TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#udate አርበኞች ግንቦት 7⬇️

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ የሁሉም ሀሳብ አራማጆች #ለዘለቄታዊ ለውጥ ቁጭ ብሎ መወያየት እንደሚገባ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።

ሊቀመንበሩ በቦሌ አየር ማረፊያ በሰጡት መግለጫ #የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለመጠበቅ ከመጣር ይልቅ #ትክክለኛ ምርጫ ማካሄድ የሚችል ስርዓትና #ተቋማት መኖራቸውን ማረጋገጥ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ገልፀዋል።

የለውጡ ኃይል የሀገሪቱን ረጅም የመከራ ቀን በመሳጠርም ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉንም አስታውቀዋል።

ከሁሉ በላይ ሁላችንም ለሀገር ለውጥ #እንወያይ የሚል ሀሳብ አንግቦ ለተግባራዊነቱም መስራቱ መጪው ጊዜ #ብሩህ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳሰነቃቸውም ገልፀዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከሁሉም ኃይሎች ጋር ተመካክሮ የተገኘውን ይህን እድል መጠቀም እንደሚሻም ነው ያሰትወቁት ።

በፖለቲካ ምክንያት ሰውን እንደጥላት የማየት አስተሳሰብ ከህብረተሰቡ ሊወጣ ይገባል #መረጋጋት ያስፈልጋል ብለዋል ፕሮፌሰሩ።

የሀገሪቱን ዘለቂ ሰላም ለማምጣትና ዲሞክራሲያዊ ባህልን ለማጎልበት ህብረተሰቡ ለመወያየትና ለመደማመጥ የሚቻልበት ሁኔታ መፍጠር አለበት ስለዚህም ለሁሉም ነገር ነገሮችን #ተረጋግቶ ማሰብ ይገባል ብለዋል።

እኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመጣ ከማድርግ ውጪ ሌላ ዓለማ የለም ይህን ስራ ለመተግበር ግን ብዙ ስራ ይጠይቃል ይህንንም ከሁሉም ጋር በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ ነን ብለዋል ሊቀመንበሩ በመግለጫቸው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ እኛ በህብረ ብሔራዊ ስሜት ሀገርን ለመገባት አስበን ብንመጣም #በብሔር ከተደራጁ አካት ጋርም ቢሆን በዲሞክራሲያዊ መልኩ #ለመወያየት ዝግጁ ነን ብለዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በብሄር ግጭት 890 ሰዎች ተገደሉ‼️

የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መረጃ መሰረት፤ በምዕራብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #በብሔር_ግጭት ሳቢያ ቢያንስ 890 ሰዎች ተገድለዋል።

#ባኑኑ እና #ባቴንዴ በተባሉ ማኅበረሰቦች መካከል ግጭት የተከተሰተው ዩምቢ በሚባለው አካባቢ በሚገኙ አራት መንደሮች ውስጥ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው፤ አብዛኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው #ተፈናቅለዋል። ዩምቢ አካባቢ ባለው ግጭት ሳቢያ ለዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ የሚሰጡት መጋቢት ላይ ይሆናል።

የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው፤ 465 ቤቶችና ህንጻዎች ተቃጥለዋል፤ ፈራርሰዋልም። ከነዚህ መካከል ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋም፣ ገበያ እና የሀገሪቱ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ቢሮ ይገኙበታል።

ከተፈናቀሉት ሰዎች 16,000 የሚሆኑት የኮንጎ ወንዝን ተሻግረው በኮንጎ ብራዛቪል ተጠልለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ሚሼል ባቼት፤ "ይህ አስደንጋጭ ግጭት ተመርምሮ ጥፋተኞቹ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው" ብለዋል። ኮሚሽኑ ምርመራ መጀመሩም ተመልክቷል።

ዩምቢ ለወትሮው ሰላማዊ ግዛት ነበር። በማኅበረሰቦቹ መካከል ግጭት የተቀሰቀሰው፤ የባኑኑ ማኅበረሰብ አባላት ባህላዊ መሪያቸውን በባቴንዴ መሬት ለመቅበር በመሞከራቸው ነበር።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምርጫን ፌሊክስ ቲስኬዲ ማሸነፋቸው ቢነገርም ሌላው ተቀናቃኝ ማርቲን ፋያሉ "አሸናፊው እኔ ነኝ" ማለታቸው ይታወሳል።

ማርቲን ፋያሉ እንደሚሉት ከሆነ፤ ፌሊክስ ቲስኬዲ ምርጫውን ያሸነፉት ከቀድሞው ፕሬዘዳንት #ጆሴፍ_ካቢላ ጋር #ተመሳጥረው ነው። ሕዝቡ የሰጠው ድምጽ ዳግመኛ ይቆጠር ሲሉም ለፍርድ ቤት አቤቱታ አሰምተዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጉዳይ በተመለከተ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ መክሯል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት . . .

ዛሬ ማክሰኞ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በ "ኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት" ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ናቸው ያላቸው ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል።

ጥናቱ ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ?

ጥናቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ምንም ማሻሻያ ሳይደረግበት መቆየቱ ተገልጿል።

ኢንስቲትዩቱ ላለፉት ሁለት / 2 ዓመታት አከራካሪ በሆኑ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች በተለይም ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች የማሻሻያ ጥናት ማድረጉን አሳውዋል።

በጥናቱም ፦

በ2000 ዓ.ም ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተዘረዘሩት 83 ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል 41 የሚሆኑት በስልታዊ የዘፈቀደ ዘዴ (systematic random sampling) ተመርጠዋል ሲል አሳውቋል።

በዚህ መሠረት የሕገ-መንግሥቱ መግቢያ ላይ ያሉ የተወሰኑ ሐሳቦች ማለትም ፦

👉 የብሔር ብሔረሰቦች ሉዓላዊነት አንቀፅ 8፣

👉 የፌዴራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ፣

👉 ብሔራዊ አርማ፣

👉 #ብሔርን መሠረት ያደረገው አስተዳደራዊ ወሰን፣

👉 #መገንጠልን የሚደነግገው አንቀፅ 39፣

👉 የፖለቲካ ፓርቲን #በብሔር_ማደራጀት

👉 #የአዲስ_አበባ_አስተዳደርን በተመለከተ መሻሻል እንዳለባቸው #ሕዝቡ_ፍላጎት እንዳለው ተመላክቷል ብሏል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የታሰሩት የምክር ቤት አባላት የት ናቸው ? በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተያዙ የም/ቤት አባላት ታስረውበት ከነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የማቆያ ቦታ እንደሌሉ እና ያሉበትን ቦታ ማወቅ እንዳልቻሉ ከጠበቆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዲሁም በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ…
#EHRC

አዋሽ አርባ ላይ ታስረው የሚገኙ አብዛኞቹ እስረኞች ለእስር የተዳረጉት #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ 5 የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የሚገኙበት ቡድን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በቁጥጥር ሥር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ጎብኝቷል።

እነዚህ ታሳሪዎች ፦
- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣
- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣
- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር፤
- ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ፣ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ፤
- የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ በለጠ ጌትነት፤
- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በኃላፊነት ይሠሩ የነበሩት አቶ ከፋለ እሱባለውን ጨምሮ በአጠቃላይ 53 ወንድ እስረኞች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ተይዘው ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኝ ጊዜያዊ / መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ የተወሰዱ ናቸው፡፡

ኮሚሽኑ በተለመደው አሠራሩ መሠረት ታሳሪዎቹን ለብቻቸው አነጋግሯል፣ ቦታውን ጎብኝቷል እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የፖሊስ ኃላፊዎች አነጋግሯል፡፡

የፖሊስ ኃላፊዎች ለኮሚሽኑ እንደገለጹት ፤ ታሳሪዎችን ወደዚህ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ማምጣት ያስፈለገው አዲስ አበባ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ መጣበብ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ታሳሪዎች ምን አሉ ?

እጅግ አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች ብሔራቸው #አማራ፣ እምነታቸው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆኑንና ለእስር የተዳረጉት ደግሞ #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

ከፊሎቹ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተያዙበትና ቤታቸው በተበረበረበት ወቅት በራሳቸውና በቤተሰብ አባል ላይ ድብደባ፣ ብሔር ተኮር ስድብ፣ ማጉላላት፣ ዛቻና ማስፈራራት እንደደረሰባቸው ሆኖም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከሆነ በኋላ የተፈጸመ ድብደባ ወይም አካላዊ ጥቃት አለመኖሩን አመልክተዋል።

ከፊሎቹ በተለይም ከአማራ ክልል ተይዘው የመጡ ሰዎች ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ እንኳን እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ታሳሪዎቹ የአዋሽ አርባ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ያለው በመሆኑና ከአካባቢው የአየር ጠባይ እንዲሁም ቦታው የወታደራዊ ካምፕ እንጂ መደበኛ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ስፍራ ስላልሆነ ለጤንነታቸው፣ ለደኀንነታቸውና ለሕይወታቸው ሥጋት እንዳላቸው፣ አልባሳትን ጨምሮ ከቤተስብ የሚፈልጉትን አቅርቦት ለማግኘት እንዳልቻሉ፣ ከፊሎቹ በሥራቸውም ሆነ በግል ሕይወታቸው ፈጽሞ በፖለቲካ ነክ ጉዳይ ተሳትፎ እንደሌሉና እንዴት ለእስር እንደበቁ መገረማቸውንና መደንገጣቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከፖሊስ ኃፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በእስር ወቅት ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሥነ ምግባር ጥሰቶች ተገቢው ማጣራት እንዲደረግ፣ ታሳሪዎቹ ከቤተሰብ ለሚፈልጉት አቅርቦት አዲስ አበባ በሚገኘው የፖሊስ ቢሮ አማካኝነት እንዲመቻች፣ ከቤተስብ መገናኛ ስልክና ጉብኝት ለሚፈልጉም በአፋጣኝ እንደሚመቻች መግባባት ላይ ተደርሷል።

(ከኢሰመኮ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia