TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ከነዳጅ ዋጋ 📈 ቤንዚን እና ናፍጣ ላይ በሊትር ከ5 ብር በላይ ጭማሪ ተደረገ። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ ተደርጓል። ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ይፋ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ገልጿል። ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እስከሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ አንጻራዊ መረጋጋት እንደታየበት ገልጿል፡፡ በዚህም…
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም መሠረት ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

- ቤንዚን 👉 በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም

- ነጭ ናፍጣ 👉 በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም

- ነጭ ጋዝ 👉 በሊትር 76 ብር ከ75 ሳንቲም

- የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 በሊትር 70 ብር ከ83 ሳንቲም

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም

- ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 61 ብር ከ83 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አካል የሆነው ፓለቲካዊ ውይይት በአስቸኳይ በተጠናከረ መልኩ እንዲጀመር ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት ጠየቀ። ድርጅቱ ለአንድ ሳምንት ያህል ዝግ ስብሰባ ሲያካሄድ ቆይቶ ትላንት ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ስብሰባውን አጠናቋል። ህወሓት መስከረም 14 /2016 ዓ.ም አመሻሽ ባወጣው መግለጫ ፥ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተከትሎ ህዝቡ ከጥይት…
" ... የተካሄደው ጦርነት መነሻ ፓለቲካዊ በመሆኑ በፓለቲካዊ ውይይት መቋጫ ማግኘት እንዳለበት ተወስኗል " - ህወሓት

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማእከላይ ኮሚቴ ሰላማዊ ትግል አጠናክሮ በማስቀጠልና በፓርቲው ስትራቴጂክ አመራር የታየው ድክመት አስመልክቶ በጥልቅ መወያየቱ ገለፀ።

ይህን የለፀው የግዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። 

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ባካሄደው ስብሰባ የአመራር ችግር በትኩረት መገምገሙንና በአስቸካይ ማሰተካከያ እንዲደረግ ወስኗል። 

" ያካሄድኩት ግምገማ ውሱንና ያልተሟላ ነው " ያለው የድርጅቱ ሊቀመንበር መግለጫ የመስመር ፣ የፓሊሲና ስትራቴጂ ፣ የብሄራዊ መከታ ግምገማ ለማረድግ ወመሰኑ አመልክተዋል።

ሰላማዊና ፓለቲካዊ ትግሉ በመምራት በኩል የተፈፀመ የአመራር ጉድለት መኖሩም መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።

ህወሓት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አካል ነው ፤ ከፌደራል መንግስት በመስማማት የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም መስማማቱም ተወስቷል በመግለጫው። 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የሰጠው ቴክኒካዊ ውሳኔ ትክክል አይደለም ፤ ህጋዊ እውቅና ያለው የህወሓት ፓርቲ እውቅና መስጠትና መንሳት በፓለቲካ እንጂ በቴክኒካዊ ሂደት የሚፈፀም አይደለም ተብሏል።

የአገሪቱ ከፍተኛ ህግ አውጪ የሆነው የተወካዮች ምክር ቤት ከሽብር መዝገብ ነፃ ያለው የፓለቲካ ድርጅት ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ህግ በተቋቋው የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና የሚነሳበት ሁኔታ የለም ብሏል።

የተፈጠረው የሰላም ስምምነት ዘላቂ እንዲሆን የህወሓት አወንታዊ አስተዋፅኦ መዘንጋት የግዚያዊ አስተዳደሩ ስራ ማደናቀፍ ማለት ነው ያሉት ከፍተኛ አመራሮቹ በትግራይ የታየው የፍትህ ፣ የፀጥታና የሙስና ችግሮች የስትራቴጂክ አመራር መጓደል ማሳያ መሆናቸው ተገምግመዋል ብሏል።  

በተፈፀሙት የሙስናና ሌሎች ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ከሁሉም በላይ ከላይ ወደ ታች የማጥራት ስራ እንዲጀመር መግባባት ተደርሷል ያለው መግለጫው " የግዚያዊ አስተዳደሩ የትኩረት አቅጣጫዎች  የህወሓትና የትግራይ ህዝብ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው ሲል " አክለዋል። 

ደሞ ተከፍሎበት የተገኘው ሰላማዊ ትግል ከማስቀጠል ውጪ ሌላ አማራጭ የለም ፤ ስለሆነም የተካሄደው ጦርነት መነሻ ፓለቲካዊ በመሆኑ በፓለቲካዊ ውይይት መቋጫ ማግኘት እንዳለበት ተወስኗል።  

የግዚያዊ መንግስቱ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸውና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ፤ " የትግሉ ሰማእታት የቤተሰቦቻቸው ብቻ ሳይሆኑ የሁላችን ናቸው " ያሉ ሲሆን  የትግራይ ህዝብን ከጥፋት ለመከላከል ዋጋ የከፈሉ ናቸው ብለዋል።

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በመላ ክልሉ የሃዘን ቀን እንደሚታወጅ የመስቀል በአል ምክንያት በማድረግ በመቐለና በዓዲግራት ባስተላለፉት መልእክት ማስታወቃቸው መዘገባችን ይታወሳል። 

@tikvahethiopia
#EHPA

የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማህበር ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ መግለጫ ልኮልናል።

በዚሁ መግለጫው በቅርቡ በአማራ ክልል በተከሰተዉ ግጭትና አለመረጋጋት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጤና እክል እንዳስከተለ አሳውቋል።

ማህበሩ ፤ አንቡላንሶች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰዉ አገልግሎት አለመስጠት እና ከታለመላቸዉ አላማ ዉጭ ለወታደራዊ እንቅስቃሴ አገልግሎት ሲዉሉ ተስተዉሏል፡ ብሏል።

" አሁንም ወደ ጤና ተቋም አገልግሎት ያልተመለሱ ብዙ አንቡላንሶች እንዳሉ አረጋግጠናል " ሲል ገልጿል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ያሉ ችግሮች ህብረተሰብን ፤ የጤናውን ዘርፍ ፤ ሀገርንም በከፍተኛ ደረጃ እየጎዱ መሆኑ አስገንዝቧል።

በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ፦

- እየተካሄደ ያለው ግጭት ባስቸኳይ እንዲቆምና ሰላማዊ ድርድር እንዲያደርጉ የሰላም ጥሪ አቅርቧል።

- በጦርነቱ ወቅት አንቡላንሶችን ከታለመላቸዉ አላማ ዉጭ መጠቀም እንዲቆም አና አንቡላንሶች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰዉ የህይወት አድን ስራቸዉን መስራት ሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር አሳስቧል።

- በትግራይ አፋርና አማራ ክልል በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸዉ ጤና ተቋማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መልሶ የማቋቋም እና በሙሉ አቅማቸዉ ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ ማድረግ ቀዳሚ የመንግስት ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ብሏል።

ማህበሩ ከዚህ በተጨማሪ በመግለጫው ፤ የጤና ባለሙያዎች ኑሮአቸውን ለመምራት የሚያስችል #ደሞዝም ሆነ #ጥቅማጥቅሞች ተነፍገዉ አየኖሩ ይገኛሉ ብሏል።

" በተደጋጋሚ ችግሩን ለመንግስት አካላት ብናቀርብም ምንም አይነት ምላሽ አልተሰጠም " ሲል ገልጿል።

ማህበሩ በቀን 30/06/2015 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ ቤት እስከ ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ለሌሎች የሃገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ተቋማት የጤና ባለሙያዎችን ደሞዝና የመብት ጥያቄዎችን ቢያቀርብም ምንም አይነት ተገቢ ምላሽ ባለማግኘቱ ጤና ባለሙያዎች ለከፋ የኑሮ ቀዉስ መዳረጋቸውን አመልክቷል።

በመሆኑንም የጤና ባለሙያዎች የሚያነሷቸዉ የመብት ጥያቄዎች አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ ማህበሩ ጠይቋል።

(ከማህበሩ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ALERT🚨 አንድ አንጀራ ለ10 ተሻምተው የሚበሉ ወገኖቻችን እንዳሉ እናውቅ ይሆን ? በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከፍተኛ ድርቅ ተመቷል። ነዋሪው ችግር ላይ ወድቋል። ሰው በረሃብ #ሞቷል ፣ እንስሳት ሞተዋል ፣ ተሰደዋል። ወገኖቻችን በቂ ምግብ አጥተው 1 እንጀራ ለአስር እየተሻሙ እየበሉ ነው። ካዛ ውጭ ጨው በውሃ በጥብጠው ነው የሚጠጡት። " በዚህ ሳምንት…
#Update

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በተለይም ሰሀላ ሰየምት ወረዳ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የወረርሽኝ ኬዞች እንዳሉ የአስተዳደሩ ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ ኪዳት እድል (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኪዳት (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፣ " ከድርቁ ጋር በተያያዘ መንገድ በእርግጥ አንድ አንድ የተቅማጥ ኬዞች አሉ " ብለዋል።

አክለውም ፤ " ነገር ግን ኬዙ አተት ወይም ኮሌራ ነዉ ብለን ለይተን ያስቀመጥነው ነገር የለም ከዚህ በኋላ ግን ከፍተኛ የሆነ ስጋት ነዉ ያለን በተቅማጥ በኩል የሚከሰት ወረርሽኝ ሊኖር ይችላል " ብለዋል።

" ከድርቁ ጋር በተያያዘ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ሊጨምሩ ይችላሉ " ያሉት ኪዳት (ዶ/)፣ " ከምግብ እጥረቱ ጋር ተያይዞ በተለይ ከ 5 ዓመት በታች ባሉ ህፃናት የሳንባ በሽታ፣ ተቅማጥ እና ተያያዥ የሆኑ ለሞት የሚያደርሱ በሽታዎች ይከሰታሉ " ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጸዋል።

" እንዲሁም ከምግብ እጥረት ጋር ተያይዞ ተቅማጥ፣ ውሃ ወለድ የሆኑ በሽታዎች ይከሰታሉ " ያሉት ኃላፊው፣ " ከእንስሳት ጋር ተያይዞም የእንስሳት በሽታዎች ይከሰታሉ እነዚህ እንግዲህ ተያያዥ ችግሮች ናቸው " ብለዋል።

" በወረርሽኝ መልክ ይከሰታሉ ብለን ከምናሰገባቸው በሽታዎች መካከል አንደኛው ወባ ሲሆን በተጨማሪም አተት የሚባለው በሽታ በተለምዶ ኮሌራ ድርቅ በተከሰተበት ወረዳ መከሰቱ የማይቀር ነው። እንዲያውም ቁጥር አንድ ይከሰታል ብለን ከምናስባቸዉ ወረዳዎች ሰሀላ ሰየምት ዋነኛው ነው " ሲሉ አክለዋል።

የጤና መምሪያ ኃላፊው፣ " እንደ ጤና ድርቅ ሲኖር የሚከሰቱ ብዙ ችግሮች አሉ ፊት ለፊት ያለው የረሀብ ችግር ነውና በተለይ አጥቢና ነፍሰጡር እናቶች ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በጤና ጉዳይ ግንባር ቀደም ተጠቂ ናቸው ስለዚህ እሱ በጣም ትልቅ ችግር ስለሆነ የምግብ እጥረት ልየታ እያሰራን ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እውነቱን ለመናገር ነዋሪዎቹ እርቧቸዋል። እያለቀሱ ነው የተናገሩት። ድረሱልን እያሉ ነው " - አቶ ምሕረት መላኩ

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር  የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋሰትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የአማራ ክልል መንግሥት ድርቅ በተከሰተባቸው ቦታዎች የዕለት ድጋፍ ለማድረስ ቢስማማም በጸጥታ ችግር መድረስ እንዳልቻለ ገልጸዋል።

ኃላፊው ከ1.2 ሚሊዮን በላይ እንስሳት ወደ አጎራባች ወረዳዎች ለመፈናቀል እንደተገደዱ በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ሂደው ማረጋገጣቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በቦታው ገብተው ድጋፍ በማድረግ ችግሩን እንስኪጋሩ ድረስ የክልሉ መንግሥት የዕለት ምግብ አቀርባለሁ ብሎ ውሳኔ አሳልፏል " ያሉት አቶ ምህረት፣ " ነገር ግን ሰሞኑን በጎንደር መስመር የጸጥታ ችግር ስለነበረ የትራንስፓርት ተጫራቾቹ ችግር አለ #አንሄድም አሉኝ ነው ያለው " ብለዋል።

" መስከረም 18 እና ዛሬ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም አንጻራዊ ሰላም ከሆነ ምግብ ይዘው እንዲገቡ ነው የተግባባነው " ሲሉ አክለዋል።

እስካሁን የተገኘ ድጋፍ እንዳለና እንደሌለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄም፣ " የሕጻናት አድን ድርጅት (ሴቭዘቺልድረን) 475 ቤት መሪዎች ለእያንዳንዳቸው 21,000 ብር ድጋፍ አደርጋለሁ ብሎ ዛሬ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም የተጠቃሚ ልየታ ሊጀመር ነው " ብለዋል።

አክለውም፣ " ቅድመ ዝግጅት ነውና እያደረግን ያለነው ወደ ሕዝቡ በተጨባጭ የገባ ድጋፍ ይለም " ነው ያሉት።

ነዋሪዎች ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄም፣ " ነዋሪዎቹ እውነቱን ለመናገር እርቧቸዋል። እያለቀሱ ነው የተናገሩት። ድረሱልን እያሉ ነው " ሲሉ ድርቅ በተከሰተበት አካባቢ በአካል ተገኝተው ያረጋገጡትን አስረድተዋል።

" እንስሳትንም ለማየት ሞክረን ነበር" ያሉት አቶ ምህረት የጋማ ከብቶች፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየሎችን ጨምሮ 1.2 ሚላዮን እንስሳት ሳር ወዳለባቸው አጎራባች ቦታዎች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል።

አክለውም ፣ " ተከዜን ተሻግሮ በሚገኙ የሰሀላ ሰየምት 13 ቀበሌዎች ከአንዱም ቀበሌ ለእንስሳት የሚሆን መኖ አላገኘነም። የእንስሳት ሞት ቁጥርም እየጨመረ ነው" ብለዋል።

ቀይ መስቀል በአካባቢው ላይ ገብቶ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥያቄ እንዳቀረቡም አቶ ምህረት ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

አዲስ አበባ ላይ የሚፈፀም የመኪና ታርጋ ስርቆት ትኩረት እንዲሰጠው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ " ይህን መሰሉ የታርጋ መስረቅ ድርጊት እየተስፋፋ መጥቷል " ያሉ ሲሆን 3 ጓደኞቻቸውና እሳቸውን ጨምሮ በዚህ 3 ቀን ውስጥ የፊት እና የኃላ ታርጋቸው መሰረቁን ገልጸዋል።

የሚመለከተው የከተማው የፀጥታ አካል ይህንን ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስበዋል።

ታርጋዎች እየተሰረቁ የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ይፈፀማሉ። የመኪና ባለቤቶች የሆናችሁ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከቆማችሁበት ስትነሱ ሁሌም ታርጋችሁ መኖሩን እንድትመለከቱ እንዲሁም መኪና ስታቆሙ ሊጠብቁ የሚችሉ የፓርኪንግ ሰዎች ባሉበት እንዲሆን እንመክራለን።

@tikvahethiopia
#WolaitaZone

• በዎላይታ ዞን የተመዘገበው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት አስደንጋጭ ነው ተብሏል።

• ፈተናው ከወሰዱት ከ31 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከ20 ፐርሰንት በታች የማለፍ ምጣኔ መመዝገቡ ተነግሯል።

በዎላይታ ዞን ፤ የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በተለየ መንገድ መሰጠቱ ዝቅተኛ ዉጤት እንዲመዘገብ ምክኒያት ሆኗል ተባለ።

እንደ ሀገር የገጠመን የትምህርት ስብራት ለመጠገን ይቻል ዘንድ በሀገር ደረጃ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነ ይታወቃል።

በተለይም በፈተና ስርአቱ እየታዩ የነበሩ ስህተቶችን ለመቅረፍ በማስብ አዳዲስ የፈተና ስርአቶች ተዘርግተዋል።

ይህን በመከተል የወላይታ ዞን በዚህ አመት የስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናን በተለዬ መልኩ መፈተኑ ተገልጿል።

የመምሪያዉ የመምህራንና የትምህርት ልማት ዳይሬክተር ቡድን መሪዉ አቶ ኢሳያስ ሀይሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት ፤ ተማሪዎችን አጥርቶ ለማሳለፍ የፈተና ጣቢያዉን በመቀየር በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መፈተናቸዉ የመጠነ ማለፉን ዝቅ ማድረጉን ያነሳሉ።

አቶ ኢሳያስ ፤ በዚህ አመት የታየዉ ከ20 ፐርሰንት በታች የማለፍ ምጣኔ መሆኑን ገልጸው ይህ ለብዙዎች አስደንጋጭ መሆኑን አንስተዋል።

ካሁኑ ችግሩን ቀርፎ ጥሩ ዉጤት  ማስመዝገብ ይቻል ዘንድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት መጀመሩን ገልጸዋል።

ከሰላሳ ሶስት እስከ ሰላሳ አምስት ፐርሰንት  የነበረዉ የማለፊያ ዉጤት በዚህ አመት ወደሀምሳ ፐርሰንት ከፍ ማለቱ ያላለፉ ተማሪዎችን ቁጥር እንዲያሻቅብ ትልቅ ምክኒያት መሆኑንም አንስተዋል።

ሀላፊዉ ይህ የማለፊያ ዉጤትና የፈተና አሰጣጥ የሚቀጥል መሆኑን አዉቀዉ ተማሪዎች ካሁኑ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዉል።

መረጀው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
" ኢትዮጵያ ውሉ በጠፋና ተለዋዋጭ በሆነ ጊዜ ውስጥ ናት " - ጥናት

አገር በቀሉ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ተቋም የማኅበራዊ ጥናት መድረክ (ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ) ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ጥናት ኢትዮጵያ ውሉ በጠፋና ተለዋዋጭ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንደምትገኝ ገለጸ፡፡ 

ይፋ ባደረገው ጥናቱ የኢትዮጵያን ወቅታዊና የወደፊት መፃዒ ሁኔታ ዳሷል፡፡

"ኢትዮጵያ ወዴት? ቢሆንታዎች" በሚል ርዕስ የቀረበው ይኼው ጥናት የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ መንገራገጭ፣ የሐምሌ ጨለማና ፀደይ በማለት በሦስት ቢሆንታዎች (Scenarios) ለማስቀመጥ የሞከረ ነበር፡፡

የቢሆንታዎችን ምንነትን ወደኋላ በመመለስ ከታሪካዊ ዳራ ተነስቶ ብይን ለመስጠት የሚሞክረው ጥናቱ፣ የወቅቱን የአገሪቱን ሁኔታም ፍቺ ለመስጠት ሞክሯል፡፡

" በአንድ ማኅበረሰብ የመንግሥት ተዓማኒነት እየተሽከረከረ ሲሄድ፣ ማኅበረሰባዊ ትስስር ሲመነምንና በሕዝብ ዘንድ የፍትሕ መጓደል/ ተበዳይነት ስሜቶች ሲያንዣብቡ #ጽንፈኝነት ይነግሣል " በማለት ነው ይኸው ጥናት የኢትዮጵያን ገጽታ በማስቀመጥ ወደ ሐተታው የሚንደረደረው።

ጥናቱ በአሁኗ ኢትዮጵያ እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች እንደሚታዩ ገልጾ ፖለቲካዊ መግባባት በአገሪቱ መፍጠር ከምንም በላይ አስፈላጊ መሆኑን ያሰምርበታል፡፡

ያም ቢሆን ግን ባለፉት 50 ዓመታት በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ችግሮችን ተወያይቶ የመፍታት ባህል አለመዳበሩ ትልቁ ራስ ምታት እንደሆነ ያወሳል፡፡

በዘውዳዊው ሥርዓት መውደቅ ማግሥት አምባገነናዊ ሥርዓት በኢትዮጵያ በማቆጥቆጡ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ተስፋው መምከኑን ያስረዳል፡፡

ደርግ ወድቆ በ1983 ዓ/ም የመንግሥት ለውጥ ሲደረግ " የሕዝቦች እኩልነት ይፈጠራል " የሚል ተስፋ መፈጠሩን ይሁን እንጂ ይህንን ለውጥ ተከትሎ የተቀረፀው ሕገ መንግሥት የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ይፈጥራል ቢባልም ነገር ግን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የጭቅጭቅ ምዕራፍ መክፈቱን ያትታል፡፡

በየታሪክ ምዕራፉ ለዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሽግግር ተስፋ የፈነጠቁ አጋጣሚዎችን አለፍ ገደም እያለ የሚዘረዝረው ጥናቱ፣ በ2010 ዓ.ም. የተፈጠረውን የፖለቲካ ለውጥ እንደ አንዱ አጋጣሚ ያነሳዋል፡፡ 

" ለውጡ ከፈጠረው ከፍተኛ የሕዝብ ፈንጠዚያ ጀርባ ግን በለውጥ አቀንቃኞችና በቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች መካከል ውስጥ ውስጡን ውጥረት ሰፈነ " ይላል፡፡

የአዲስ ተስፋው ፍንጣቂ በለውጡ  ማግሥት ብዙም ሳይዘገይ በመጣው " የነውጥ ጊዜ " እንደተተካም ነው ጥናት ያመላከተው፡፡

የኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ታሪክ በብዙ ፈታኝ ውጣ ውረዶች ውስጥ የማለፍ አስገራሚ ፅናት የተላበሰ መሆኑን ጥናቱ ያብራራል፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል ግን ፈላጭ ቆራጭነት የሰፈነበት ሆኖ መቆየቱን ይገልጻል። በኢኮኖሚውም መስክ በአስከፊ ድህነት ውስጥ አገሪቱ ተዘፍቃ መኖሯን ያትታል፡፡

ከዚህ ሁሉ ተነስቶ አገሪቱ የሐምሌ ጨለማ፣ መንገጫገጭና ፀደይ የሚል ስም የተሰጣቸው ቢሆንታዎችን ልታስተናግድ እንደምትችል ሰፊ ትንተና ያቀርባል፡፡

በሌላ በኩል የመበታተን አደጋን እንደ አንድ ቢሆንታ ያነሳዋል። " አስደንጋጭ ቢሆንም የአገሪቱ የመበታተን አደጋ የማይታሰብ ነው ለማለት አይቻልም " ሲል ነው ጥናቱ ያብራራው።

ጥናቱ ከአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ እስከ አየር ንብረት ለውጥ #ከሃይማኖት እና #ፖለቲካ ፅንፈኝነት እስከ የብሔርና ያልተማከለ አስተዳደር ውጥረት አገሪቱን ሊፈትኑ የሚችሉ ነጥቦችን ይፈትሻል፡፡

ከኢኮኖሚ አለመረጋጋት እስከ የዋጋ ንረት ውጣ ውረዶንችም ያነሳል፡፡

በሌላ በኩል፤ የአማራ ክልልና አገሪቱን ወጥረው የያዙ በየአቅጣጫው ያሉ የግጭት ሁኔታዎችን ተፅዕኖም የፈተሸ ነው። #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ❤️

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን በዛሬው ዕለት መካሄዱን በጀመረው የሪጋ የአለም የጎዳና ላይ ሻምፒዮና የተለያዩ ድሎችን ማስመዝገብ ችለዋል።

በወንዶች የ 5ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት በሀጎስ ገብረሕይወት #ወርቅ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ #የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችለዋል።

ሀገራችን የአለም ሪከርድ በሰበረችበት የአንድ ማይል ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በሴቶች የ 5ኪ.ሜ ውድድር አትሌት እጅጋየሁ ታዬ #ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሯን አጠናቃለች።

የሜዳሊያ ሰንጠረዡን የሚመሩት ሀገራት እነማን ናቸው ?

1. ኢትዮጵያ :- ሁለት ወርቅ ፣ ሁለት ብር እና አንድ ነሐስ

2. ኬንያ :- አንድ ወርቅ ፣ አንድ ብር እና ሁለት ነሐስ

3. አሜሪካ :- አንድ ወርቅ እና አንድ ነሐስ

via @tikvahethsport

@tikvahethiopia