TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" 7 ስድተኞች ህይወታቸው አልፏል ፤ 9 ተጎድተዋል " - IOM

ታንዛኒያ ውስጥ በደረሰ አደጋ ስደተኞች ህይወታቸው አለፈ።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) በተባበሩት ታንዛኒያ ሪፐብሊክ ፤ ኒጆምቤ ክልል በደረሰ የመኪና አደጋ ስደተኞች ላይ የሞት እና አካል ጉዳት መድረሱን ባወጣው መግለጫ አሳውዋል።

ድርጅቱ አደጋው እንደደረሰ የታመነው እኤአ መስከረም 14 መሆኑን አመልክቷል። #ኢትዮጵያውያን ናቸው ተብለው የታሰቡ 29 ስደተኞችን የጫነ መኪና ወደ ዛምቢያ ድንበር ቱንዱማ በመጓዝ ላይ እያለ አደጋው መድረሱን ገልጿል።

በአደጋው 7 ስደተኞች እንደሞቱና 9ኙ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጿል። 13 ስድተኞች ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ብሏል።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በዚህ አሰቃቂ አደጋ ለተጎዱት ሁሉ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

ሰራተኞቹ በታንዛኒያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች ጋር በመሆን በቦታው ተገኝተው ስለሁኔታው የበለጠ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና በተቻለ መጠን ድጋፍ ለማድረግ እየሰሩ እንደሆነ አሳውቋል።

በኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም በውጭ ጉዳይ በኩል ጉዳዩን በተመለከተ የሚወጣ መረጃ / መግለጫ ካለ ተከታትለን እንልካለን።

@tikvahethiopia
#HaileCoffee

በብራይተን ነዋሪነታቸውን ያደረጉ የቀድሞ የእንግሊዝ አትሌቶች በኢትዮጵያዊው ጀግና አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ስም " ሀይሌ ኮፊ " የተሰኘ ቡና #ለሯጮች መሸጥ መጀመራቸው ተገልጿል።

" ሀይሌ ኮፊ " የሚል ስያሜን ያገኘው ይህ ቡና በቀድሞ የእንግሊዝ የማራቶን ሯጭ ሪቻርድ ኔርኩር ሀሳብ አመንጪነት ለገበያ መቅረቡ ታውቋል።

ሪቻርድ ኔርኩር ዘጠኝ አመታትን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በቆየበት ወቅት ከኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሀይሌ ጋር በነበረው ቅርበት ይህ የቢዝነስ ሀሳብ ሊመጣለት እንደቻለ ተገልጿል።

" ቡና በኢትዮጵያውያን ባህል ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው " ያለው ኔርኩር ሀይሌ በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ያለውን ስም በመጠቀም ቡናን ለሚያዘወትሩ አትሌቶች " ሀይሌ ኮፊን " እንደሚያቀርብ ገልጿል።

ለሽያጭ የሚቀረበው " ሀይሌ ኮፊ " ምርት " Premium Ethiopian Coffee " የሚል መገለጫ እንደሚኖረው ታውቋል።

" በሀይሌ ኮፊ " ሶስት የተለያዩ የቡና አይነትን ለሯጮች እንደሚቀርብ ሲገለፅ Champion’s Choice  ፣ Emperor's Delight እና Haile Blend እንደሚሰኙ ተገልጿል።

ሀይሌ ኮፊ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ለተጠቃሚዎች ለሽያጭ መቅረቡ ተዘግቧል።

Via @tikvahethsport    
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሩስያ ሩስያ ላልተወሰነ ጊዜ ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ወደ ውጭ መላክ አቆመች ፤ ይህ ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅእኖ ይኖራል ተብሎ ተሰግቷል። ሩስያ ፤ " የሀገር ውስጥ ገበያን ለማረጋጋት እንዲሁም የሀገር ውስጥ የነዳጅ ፍላጎትን ለማሻሻል " በሚል ከአራት የቀድሞ የሶቪየት ሕብረት አባላት ውጭ ወደ #ሁሉም_ሀገራት የነዳጅ ምርቶችን ቤንዚን እና ናፍጣ መላክን ለጊዜው አግዳለች። እገዳው…
#የነዳጅ_ዋጋ !

በዓለም ገበያ 1 በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከ3 ወራት በፊት 74 የአሜሪካ ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን 94.8 የአሜሪካ ዶላር ገብቷል።

የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ ይገኛል። ትላንት 97 ዶላር ደርሶም ነበር። ይህም እኤአ ከህዳር 2022 ወዲህ ከፍተኛው ጭማሪ ሆኖ ተመዝግቧል።

የዚህ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ #ምክንያት የፍላጎት መጨመር እና የድፍድፍ ዘይት አቅርቦቶች በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ነው ተብሏል።

ለአቅርቦት መቀነሱና ለዋጋ ንረቱ ደግሞ የ " OPEC+ " አባላት የሆኑት ሳዑዲ አረቢያና ሩስያ ከዚህ ቀደም ያሳለፏቸው ውሳኔዎች ትልቁን ድርሻ ይይዛል ተብሏል።

በርካታ በዘርፉ ላይ ያሉ ተንታኞች ዋጋው በቅርብ ጊዜ ከ100 ዶላር በላይ ሊደርስ እንደሚችል እየገለፁ ናቸው።

@tikvahethiopia
ቪዲዮ ፦ ከላይ የምትመለከቱት #በአሜሪካ ሀገር ፣ ፊላደልፊያ በአንድ የ " አይፎን ስቶር " ላይ ከቀናት በፊት የተፈፀመ ዘረፋ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው በርካታ #ጭምብል የለበሱ እና ያለበሱ ሰዎች የአፕል ስትሮን በኃይል ሰብረው ይገባሉ።

በኃላ ውስጥ የነበሩ ለእይታ የቀረቡ #ሁሉንም አዳዲሶቹን የ " አይፎን 15 " ምርቶች እና ሌሎች የአፕል ቴክኖሎጂ ውጤቶችን " free iPhone " እያሉ እየጮሁ ይወስዳሉ።

ከአፕል ስቶር ስልኮቹን ይዘው ከወጡ በኃላ አንድ ድምፅ ይሰማሉ ፤ ስልኩ አገልግሎት እንደማይሰጥ እንዲሁም ስልኩን የያዘው ሰው ላይ ክትትል እንደሚደረግ ስልኩ ላይ በተመለኩት ፅሁፍ ይረዳሉ።

በየአፕል ስቶር ውስጥ ለማሳያ የሚቀመጡት አይፎን ስልኮች ለሽያጭ ከሚቀርቡት አይፎኖች ላይ ከሚጫነው ሶፍትዌር በተለየ ልዩ ሶፍትዌር የሚጫንባቸው ናቸው።

ይህን ሲገነዘቡ " አይፎን 15 " ስልኮቹን ጥቅም እንዳይሰጡ አድርገው ወደ መሬት እየጣሉ #ይሰባብራሉ። የውሃ መውረጃ ትቦ ውስጥም ይጨምራሉ።

ፖሊስ ደርሶ በዘረፋው ላይ የተሳተፉትን በቁጥጥር እንዳዋለ ተነግሯል። በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን ፖሊስ አሳውቋል።

ድርጊቱ ብዙ የአሜሪካ ዜጎችን በማህበራዊ ሚዲያ እያናጋገረ እና እያወያየ ሲሆን አንዳንዶች በዘረፋ ድርጊት ፈፃሚዎች ላይ ላልቷል ያሉትን ህግ ሲተቹ ታይተዋል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በዚህ ሩጫ በበዛበት ዘመን የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችና የገንዘብ ዝውውሮችን ካሉበት ሆነው ለመፈፅም የአቢሲንያ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ አይነተኛ አማራጭ ነው።

በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት፣ የጉዞጎ ትኬት፣ የዲኤስ ቲቪ፣ የኢትዮ ቴሌኮም፣ የዌብ ስፕሪክስ ኢንተርኔት፣ የትምህርት ቤት፣ የዉሀ፣ ካናል ፕላስ፣ የዩኤስ ቪዛ ክፍያዎችን ይፈፅሙ እንዲሁም ገንዘብ ወደ አዋጭ፣ ቴሌብር፣ ኤም ፔሳና ኤም ፔሳ ትረስት አካውንት በቀላሉ ይላኩ!

https://t.iss.one/BoAEth
#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ ዉስጥ ያለዉ ህገወጥ እንቅስቃሴ ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር ሆኖ በሰራዉ ስራ ከፍተኛ ለዉጥ ቢታይም አሁንም ችግሮች መኖራቸዉ ተገለጸ።

በከተማዉ ባሉ የታክሲ መሳፈሪያና መዉረጃ አካባቢዎች የስልክ ነጠቃና ስርቆት እንዳማረራቸዉ የሚናገሩት ነዋሪዎቹ በዚህ መልክ የተዘረፉ ስልኮች በገበያ ዉስጥ በግልጽ ሲሸጡ እንደሚታይ ይናገራሉ።

አሁን ላይ የተሰረቁ ስልኮችን በግልጽ በከተማዉ ዉስጥ ባሉ የገበያ መግቢያዎች ሲሸጡ እንደሚታይ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ ይህ ጉዳይ ሀይ ሊባል እንደሚገባ በመግለፅ የሚመለከተዉ አካል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ላይ በቅርቡ መግለጫ የሰጠዉ  የከተማዉ ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ ሁኔታዎችን ለማስተካከል በአዲስ አደረጃጀትና ተልእኮ ከተማዋን የተሻለ ሰላም ያላት ለማድረግ  እንደሚሰራ  ገልጿል።

በቅርቡ ወደስልጣን የመጡት የሀዋሳ ከተማ ጸጥታ ጉዳይ ሀላፊዉ አቶ ወንድሙ ቶርባ ሁኔታዉን ለማስተካከል ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን በከተማዉ ነዋሪ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ባደረጉት ዉይይት ገልጸዋል።

ይህ የማህበረሰብና የፖሊስ የትብብር አንቅስቃሴና ስምሪት  በደመራ በአል በስፋት የተስተዋለ ሲሆን ወጣቶችና ፖሊስ በመቀናጀት ዉጤታማ ስራ ሲሰሩ መታየታቸዉን በቦታው የሚገኙ የቲኪቫህ ቤተሰቦች ተመልክተዋል።

@tikvahethiopia
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ " ጸሎተኛው ፣ ደጉ፣ ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል " ብሏል።

ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ከዚህ ዓለም ድካም እንዳረፉ ተገልጿል።

የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ ተወስኖ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
" የችግሩ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየከፋ ነው "

በአማራ ክልል ፣ በሰሜን ጎንደር 202 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

በዞኑ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺ ዜጎች መጎዳታቸው ተገልጿል።

የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ይፋ እንዳደረገው ፤ በዞኑ ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺህ ዜጎች ተጎድተዋል፤ 202 ሺህ ዜጎችም አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ከፅህፈት ቤቱ በተገኘው መረጃ ፦

- ጃናሞራ ፣ ጠለምት ፣ የበየዳ ወረዳዎችን ጨምሮ፣ ምሥራቅና ምዕራብ ጠለምትና የተወሰኑ የደባርቅ አካባቢዎች በድርቅ ተጎድተዋል፡፡

- ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ሳቢያ 6 ወረዳዎች ለድርቅ ተጋልጠዋል።

- በድርቁ ሳቢያ 19 ሺህ 500 ሄክታር ሰብል ጉዳት ደርሶበታል።

- በዝናብ እጥረት 103 ሺሕ እንስሳት ለድርቅ አደጋ የተጋለጡ ሲሆን 53 ሺሕ የሚደርሱ እንስሳት በድርቁ ሳቢያ #ሞተዋል

- በጠለምትና ጃናሞራ ወረዳዎች በድርቁ ምክንያት ከ4 ሺሕ በላይ ዜጎች ከአካባቢያቸው ለቀው ወደ ወረዳ ማዕከላት ሄደዋል።

- ዞኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ ለማቅረብ ጥረት በማድረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡

- በድርቁ አካባቢዎች ላይ ተላላፊ በሽታዎች በተለይም #የኮሌራ_በሽታ ተከስቷል።

- ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ ለሚገኙ ዜጎች አስቸኳይ የዕለት ምግብ፣ መድኃኒቶች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ውሃና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አስፈላጊ ነው።

- የችግሩ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየከፋ ነው። በድርቁ ሳቢያ ዜጎች ለከፋ ችግር እየተጋለጡ በመሆኑ ሁሉም አካላት እንዲረባረቡ ፤ መንግሥት፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ አጋር አካላት የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያቀርቡ መልዕክት ተላልፏል።

እስካሁን ምን ድጋፍ ተደረገ ? ፅ/ቤቱ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ክልሉ ከአንድ ሺሕ 500 ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ ማድረጉንና ድጋፉን 14 ሺሕ ዜጎች ማድረስ እንደተቻለ ገልጿል።

Via EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የችግሩ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየከፋ ነው " በአማራ ክልል ፣ በሰሜን ጎንደር 202 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል። በዞኑ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺ ዜጎች መጎዳታቸው ተገልጿል። የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ይፋ እንዳደረገው ፤ በዞኑ ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺህ ዜጎች ተጎድተዋል፤ 202 ሺህ ዜጎችም አስቸኳይ…
#ጃናሞራ

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር የሚገኘው የጃናሞራ ወረዳ አስተዳደር ከሰሞኑን ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፤ በወረዳው ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ 16 ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።

አብዛኞቹ የሞቱት ሴቶች እና አረጋውያን ናቸው።

አተትን ጨምሮ ሌሎች ወረርሽኞችም ተከስተዋል።

አርሶ አደሮች ተስፋ ቆርጠዋል ፤ እስካሁን 4 ሺህ የሚደርሱ አርሶ አደሮች የሄዱበት እንደማይታወቅ ተገልጿል። የወረዳ አመራሮች አርሶ አደሮችን ለማግኘት ሲንቀሳቀሱ ቤታቸው ተዘግቶ ነው የሚያገኙት።

በድርቁ ከ7500 በላይ የዳልጋ እና ጋማ ከብቶች ሞተዋል። የተረፉትም ደክመዋል ለገበያ እንኳን ሊቀርቡ አይችሉም።

ነዋሪዎች መንግሥት እንዲደርስላቸው ተማፅነዋል።

ወረዳው ያለውን አስከፊ ሁኔታ ለሚመለከታቸው አካላት ቢያሳውቅም ምላሽ እንዳላገኘ ገልጿል። ለበሽታ ለተጋለጡ ወገኖችም #መድሃኒት እንኳን ማቅረብ አልተቻለም።

@tikvahethiopia
GLOBAL_BANk_ETHIOPIA_3_VOICE_MAK_LAST_CHOIR_NEW_972023_GLOBAL_BANK
<unknown>
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ያሰራውን ሙዚቃዊ ብራንድ (Jingle) ይፋ አደረገ።

የባንካችን ሁለንተናዊ ለውጥና ራዕይ  እንዲሁም ለደንበኞቹ ያለውን ክብርና የላቀ አገልግሎት በሚገልፅ መልኩም አዲስ ሙዚቃዊ ብራንድ ( Jingle ) ለመላ ደንበኞቻችን ስናስተዋውቅ በታላቅ ደስታ ነው።

ሁሉን አቀፍ ለውጥ ማምጣት የቻለው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ስያሜውንና አስተሳሰቡን በሚያሳይና በሚመጥን መልኩ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ሳይለቅ አገልግሎቱ ዓለም አቀፋዊ ማድረግ ችሏል።

ተጋበዙልን!

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.iss.one/Globalbankethiopia123

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን