TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በአዲስ አበባ በሞተር ብስክሌት በመታገዝ የቅሚያ ወንጀል ከፈፀሙ ግለሰቦች መካከል ግማሽ ያህሉ #መያዛቸውን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የኢንዶክትሬሽንና ህዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር #ፋሲካ_ፈንታ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ 61 በሞተር ሳይክል የተደገፈ ቅሚያ በከተማዋ ተፈፅሟል።

ወንጀሉ የተፈፀመው በከተማዋ በሚገኙ 8 ክፍለ ከተሞች መሆኑንም ተናግረዋል።
ከፍተኛ የቅሚያ ወንጀል የተፈፀመበት የቦሌ ክፍለ ከተማ 21 በሞተር ሳይክል የተደገፉ ወንጀሎች የተፈፀመበት ሲሆን ዝቅተኛ የቅሚያ ወንጀል በተፈፀመበት ልደታ ክፍለ ከተማ አንድ ወንጀል ተፈጽሟል።

በአቃቂ ቃሊቲና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ምንም አይነት በሞተር ብስክሌት የተደገፈ ቅሚያ አለመፈጸሙን ገልጸዋል።
ወንጀል ፈፃሚዎቹ በራሳቸውና በተከራዩት የሞተር ብስክሌት የቅሚያ ወንጀሉን እየፈፀሙ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር ፋሲካ ወንጀሉን ፈጽመው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች በፍርድ ቤት ጉዳያቸው እንደተያዘና ቀሪ የወንጀል ፈጻሚዎች ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ፖሊስ የሚያከናውነውን ወንጀል የመከላከል ተግባር ኅብረተሰቡ ወንጀል ፈፃሚዎችን #የማጋለጥና ወንጀል የመከላከል ስራው እንዲደግፍ ጥሪ አቅርቧል።

”ወንጀልን መከላከል በፖሊስ ጥረት ብቻ የሚከወን አይደለም” ያሉት ኮማንደር ፋሲካ የኅብረተሰቡ ድጋፍ ከተጠናከረ ወንጀል ፈፃሚዎች ሊያመልጡ እንደማይችሉም ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ከቅሚያ ወንጀሉ በተጨማሪ ሌሎች የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን የፈፀሙ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ላይም እርምጃ መወሰዱን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

#ሀሰተኛ_መንጃ_ፈቃድ ይዘውና ያለመንጃ ፍቃድ ሞተር ብስክሌት ሲያሽከረክሩ የነበሩ እንዲሁም ሲያሽከረክሩ ማሟላት የሚገባቸውን እንደሄልሜት ያሉና ሌሎች የትራፊክ ደንብ ጥሰት የፈፀሙ ከ7ሺህ በላይ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው የጸጥታ ችግር ተራ የቡድን ጸብ እንጂ ከፖለቲካ ግጭት ጋር የተገናኘ እንዳልሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በቡድን ጸቡ ተካፋይ የነበሩትን 231 ተጠርጣሪዎች #በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሎ ባደረገው ማጣራት ከጉዳዩ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ 72 ወጣቶችን በማስቀረት ቀሪዎቹን 159 ወጣቶች በምክር #መልቀቁንም አስታውቋል።

የፖሊስ ኮሚሽኑ የኢንዶክትሪኔሽን እና የህዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር #ፋሲካ_ፈንታ ማምሻውን ለአርትስ ቲቪ እንዳስታወቁት በወጣቶቹ መካከል የተፈጠረውን ጸብ ከቄሮ የወጣቶች ቡድን ጋር በማገናኘት የፖለቲካ ግጭት አስመስሎ የተናፈሰው ወሬ ፍጹም መሰረተ ቢስ ነው። እንደኮማንደር ፋሲካ ገለጻ የጸቡ መነሻ በአንድ የላዳ ታክሲ ሹፌር እና በአካባቢው በነበሩ ወጣቶች መካከል “መንገድ አሳልፈኝ አላሳልፍም” በሚል ጭቅጭቅ የተነሳ አለመግባባት ነው።

ትናንት መጋቢት 8 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ አንድ ክልል አየርአምባ ትምህርት ቤት ከፍ ብሎ በሚገኘው የጫት መሸጫ ሱቆች አካባቢ ተከስቶ በነበረው በዚሁ ተራ ግጭት ቂም የያዘው የታክሲ ሹፌር ወደሰፈሩ በመሄድ ለጓደኞቹ በአካባቢው ወጣቶች ጥቃት እንደደረሰበት ተናግሮ ለጸብ ሲዘጋጁ ካደሩ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደስፍራው በመምጣት አጥቅተውኛል ካላቸው ወጣቶች ጋር ግጭት እንዲፈጠር አድርጓል።

እንደኮማንደር ፋሲካ ገለጻ ፖሊስ አስቀድሞ መረጃ ስለደረሰው ወደስፍራው ሃይል በማሰማራት ጸቡን ለመከላከል ጥረት በማድረግ ላይ እያለ በሁለቱ ሰፈር ወጣቶች መካከል በተቀሰቀ ጸብ በእንቅስቃሴ ላይ የነበሩ ሶስት ተሽከርካሪዎች መስተዋት ሲሰበር በተመሳሳይ በመስተዋት ተሰርተው የነበሩ የጫት መሸጫ ሱቆች እና በአካባቢው በሚገኝ የኦሮሚያ ባንክ ቅርንጫፍ ቢሮ መስተዋት ላይም መጠነኛ ጉዳት ደርሷል።

ፖሊስ በሁለቱም ወገን የጸቡ ተካፋይ ናቸው ያላቸውን 231 በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማጣራቱንና በቀጥታ በግጭቱ ተሳታፊ ናቸው ያላቸውን 67 ወንዶችና 5 ሴቶች በድምሩ 72
ተጠርጣሪዎች በእስር አቆይቶ ቀሪዎቹን 159 ተጠርጣሪዎች በሙሉ ዳግም በዚህ አይነት ጥፋት ላይ እንዳይገኙ መክሮ መልቀቁን ተናግረዋል።

ኮማንደር ፋሲካ እንዳሉት እውነታው ይኸው ሆኖ ሳለ አንዳንድ አክቲቪስቶች በማህበራዊ ሚዲያ “በቦሌ ቄሮ እና በአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ” በማለት ባሰራጩት የሃሰት መረጃ ያልተገባና ለፖለቲካ አላማ የታቀደ ተግባር በመፈጸም የህብረተሰቡን ደህንነት ስጋት ውስጥ ለመክተት ሞክረዋል። ከተማዋ አለመረጋጋት እንደሌላት በማሰብ ብዙዎች ለደህንነታቸው ስጋት እንዲገባቸውም ምከንያት ሆነዋል። ይህ ተግባር ፍጹም ሃላፊነት የጎደለውና ማመዛዘን ከሚችል አካል የማይጠበቅ ነው ያሉት ኮማንደሩ እንዲህ አይነት የሃሰት መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦችም በህዝብ ሰላምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ወንጀል እየፈጸሙ መሆኑን ሊገነዘቡና ሊጠነቀቁ ይገባል ነው ያሉት።

ህብረተሰቡም በዚህ አይነት #የፈጠራ_መረጃ እንዳይደናገር ያሳሰቡት የፖሊስ ሃላፊው ለማይበርድ ግጭት የሚዳርጉ የሃሰት ወሬዎችን ባለማራገብ ሰላሙን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከዚህ ግጭት ምርመራ ጋር ተያይዞ ያሉትን ቀሪ ውጤቶች በቀጣይ ለህዝቡ ይፋ እንደሚያደርግም ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል።

Via ArtsTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia