TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የ2016 ዓ/ም የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ እየተከበረ ይገኛል።

#TikvahFamilyBishoftu / #ENA

@tikvahethiopia
" ለባለቤቷ ለቅሶ የተቀመጠችው በዚሁ አደጋ ወላጅ እናቷንም አጥታለች " - የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

ትላንት በአዲስ አበባ ሸጎሌ አካባቢ አንድ የከተማ አውቶብስ ለለቅሶ የተጣለ ድንኳን ጥሶ በመግባት ባደረሰው ጉዳት የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋው ከምሽቱ 1 ሰዓት የደረሰ ሲሆን በአደጋውን እስከ ትናንት ምሽት ድረስ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ20 በላይ ሰዎች ላይም ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በአደጋው ጉዳት  ከደረሰባቸው ተጎጂዎች መካከል የተወሰኑትን የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቅድመ ሆስፒታልና አምቡላንስ አገልግሎት ባለሞያዎች ሕክምና እያደረጉላቸው ወደ-ሆስፒታል አድርሰዋቸዋል።

የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፤ በድንኳን ውስጥ ለባለቤቷ ለቅሶ የተቀመጠችው በዚሁ አደጋ ወላጅ እናቷንም አጥታለች ሲል ገልጿል።

ህይወታቸውን ያጡትና ጉዳት የደረሰባቸውም ሀዘንተኛዋን ለማጽናናት በድንኳን ውስጥ የተቀመጡ ናቸው ብሏል።

ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል በአስጊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ያሉ ሲሆን ተጎጂዎቹ በአቤትና በራስ ደስታ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

መረጃው የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው።

@tikvahethiopia
#Update #MoE #Result

ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል።

ሚኒስቴሩ ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ጀምሮ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በተመለከተ በሚኒስቴሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል ተፈርሞ ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ደብዳቤ ተልኳል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ (@tikvahuniversity) ለመገናኛ ብዙሃን የተላከውን ደብዳቤ ትክክለኛነት #አረጋግጧል

በሐምሌ 2015 ዓ.ም መጨረሻ በሁለት ዙር የተሰጠውን የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ 840 ሺህ በላይ ተፈታኞች መውሰዳቸው ይታወሳል።

More Tikvah Ethiopia University 👇
https://t.iss.one/+RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #MoE #Result ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል። ሚኒስቴሩ ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ጀምሮ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በተመለከተ በሚኒስቴሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል ተፈርሞ ለተለያዩ…
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ  ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

@tikvahethiopia
ልገሳዎን ቀጥታ ያድርሱ!
EthioDirect
***********
በኢትዮ-ዳይሬክት ለተቸገረ ወገንዎ ወይም ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ልገሳዎን ቀጥታ ወደ ሂሳባቸው ይላኩ!
#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
=============
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም  App Store በማውረድ  አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
#SouthWestEthiopia

በአንድ ሞተር ላይ ሆነው ሲጓዙ የነበሩ 3 ሰዎች ከአይሱዙ መኪና ጋር ተጋጭተው የሁሉም ህይወት ወዲያው ማለፉ ተሰማ።

ይህ አሰቃቂ አደጋ የደረሰው ትላንት መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ/ም ልክ ከቀኑ 8:10 ላይ  በኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ " ጥሴ " ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ነው።

እንደ ፖሊስ መረጃ መነሻውን ከመንደር 11 ወደ ኮይሻ ገበያ 3 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሞተር ከኮይሻ ገበያ ወደ መንደር 11 ይጓዝ የነበረ የጭነት አይሱዚ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የሞተሩ አሽከርካሪ እና 2 ተሳፋሪዎች ወዲያውኑ ህይወታቸዉ አልፏል።

መረጃው ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን የተገኘ ነዉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

• የሞቱ እስራኤላውያን ከ700 በላይ ሆነዋል። ከ350 በላይ ፍልሥጤማውያንም ህይወታቸው ጠፍቷል።

#ኢራን ፍልስጤምን ደግፋ ስትቆም ፤ #አሜሪካ ከእስራኤል ጎን መሆኗን አረጋግጣ ወታደራዊ ድጋፍ ማድረግ እንደምትጀምር አሳውቃለች።

በእስራኤል ጦርና በፍልስጤሙ ሃማስ መካከል ጦርነቱ ዛሬም ተባብሶ መቀጠሉን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በተለይም እስራኤል ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ብርቱ ውጊያ እየተካሄደ ነው ተብሏል።

በጦርነቱ እስራኤል ውስጥ ከ700 በላይ #እስራኤላውያን መገደላቸው ተሰምቷል።

እስራኤል ተከፍቶብኛል ላለችው ጦርነት እየወሰደች ባለችው የአፀፋ እርምጃ በጋዛ ሰርጥ ከ350 በላይ #ፍልጤማውያን ተገድለዋል።

በአጠቃላይ ባለፉት ሰዓታት ብቻ እስካሁን ይፋ በተደረገው ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ተጎድተዋል።

ጋዛ ውስጥ መሰረተልማቶች ፣ ህንፃዎች እንዳልነበሩ ሆነዋል፣ የኤሌክትሪክ ፣ የነዳጅና የፍጆታ እቃዎች አቅርቦት ተቋርጧል ፤ ያለው ሁኔታ እጅግ የከፋ ነው ተብሏል። ሰብዓዊ እርዳታ የሚገባበት መንገድ እንኳን የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል የሊባኖሱ ሂዝቦላህ ከፍቶብኛል ላለችው ተኩስ በሊባኖስ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈፅማለች።

ሂዝቦላም እስራኤል ላይ ተኩስ ስለመክፈቱ ኃላፊነቱን ወስዷል።

ተኩሱ የተከፈተው እስራኤል፣ ሊባኖስ እና ሶሪያ በሚወዛገቡበት ግዛት እና ሶስቱንም ሃገራት በሚያገናኛቸው የዶቭ ተራራ አካባቢ ነው።

እስራኤል የሊባኖስ ታጣቂ ሂዝቦላህ በውጊያው ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ አስጠንቅቃለች።

ሃማስ ፤ እስራኤል በወረራ ከያዘቻቸው ግዛቶች ለመጠራረግ ፍልስጥኤማውያን እንዲሁም ሌሎች አረቦች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

እስራኤል ያለጥርጥር በበርካታ ግንባሮች ሊከፈት የሚችል ጦርነት ሊኖር እንደሚችል ነው እየታያት ያለው ተብሏል።

ምናልባትም ጦርነቱ የከፋ የሚሆነው ከፍተኛ ኃይል ያለውን የሊባኖሱን ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላ መሳብ ከቻለ እንደሆነ ተነግሯል።

በእስራኤል እና የፍልስጤም ሃማስ ጦርነት ሀገራት የተለያዩ አቋማቸውን እያንፀባረቁ ሲሆን ኢራን የሃማስን ጥቃት ደግፋ ቆማለች።

ኢራን " የፍልስጤምን ሕጋዊ የመከላከል መብት እደግፋለሁ " ብላለች።

አሜሪካ በበኩሏ ከእስራኤል ጎን እንደሆነች በተደጋጋሚ እያረጋገጠች ነው ፤ ወታደራዊ ድጋፍም ለማድረግ እየተዘጋጀች መሆኑ ተሰምቷል። የአሜሪካ መከላከያ ድጋፉን ከዛሬ ጀምሮ የሚልክ ሲሆን በመጪዎቹ ቀናት ይደርሳል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጦር ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ወታደሮቹን እያሰማራ ሲሆን በጋዛ ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን ከማድረግ በተጨማሪ የምድር ላይ ዘመቻ ለማድረግ ማቀዱን ተሰምቷል።

መረጃው ከቢቢሲ እና አልጀዚራን ጨምሮ ከሌሎች ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የተገኘ ነው።

More - @BirlikEthiopia

@tikvahethiopia
#ሐረሪ

" የሽንኩርት ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ወስደናል " - የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ

የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ ፤ " የሽንኩርት ዋጋን ያለቅጥ አንረዋል " ባላቸው የሐረር ከተማ ነጋዴዎች ላይ የእስር ዕርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

በዳቦ ነጋዴዎችም ላይ ተመሳሳይ ዕርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል።

የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ " የሽንኩርት ዋጋን ያላግባብ ያስወድዳሉ " ያላቸውን 3 ዋና ዋና ነጋዴዎችን ጨምሮ 17 የሽንኩርት አከፋፋዮችን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማድረጉን ገልጿል።

በሽንኩርት ነጋዴዎቹ ላይ ዕርምጃ ከመወሰዱ በፊት ቀደም ብሎ የማወያየት ሥራ መከናወኑን አመልክቷል።

የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፦ " ባቢሌ አካባቢ የተፈጠረውን የአንድ ቀን ግጭትና መንገድ መዘጋት ተጠቅመው በሽንኩርት ላይ የተጋነነ ዋጋ ጨመሩ፡፡

ነጋዴዎቹን ቢሮ ድረስ ጠርተን ከማወያየት ባለፈ ቦታው ድረስ ባለሙያ በመላክ ሁኔታውን ገምግመናል፡፡

በጉዳዩ ላይ በመተማመን ዋጋውን ለማስተካከል ቃል ገብተው ቢሄዱም፣ ዋጋውን ባለማስተካከላቸው ወደ ዕርምጃ ተገብቷል። " ብለዋል።

ዕርምጃ የተወሰደባቸው የሽንኩርት ነጋዴዎቹ በሐረር ከተማ ብቻ ሳይሆን፣ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎችም የማከፋፈል ሥራ የሚሠሩ ዋና ዋና ነጋዴዎች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

ከ110 ብር እስከ 150 ብር አሻቅቦ የነበረው የአንድ ኪሎ የሽንኩርት ዋጋ ከዕርምጃው በኋላ መስተካከሉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ ፤ ዳቦ ቤቶችን እና ነጋዴዎችን በቀጣይ ሳምንት በቢሮው ሰብስቦ እንደሚያነጋገር አሳውቋል።

የዳቦ ግራምና ዋጋ የሚያጭበረብሩ እንዲያስተካክሉ የአንድ ሳምንት ወይም የአሥር ቀን ገደብ ይሰጣል ብሏል።

ማስተካከያ ባላደረጉ ላይ ግን ልክ እንደ ሽንኩርት ነጋዴዎቹ ሁሉ ዕርምጃ ይወሰዳል ሲል ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

#ሽንኩርት ፦ የሽንኩርት ዋጋ በመዲናዋ ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች ዋጋው አልቀመስ ካለ ሰንበትበት ብሏል። በርካቶች በዋጋው ንረት ሸምቶ ለመግባት ማቸገራቸውን ይገልጻሉ። እርሶስ በጉዳዩ ላይ ምን ይላሉ ? በዚህ ይነጋገሩ @BirlikEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
የእስራኤልና ፍልስጤሙ ሃማስ ጦርነት በቀጣይ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ?

ዋና ነጥቦች ፦

▪️ሃማስ ፤ " ወራሪ " ናት በሚላት #እስራኤል ላይ  ወታደራዊ ኦፕሬሽን ማካሄድ መጀመሩንይህ ኦፕሬሽንም #ፍልስጤማውያን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለደረሰባቸው ግፍ ሁሉ ምላሽ እንደሆነ ገልጿል።

▪️ እስራኤል ፤ " አሸባሪ " የምትለው የሃማስ ቡድን ጥቃት መክፈቱ ከባድ ስህተት መሆኑን በመግለፅ ለእያንዳንዱ ድርጊቱ የከፋ ዋጋ እንደሚከፍልበት ፤ ለሚመጣው ነገር  ሁሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ገልጻለች። ሃማስ ላይም መጠነ ሰፊ የአፀፋ እርምጃ ጀምራለች።

▪️እስካሁን ከእስራኤል ከ700 በላይ ከፍልስጤም ከ400 በላይ ሰዎች አልቀዋል።

በእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ሀገራት እና መሪዎች አቋማቸውን እያንፀባረቁ ናቸው።

አንዳንዶቹ በግልፅ ሃማስን " የሽብር ቡድን " እንደሆነ ገልፀው ጥቃቱን ሲያወግዙ አንዳንዶቹ ደግሞ በሁለቱም በኩል ግጭት ቆመ በእርጋታ ነገሮች እንዲፈቱ እየጠየቁ ነው።

እስራኤል አጋሮቿ ሁሉ የተከፈተባትን ጥቃት በግልፅ እንዲያወግዙ ትሻለች።

በወታደራዊና ኢኮኖሚ አቅማቸው ጠንካራ የሆነ የዓለም ሀገራት ምን አቋም ነው የያዙት ?

🇺🇸አሜሪካ - የእስራኤል ወዳጇ #አሜሪካ የ ' ሃማስን ' ጥቃት የአሸባሪዎች ጥቃት ነው በማለት በግልፅ ጥቃቱን አውግዛ ለእስራኤል ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አደርጋለሁ ብላለች። ወታደራዊ ድጋፍም ልካለች።

🇫🇷ፈረንሳይ - የሃማስን ጥቃት " የአሸባሪዎች ጥቃት " ስትል ገልጻ ከእስራኤል ጎን እንዳሆነች ገልጻለች።

🇩🇪ጀርመን -ጥቃቱን አውግዛ ከእስራኤል ጎን መሆኗን ገልጻለች። ሃማስንም አሸባሪ ስትል ጠርታለች።

🇮🇳ሕንድ-እስራኤል የተፈፀመባት ጥቃት የአሸባሪዎች ጥቃት ነው ብላ ከእስራኤል ጎን መሆኗን ገልጻለች።

🇬🇧ዩናይትድ ኪንግደም - በእስራኤል ላይ " የሽብር " ጥቃት መፈፀሙን ገልጻ ሀገሪቱ እራሷን የመከላከል መብት አላት ብላለች። ከእስራኤል ጎን እንደሆነችም ገልጻለች።

_

🇮🇷ኢራን - " የፍልስጤም ህዝብ #ራሱን_የመከላከል መብት አለው " ብላ የሃማስን ጥቃት በግልፅ " አኩሪ ተግባር " ስትል አወድሳለች።  " ፍልስጤም እና እየሩሳሌም " ነፃ እስኪወጡ ከፍልሥጤም ተዋጊዎች ጎን እንቆማለን ብላለች።
_

🇨🇳ቻይና- ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት እንዲረጋጉ ፤ ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ እና ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እንዲሁም ሲቪሎች እንዲጠበቁ ፤ የሁኔታውን እንዳይባባስም እንዲሰሩ አሳስባለች።

ቤጂንግ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የቻይና አቋምን በተመለከተ እስራኤል ሃማስ ላደረሰው ጥቃት ከቻይና ጠንካራ ውግዘት ጠብቃ ነበር ብሏል።

ቻይና የሃማስ ታጣቂ ኃይልን እንደ አሸባሪ ድርጅት ሳይሆን እንደተቃዋሚ ኃይል ነው የምታየው።

🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ - ሀገሪቱ በቅርቡ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ እየተንቀሳቀሰች ሲሆን አሁን የተቀሰቀሰው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርባለች። ሁለቱም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙና ሲቪሎችም እንዲጠበቁ አሳስባለች።

🇦🇪የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) - ያለው ሁኔታ እጅግ እንዳሳሰባት በመግለፅ ግጭት እንዲቆም እና ሲቪሎች እንዲጠበቁ ስትል ጥሪ አቅርባለች።

🇹🇷ቱርክ - በእስራኤልና ፍልስጤም ሃይሎች መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ለማረጋጋት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደምታደርግ አቋሟን ገልጻለች። ለሁለቱ ሀገራት መፍትሄ ቀጣናዊ ሰላም ማስፈን ብቸኛ መንገድ ነው ብላለች። አሁን ላይ ያለው ከፍተኛ ውጥረት እንዲረግብ እንደምትሰራ ነው የገለፀችው።

🇷🇺 ሩስያ - ሩስያ በአቸኳይ #ተኩስ_እንዲቆም ጥሪ አቅርባለች።

_

አፍሪካውያን ምን አሉ ?

- የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሣ ፋኪ ማሃማት " የእሥራዔል-ፍልስጥዔም ቋሚ ውጥረት ዋናው ምክንያት የፍልስጥዔም ህዝብ መሠረታዊ መብቶቹን፣ በተለይም ነፃና ሉዓላዊ መንግሥት መነፈጉ ነው " ብለዋል። ሁለቱ ኃይሎች ግጭት አቁመው ወደ ድርድር ጠረጴዛ ይቅርቡ ብለዋል።


- የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቨኒ " በእሥራዔል እና በፍልስጤም መካከል እንዳዲስ ግጭት መቀስቀሱ የሚያሳዝን ነገር ነው። ለምን ሁለቱም ወገኖች የሁለት መንግስት መፍትሄን ተግባራዊ አያደርጉም? በተለይ ደግሞ ሰላማዊ ዜጎችን እና ተዋጊ ያልሆኑ አካላት በታጣቂዎች ዒላማ መደረጋቸው መወገዝ አለበት " ብለዋል።

- #ኬንያ በፕሬዜዳንቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ እስራኤል ላይ የተፈፀመው የሽብር ጥቃት መሆኑን በመግለፅ ከእስራኤል ጎን እንደሆነች ገልጻለች።   በተጨማሪ ግጭቱ እንዲበርድ እና እስራኤልም ፍልስጤምም ከወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ ብላለች።

የUN ፀጥታ ም/ቤት ስብሰባ በምን ተጠናቀቀ ?

ትላንትና ምሽት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በእስራኤል - ጋዛ ጦርነት በዝግ አስቸኳይ ስብሰባ ቢቀመጥም አባል ሀገራቱ መስማማት ስላልቻሉ የጋራ መግለጫቸውን ማውጣት አልቻሉም።

አሜሪካ 15ቱ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት #ሃማስን አጥብቀው እንዲያወግዙ መጠየቋ ተሰምቷል።

የአሜሪካው ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ሮበርት ዉድ ፤ " የሃማስን ጥቃት ያወገዙ ብዙ አገሮች አሉ። ሁሉም እንዳልሆኑ ግልፅ ነው " ያሉ ሲሆን " እኔ ምንም ሳልናገር ከመካከላቸው አንዱን ማወቅ ትችላላችሁ " ሲሉ ሩስያ ጥቃቱን ካላወገዙት ውስጥ እንደሆነች ተናግረዋል።

መረጃዎቹ ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የተሰባሰቡ ናቸው።

@tikvahethiopia
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ።

በእስራኤል እና በፍልስጤም ሃማስ መካከል የተቀሰቀሰው ከፍተኛ ጦርነት የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ማድረጉ ተዘግቧል።

የአንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ4 % በላይ መጨመሩ ተነግሯል።

ባለፉት ሳምንታት ወደ 96 ዶላር ደርሶ የነበረው የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ባለፉት ቀናት ጥሩ የሚባል ቅናሽ እያሳየ መጥቶ ነበር።

ነገር ግን ቅዳሜ በሃማስ እና እስራኤል መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኃላ የነዳጅ ዋጋ ዛሬ በ4.53 % ጭማሪ አሳይቶ 88.41 ዶላር መድረሱን ሲኤንቢሲ ዘግቧል።

በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴትም አንድ በርሜል ነዳጅ በ4.69% ጨምሮ ወደ 88.67 ዶላር ከፍ ብሏል።

ምንም እንኳን እስራኤል እና ፍልስጤም ነዳጅ አምራች ባይሆኑም ግጭቱ በመካከለኛ ምስራቅ ቀጠና ላይ ሰፊ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ያደርጋል ተብሎ ተሰግቷል።

ይህ ቀጠና በዓለም ላይ ከፍተኛ የነዳጅ አቅርቦት ያለበት ነው።

@tikvahethiopia
" ተፈታኞች ከሚያስቀጣ ተግባር ተቆጥባችሁ ተረጋግታችሁ ተፈተኑ " - የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ

በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል። 

ፈተናው ነገ መስከረም 29 ጀምሮ ጥቅምት 2 ይጠናቀቃል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለፈተናው አስፈላጊው ሁሉ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን በይፋ አሳውቋል።

የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ለትግራይ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ፤ በትግራይ በተካሄደው ዘግናኝና ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ፈተናው ላለፉት ሦስት ዓመታት በክልሉ እንዳልተሰጠ አስታውሰዋል።

የተካሄደው እጅግ አስከፊ ጦርነት በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጉዳት ማድረሱ የገለፁት ዶ/ር ኪሮስ፤ ተማሪዎች ከደረሰባቸው ጉዳት በማገገም ለፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ የማጠናከሪያ ትምህርትና ድጋፍ ለሁለት ወራት ያህል ተሰጥቷል ብለዋል።

በክልሉ ባሉት አራት የፌደራል መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በዝግ የተሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርትና ድጋፍ ውጤታማ ነበር ያሉት ሃላፊው  ተማሪዎቹ ባለፉት ሦስት አመታት በአገር አቀፍ ደረጃ በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ አዳዲስ ህጎች መውጣታቸው በማወቅና በመተግበር በጥንቃቄ መፈተን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ፦
- በኣክሱም ፣
- በዓዲግራት ፣
- በመቐለና በራያ ዩኒቨርስቲዎች ብቻ እንደሚሰጥ ኃላፊው አብራርተዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በያዝነው ወር የመጀመሪያ ሳምንት ለፈተና የሚያዘጋጃቸውን ቅፅ መሙላታቸውን ዶ/ር ኪሮስ በዚሁ መሰረት ከስህተት የፀዳና ከሚያስቀጣ ተግባር በመቆጠብ ተረጋግተው እንዲፈተኑ አደራ ብለዋል።

መረጃውን የትግራይ ቴሌቪዥን በመጥቀስ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ነው የላከው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቀጥታ

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በቦታው የሚገኝ ሲሆን መግለጫውን በቀጥታ ወደ ተማሪዎች እና ወላጆች ያደርሳል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia @tikvahUniversity @tikvahethmagazine