#ጋምቤላ
በጋምቤላ ክልል ወንዞች ሞልተው ባስከተሉት የውሃ መጥለቅለቅ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቀሉ።
በክልሉ በጋምቤላ ከተማ ጨምሮ በ9 ወረዳች ወንዞች ሞልተው ባስከተሉት መጥለቅለቅ ዜጎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
እንደ ክልሉ መግላጫ ፦
- የባሮ፣
- የአልዌሮ፣
- የጊሎና
- የአኮቦ ወንዞች ሞልተው በመፍሰሳቸው ነው በነዋሪች ላይ ጉዳት የደረሰው።
በክልሉ ደጋማው አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በኑዌር ዞን የሚገኙ አምስቱም ወረዳዎች፣ ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ጎግና ጆር ወረዳዎች ላይ የውሃ መጥለቅለቅ ተከስቷል።
የውሃ መጥለቅለቅ ከደረሰባቸው ወረዳዎች፤ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። ተፈናቃዮቹን ለጊዜው ደረቃማ በሆኑ አካባቢዎች እንዲጠለሉ ተደርጓል።
ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ለማድረግ የአደጋውን መጠን የመለየት ስራ እየተከናወነ ነው ተብሏል።
በቀጣይም የወንዞቹ ሙላት ሊጨምርና ከዚህ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጋምቤላ ክልል ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopia

#አማራ
ቤተሰቦቻቸው በአማራ ክልል የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በክልሉ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት በየዕለቱ የበርካታ ሰዎች ህይወት እያለፈ፣ ንብረት እየወደመ ፣ ቀድሞም የደቂቀው ኢኮኖሚና የኑሮ ሁኔታ እየባሰበት እየሄደ መሆኑን ገለፁ።
ለችግሮች መፍትሄ እንዲፈለግም ጠይቀዋል።
ስማቸውን መናገር ያልፈለጉ ቤተሰቦቻቸው ጎጃም ውስጥ እንደሚኖሩ የገለፁ አንድ የቤተሰባችን አባል፤ " ህዝቡ በሰላም እጦት መሰቃየት ከጀመረ ወራት ተቆጠሩ " ብለዋል።
እሳቸው ባላቸው መረጃም በጦርነቱ በርካታ ሲቪል ሰዎች ሰለባ እንደሆኑ ገልጸዋል።
ቤተሰቦቻቸው ባሉበት አካባቢ ያለው ግጭት አንዴ እየቀዘቀዘ ዳግም ደግሞ እያገረሸ ወራት መቆጠሩን በመግለፅ ሁኔታው ለእርሻ፣ ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አዳጋች እንደሆነና በዚህም ህዝቡ ሁለንተናዊ ስቃይ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
" ያለፉት ዓመታት ጦርነት ያሳጣንን ማስታወስ ይገባል " ያሉት እኚሁ ግለሰብ በአስቸኳይ ሰላማዊ መፍትሄ ተገኝቶ ህዝቡ በተለይ ገበሬው ወደቀደመው ስራ ካልተመለሰ ቀጣይ የሚመጣው ቀውስ እጅግ የከፋ ነው ብለዋል።
ደብረ ማርቆስ ውስጥ እናት እና አባቷ እንዳሉ የገለፀች የአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ስለ ቤተሰቦቿ መጨነቅ ከጀመረች ወራት እንዳለፈ ተናግራለች።
" ዘውትር እንቅልፍ የለኝም፤ ከዛሬ ነገ ምን ይፈጠራል እያልኩኝ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ከወደኩ ይኸው ሳምንታት አልፈዋል " ብላለች።
ጦርነቱ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ከመሆኑም በላይ ኑሮ ውድነቱን እያባባሰው ነው የምትለው ይህች የቤተሰባችን አባል መፍትሄ እንዲፈለግ ርብርብ ይደረግ ስትል ተማፅናለች።
ሌላው አንድ በአማራ ክልል ቤተሰቦቹ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ እሱን ጨምሮ ሌሎችም ያለ አንዳች ጥፋት " የፋኖ ደጋፊ ናችሁ " በሚል ለእስር ተዳርገው እንደነበር በመግለፅ ጦርነቱ እየፈጠረው ያለው ቀውስ ሁለንተናዊ ነው ብሏል።
በርካቶች አሁንም በጥርጣሬ ብቻ በእስር እየማቀቁ፣ ቤተሰብም እየተሰቃየ ነው፣ ይህንን ስሜት በቦታው ላይ ካልሆነ ማንም አይረዳውምና ስቃዩና መከራው ያበቃ ዘንድ መፍትሄ እንዲፈለግ ተማፅኗል።
ሌላው አንድ የሚወዳቸውን ሰዎች በዚሁ ጦርነት የተነጠቀ የቤተሰባችን አባል #አሉታዊ ነው ያለውን የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ የተቃወመ ሲሆን ለተገደሉት ለተገፉት ወገኖች ፍትህ ጠይቋል።
" #አንዳንዶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብቻ ቀኑን ሙሉ ሲሰዳደቡ፣ ሲበሻሸቁ፣ በዘፈን፣ በድለቃ ፣ በወሬ የሚጮሁ ከግጭት ቀጠናው ፍፁም የራቁ፣ ወንድም እህታቸውን እናት አባታቸውን ያላጡ፣ የሰላምን አየር እየተነፈሱ ያሉ፤ ጦርነት ምን እንደሆነ ፈፅሞ የማይያውቁ ናቸው " ብሏል።
" የአማራ ህዝብ ኢንተርኔት ካጣ ወራት አልፎታል፣ የሰላም እጦቱ ሰለባ እሱ ነው፤ #አንዳንዶቹ አንድም ቀን የጥይት ድምፅ ሰምተው የማያውቁ፣ ሰው ያልሞተባቸው ናቸው " ሲል ተችቷል።
ከምንም በላይ እየተካሄደ ባለው ግጭት ያለ ሃጢያታቸው ነፍሳቸውን ለተነጠቁ ንፁሃን ወገኖች፣ በሀዘን ላይ ለሚገኙ ቤተሰቦች፣ ለተጎዱ፣ ለተገፉ ወገኖች ሁሉ ፍትሕ ይስፈን፤ ንፁሃንን የገደሉ፣ ያስገደሉ፣ ትዕዛዝ ያስተላለፉ ሁሉም ጥፋተኞች ይጠየቁ፤ በዚህ ጉዳይ ሁሉም ድምፁን ሊያሰማ ይገባል ሲል አሳስቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይም ከቤተሰቦቹ የሚደርሱትን መልዕክቶች እያሰባሰበ ያቀርባል።

" የአገዛዙ አካሄድ ያልተስማማቸው ካሉ ቁጭ ብለው እንዲነጋገሩ ከማንም ሳንወግን እንዲነጋገሩና ሰላም እንዲገነባ እንሰራለን " - ዶ/ር ዮናስ አዳዬ
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጠው ቃለ ፤ የኮሚሽኑ ዋናው መርህ አካታችነት እንደመሆኑ በሀገራዊ ምክክር መድረኩ የተለያየ ሃሳብ እና አቋም ያላቸው ወገኖች ሁሉ መሳተፍ አለባቸው ብሏል።
በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) / መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው ታጣቂ ቡድን በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እንዲሳተፍ ለማድረግ ከተለያዩ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳውቋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ፤ " በኦሮሚያ ክልል ካሉ ወንድሞቻችን ጋር በተቻለ መጠን እነሱ ወክሏቸዋል ተብለው የታሰቡትን በኦሮሚያ ውስጥ ያሉትን በአባገዳዎች አማካኝነት ፣ በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት ከነሱ ጋር በጅማ ፣በአዳማ ከተማዎች እንዴት አድርገን ሰላማዊ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሁሉም የሚሳተፉበትን መንገድ እንፍጠር በሚለው ስንመከከር ነበር " ብለዋል።
" ከሽማግሌዎች ጋር ፣ከሲቪል ማህበራት ጋር ፣ ከምሁራን ጋር ባገኘነው አጋጣሚዎች ሁሉ ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ማምጣትን ባህል ለማድረግ እየሰራን ነው ጥረታችን ይቀጥላል ፤ የክልሉ መንግሥት በጣም ደጋፊ ነው ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ደጋፊዎች ናቸው ፣ ሲቪክ ማህበራትም እየጣሩ ነው " ሲሉ አክለዋል።
ከዚህ ባለፈ ኮሚሽኑ ፤ በአማራ ክልል ከመንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው " ፋኖ " የሀገራዊ ምክክሩ አካል እንዲሆን ጥረት እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።
ዶ/ር ዮናስ " ከምሁራን ጋር፣ ከሲቪክ ማህበራት ጋር ፣ ከክልል መንግሥታት ጋር ፣ ሽማግሌዎችን እያማከርን እየሰራን ነው " ብለዋል።
" እነዚህ (ኦሮሚያና አማራ ክልል ያሉ ግጭቶች) ጎልተው ወደሚዲያው ስለወጡ ነው እንጂ ሌሎችም ካሉ አንድ ላይ ተመካክሮ ፣ ችግሮቻችንን ልዩነቶቻችንን በመመካከር ለመፍታት ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እንዲመጣ ማድረግ ነው ስራችን " ሲሉ ተናግረዋል።
ችግሮች እንዲፈቱ በኢትዮጵያ ጥያቄ ያለው ማንኛውም አካል ከዚህ ሀገራዊ ምክክር ሊገለል እንደማይገባ የተናገሩት ዶ/ር ዮናስ ልዩነት አለን የሚሉ ሁሉ ችግሮችን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።
" የተለያዩ የአገዛዙ አካሄድ ያልተስማማቸው ካሉ ያን አለመስማማታቸውን ቁጭ ብለው ለመነጋገር እኛ ደግሞ ከማንም ሳንወግን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በሚያካትት መልኩ ፣ ሁሉንም በማነጋገር በመመካከር መጨረሻም ላይ ለልዩነቶች መሰረት የሆኑትን ነቅሰን በማውጣት ወደአንድነት ለመምጣትና ሰላም ለመገንባት ፣ ሀገርን ለመገንባት ነው ትልቁን ጥሪያችንን እያቀረብን ያለነው " ብለዋል።
ኮሚሽኑ በቀጣይ ለሚደረገ ሀገራዊ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ አስተባባሪዎች ፣ እና ተሳታፊዎችን የመለየት ስራ በአ/አ ጨምሮ በክልሎች እየሰራ ነው።
በትግራይ ክልልም በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ውይይት እንዳጀመር ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ደብዳቤ ገብቶ ምላሽ እየተጠበቀ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ መገለፁን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

#Bank_of_Abyssinia
የአቢሲንያ ባንክን የተለያዩ አገልግሎቶች አጠቃቀም እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ከዚህ ጋር የተያያዘውን ሊንክ በመጠቀም ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.iss.one/BoAEth

TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#ጣልያን
በስደተኞች ቁጥር መጨመር እየተቸገረ ያለው የጣሊያን መንግስት ትናላንት ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ስደተኞች የሚታሰሩበት ጊዜ እንዲረዝም እና ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ተይዘው እንዲመለሱ የሚያደርግ ህግ አጽድቋል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው ባለፈው ሳምንት 10ሺ የሚሆኑ ስደኞች በጣሊያኗ ላምፔዱሳ ወደብ መድረሳቸውን ተከትሎ ነው።
የስደተኞቹ ወደ ጣሊያን መጉረፍ ህገወጥ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ቃል ለገቡት የቀኝ ዘመም ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ትልቅ ችግር እንደፈጠረባቸው ተነግሯል።
ሜሎኒ ፤ በካቢኔ ስብሰብ መጀመሪያ ላይ እንደገለጹት ወደ ሀገራቸው ለመመስ የሚጠባቀቁ ስደተኞች ከ6 እስከ 18 ወራት እስራት ይጠብቃቸዋል።
የመንግስት ምንጮች ካቢኔው መንግስት ያቀረበውን ህግ ማጽደቁን እና ራቅ ባሉ ቦታቸው እስርቤቶች እንደሚሰሩ መወሰኑን ገልጸዋል።
ሜሎኒ ቀደም ሲል በነበሩት የስደተኞች ፖሊሲዎች ምክንያት የተዳከሙትን የማቆያ ቦታዎች ወይም እስርቤቶችን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።
ህገወጥ ስደተኞች በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው የማይላኩ ከሆነ የሚቆዩበት እስርቤት ይኖራል ያሉት ሜሎኒ ስደተኞችን ለማቆም ከዚህ በፊት የተደረጉ ሙከራዎች ሳይሳኩ መቅረታቸውን ገልጸዋል።
የጣሊያን ባለስልጣናት አብዛኞቹ ስደተኞች በኢኮኖሚ ምክንያት የሚሰደዱ ስለሆነ ጥገኝነት ለመጠየቅ መስፈርት አያሟሉም ይላሉ።
ሜሎኒ በካቢኔ ስብሰብ መጀመሪያ ላይ እንደገለጹት ወደ ሀገራቸው ለመመስ የሚጠባቀቁ ስደተኞች ከ6 እስከ 18 ወራት እስራት ይጠብቃቸዋል።
መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።

" ክትትል እየተደረገ ነው ፤ በወረርሽኝ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች አሉ " - ወ/ሮ ሰላማዊት ግርማቸው (በኢሰመኮ የሰሜንና ማዕከላዊ ሪጅን የክትትልና ምርመራ ዳይሬክተር) በኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ በማቆያና በፓሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ ወገኖች እንዳሉና በእነዚህ ወገኖች የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ላይ ክትትል እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።…
" በመጠለያ ጣቢያው ከነበሩ ሰዎች የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአብዛኛው ውሎ እና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ (በተለምዶ አጠራሩ ጎዳና ተዳዳሪዎች ተብለው የሚታወቁ) ሰዎች ከጎዳና ላይ ተነስተው እንዲቆዩ የሚደረግበት በሸገር ከተማ፣ ሲዳ አዋሽ ወረዳ በተለምዶ " ሲዳማ አዋሽ " በመባል የሚታወቅ አካባቢ የሚገኘው ጊዜያዊ ማቆያ ማእከል ቦታን ጨምሮ በአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕፃናት እና ማኅበራዊ ቢሮ ሥር የሚተዳደሩ ማእከላትን ቦታዎችን በመጎብኘት እና ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።
ኮሚሽኑ ፤ ነሐሴ 24 እንዲሁም በጳጉሜን 2 እና 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በዚህ ማቆያ ማእከል ቦታ ካደረገው ጉብኝት በኋል መግለጫ ልኮልናል።
ኮሚሽኑ ምን አሉ ?
- በማቆያ ማእከሉ የሚገኙት ሰዎች ውሎ እና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎች ሲሆኑ አረጋውያን፣ ሕፃናት፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞችም ይገኙበታል።
- እነዚህ በተለያየ ጊዜ ወደ ማእከሉ እንዲመጡ የተደረጉ ሰዎች ብዛት በየጊዜው ተለዋዋጭ ሲሆን፤ በሺዎች የሚገመቱ ሰዎች በማቆያ ማእከሉ ውስጥ ይገኙ እንደነበርና ኮሚሽኑ ክትትል ያደረገበትን ጊዜ ተከትሎ እና በዚህ ሪፖርት ዝግጅት ወቅት ቁጥሩ ከግማሽ በላይ ቀንሶ በመቶዎች የሚገመቱ ሰዎች መኖራቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡
- የማቆያ ማእከሉ አስተባባሪዎች ለኮሚሽኑ እንዳስረዱት የጊዜያዊ ማእከሉ ዋነኛ ዓላማ ከጎዳና ላይ እንዲነሱ የተደረጉትን ሰዎች በመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም በማገዝ ወደ መጡባቸው አካባቢዎች እንዲመለሱ እና ከጎዳና ላይ ውሎና አዳር እንዲወጡ ማድረግ መሆኑንና በዚሁ መሠረት በተለያየ ጊዜ ብዙ ሰዎች ወደ መጡባቸው አካባቢዎች እንዲመለሱ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
- በማእከሉ ከሚገኙት ሰዎች ውስጥ 29 በቀን ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች፣ የጥበቃ እና የግንባታ ሠራተኞች እንዲሁም ሴቶችና ሕፃናት ጳጉሜን 3 ቀን 2015 ዓ.ም. እንዲለቀቁ እንደተደረገ የማእከሉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል።
- በማቆያ ማእከሉ ለሚገኙ ሰዎች ምግብ በቀን 3 ጊዜ እና የመጠጥ ውሃ የሚቀርብ ሲሆን በአንጻሩ ይህ ጊዜያዊ ማቆያ ማእከል ለሰዎች መለያ ወይም ማቆያ ተብሎ የተዘጋጀና የተደራጀ ሳይሆን፤ ለኢንዱስትሪ ዕቃዎች ማከማቻ ተዘጋጅቶ የነበረ ስፍራ በጊዜያዊ መለያ ጣቢያነት እንዲያገለግል የተደረገ ነው፡፡ የተሟላ መሠረተ ልማት የሌለውና ለተፈለገበት ዓላማ ምቹ ባለመሆኑ በጣቢያው የሚገኙ ሰዎችን ሰብአዊ ክብር የጠበቀ አያያዝ አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡
- የተሟላ የንጽሕና ቤቶች አለመኖራቸው እንዲሁም ለግል ንጽሕና መጠበቂያ የሚሆን የውሃና የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦት፣ የመኝታ አልጋ፣ ፍራሽና አልባሳት አለመኖራቸው፣ ለማደሪያ የተዘጋጀው ቦታ በቂ አየርና የፀሐይ ብርሃን የማያገኝ መሆኑ እና ከፍተኛ የንጽሕና ጉድለት ኮሚሽኑ ከተመለከታቸው ችግሮች ውስጥ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።
- በማቆያ ማእከሉ በቅርቡ በተባይ የሚተላለፍ ሕመም መከሰቱን ተከትሎ ለተላላፊ በሽታው የተጋለጡ ሰዎች ወደ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና እንዲሰጥ ተደርጓል።
- የተከሰተው ተላላፊ በሽታ በተባይ (በቅማል) የሚመጣ የተስቦ በሽታ (Relapsing fever) መሆኑን፣ በመጠለያ ጣቢያው ከነበሩ ሰዎች መካከል 190 ሰዎች በሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት ያገኙ መሆኑን እና ክትትሉ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ የ3 ሰዎች ሕይወት ያለፈ መሆኑን እና 3 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ሕክምና እያገኙ እንደነበር ከሕክምና ተቋሙ ማወቅ ተችሏል።
(ከኢሰመኮ የተላከን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#Tigray
ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ ወደሌሎች ክልሎች በተስፋፋው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት " በሺዎች የሚቆጠሩ " የትግራይ ተዋጊዎች መሞታቸው፣ ሌሎች በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸዉ የክልሉ ባለስልጣናት ማስታወቃቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዳስታወቀዉ በጦርነቱ ለሞቱ የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት፣ ቤተሰቦቻቸው #በቅርቡ በይፋ መርዶ ይነገራቸዋል።
ዛሬ በመቐለ ከተማ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ማእከል ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ንግግር ያደረጉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ ቁጥሩን በትክክል ባይጠቅሱም " በሺዎች የሚቆጠሩ " ያልዋቸው የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት በሁለት ዓመቱ ጦርነት መሞታቸውን አረጋግጠዋል።
የሟች ቤተሰቦችን ከማርዳት በተጨማሪ መስተዳድራቸዉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።
መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ዛሬ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፣ ሶዶ ወረዳ በአናቲ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 4 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው።
የሶዶ ወረዳ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ፍሰት ቁጥጥር ማስተባበሪያ በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12 ሰአት ላይ ነው አደጋው የደረሰው።
አደጋው የህዝብ ማመላለሻ FSR የሰሌዳ ቁጥር " ደቡብ 13955 " የሆነ 49 ሰዎችን ጭኖ ከአዲስ አበባ እየመጣ ከሆሳዕና ወደ አዲስ አበባ የሚሄድ የሰሌዳ ቁጥሩ " B-20669 " ላንድ ክሮዘር መኪና ጋር በሶዶ ወረዳ አናቲ ቀበሌ በመጋጨቱ የተፈጠረ ነው።
በዚህም አደጋው የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉና 4 ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።
ፖሊስ አደጋው የተከሰተበት ሰአት የአየር ንብረቱ ጭጋጋማ እንዲሁም አደጋ የደረሰበት አካባቢ መንገዱ ብልሽት ያለበት መሆኑን ገልጿል።
ይህ ቦታ በየጊዜው አደጋ እንደሚደርስበትና በተደጋጋሚ በትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት የሚቀጥፍበት ፣ ንብረትም የሚወድመት መሆኑ ተጠቁሟል። በመሆኑም አሽከርካሪዎች ከፍጥነት በላይ ባለማሽከርከር ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ፖሊስ ማሳሰቡን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።
በተያያዘ መረጃ ፤ በዚህ እጅግ አሳዛኝ የትራፊክ አደጋ ፤ የሆሳዕና ከተማ እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን መሪ እና አገልጋይ ዮናስ ዱባለን ጨምሮ አብረዋቸው የነበሩ ሁለት ጓደኞቻቸው ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።
በዚህም የሆሳዕና ከተማ ምዕመናን መሪር ሀዘን ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።