TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ላመጡት ሰላምና እርቅ ልዩ ሽልማት አበርክታለች።

©አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኦሮሞ ትግል ከየት ወዴት"...

“የኦሮሞ ትግል ከየት ወዴት” በሚል ርዕስ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው። ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዲፒ ሊቀመንበር ዶክተር #አብይ_አህመድና የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር እና የኦዲፒ ምክትል ሊቀመንበር #ለማ_መገርሳ ናቸው። በውይይቱ ላይ የኦዲፒ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ሽመልስ አብዲሳ በርዕሱ ላይ መነሻ ሐሳብ ማቅረባቸው ተገልጿል። በውይይቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ ወጣቶችና ባለሃብቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መሪዎቹ ሀዋሳ ገብተዋል...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድና የኬንያው ፕሬዚዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት እያደረጉ ነው። የሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ከተማ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ÷ ጉብኝቱ የሚካሄደው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር በማሰብ ነው ብለዋል።

Via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጁባ🛬

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይና አቶ ለማ🚁በደሌ🔝

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ከተማ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ ማለዳ ላይ ነው በደሌ ከተማ የገቡት።

በበደሌ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም ከቡኖ በደሌ ዞን ከተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁንም አድማ ላይ ናቸው...

ጠቅላይ ሚንስትር #አብይ_አህመድና የህክምና ባለሙያዎች ያሏቸውን ቅሬታዎችና የመብት ጥያቄዎች በተመለከተ ሀገር አቀፍ ውይይት ቢያደርጉም አንዳንድ የጤና ባለሙያዎቹ አሁንም ድረስ አድማ ላይ መሆናቸውን ፎርቹን አስነብቧል። ውይይቱ ውጤታማ እንዳልነበረም ዘገባው አብራርቷል። የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎችና ኢንተር ሀኪሞች አሁንም አድማ ላይ ናቸው።

Via #ፎርቹን/በዋዜማ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia