#HaileCoffee
በብራይተን ነዋሪነታቸውን ያደረጉ የቀድሞ የእንግሊዝ አትሌቶች በኢትዮጵያዊው ጀግና አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ስም " ሀይሌ ኮፊ " የተሰኘ ቡና #ለሯጮች መሸጥ መጀመራቸው ተገልጿል።
" ሀይሌ ኮፊ " የሚል ስያሜን ያገኘው ይህ ቡና በቀድሞ የእንግሊዝ የማራቶን ሯጭ ሪቻርድ ኔርኩር ሀሳብ አመንጪነት ለገበያ መቅረቡ ታውቋል።
ሪቻርድ ኔርኩር ዘጠኝ አመታትን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በቆየበት ወቅት ከኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሀይሌ ጋር በነበረው ቅርበት ይህ የቢዝነስ ሀሳብ ሊመጣለት እንደቻለ ተገልጿል።
" ቡና በኢትዮጵያውያን ባህል ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው " ያለው ኔርኩር ሀይሌ በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ያለውን ስም በመጠቀም ቡናን ለሚያዘወትሩ አትሌቶች " ሀይሌ ኮፊን " እንደሚያቀርብ ገልጿል።
ለሽያጭ የሚቀረበው " ሀይሌ ኮፊ " ምርት " Premium Ethiopian Coffee " የሚል መገለጫ እንደሚኖረው ታውቋል።
" በሀይሌ ኮፊ " ሶስት የተለያዩ የቡና አይነትን ለሯጮች እንደሚቀርብ ሲገለፅ Champion’s Choice ፣ Emperor's Delight እና Haile Blend እንደሚሰኙ ተገልጿል።
ሀይሌ ኮፊ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ለተጠቃሚዎች ለሽያጭ መቅረቡ ተዘግቧል።
Via @tikvahethsport