቃቀም ላይ መደበኛ የኦዲት ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጾ በዚህም በተገኘው ግኝት የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ  ጽ/ቤት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና ማስረጃ ቡድን #መሪ እና 2 ባለሙያዎች በሰሩት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ሲል ገልጿል።

ኤጀንሲው የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት በደረሰው ጥቆማ ላይ ተመስርቶ ባሰባሰበው ማስረጃ ፦

- ለወረዳው ፈቃድ ሳይሰጥ የውጭ ዜጎችን #ገንዘብ_በመቀበል ጋብቻ በመፈፀም፣

- ባልተሟላ ማስረጃ የልደት ምዝገባ በማከናወን እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያዎችዎቹ ተጠርጥረው ከስራ እንዲታገዱ በማድረግ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድ አድርጓል ብሏል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ኤጀንሲው ፤ #በለሚ_ኩራ ክ/ከተማ  ወረዳ 13 ጽህፈት ቤት 1 ቡድን መሪ እና ባለሙያዎች በወንጀል ጉዳዮቸው እየታየ መሆኑ አስታውሷል።

ነዋሪዎች የትኛውንም ዓይነት ቅሬታ ፣ ጥቆማ ወይም መረጃ ለመስጠት የኤጀንሲውን ነፃ የስልክ መስመር 7533 መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia