TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

" ምክክሩ በመንግሥትም ሆነ በሌላ የውጭ አካላት እንዲጠመዘዝና እንዲመራ አንፈቅድም " - ፕ/ር መስፍን አርአያ

ብዙዎች ከምንም በላይ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ያመጣል ብለው ተስፋ የጣሉበት አገራዊ የምክክር መድረኮች በቀጣይ ዓመት ሕዳር ወር እንደሚጀምሩ ይፋ ሆኗል።

አገራዊ የምክክር መድረኮች ሕዳር ወር (2015 ዓ/ም) እንደሚጀመሩ ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ናቸው።

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ አገራዊ ምክክሩ የቅድመ-ዝግጅት ፣ ዝግጅት፣ ምክክር እንዲሁም የትግበራና ክትትል የተሰኙ 4 ምዕራፎች እንዳሉት ጠቁመዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች መካከል ዋነኛ የሆነው የእቅድ ሥራ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ተጠናቆ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይትና ግምገማ እንደሚደረግበት ገልፀዋል።

የዝግጅት ምዕራፎች ደግሞ የተሳታፊ ልየታና ሥልጠና እንዲሁም ለአገራዊ መግባባት የተሻሉ አጀንዳዎችን መለየት የሚሉ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተያዘው ክረምት የዝግጅት ምዕራፎች ተጠናቀው በመጭው ዓመት ህዳር ወር ላይ የምክክር መድረኮች እንደሚጀመሩ ነው ይፋ ያደረጉት።

ፕ/ር መስፍን የውይይት አጀንዳ የሚቀረጸው ከታችኛው ኅብረተሰብ ክፍል ፍላጎት እንደሆነ ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ #ገለልተኛ_የሕዝብ_ወኪሎች በተገቢው መልኩ ይለያሉ ብለዋል።

" ምክክሩ በመንግሥትም ሆነ በሌላ የውጭ አካላት እንዲጠመዘዝና እንዲመራ አንፈቅድም " ያሉት ፕሮፌሰር ማስፍን " #ከውስጥና #ከውጭ ያሉ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ምክክሩ ግቡን እንዲመታ እንሰራለን " ብለዋል።

ምንጭ፦ telegra.ph/ENA-05-14

@tikvahethiopia