TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ከተጎጂዎች መካከል 30,427 ህፃናት ናቸው። የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደርሷል ” - ሴቭ ዘ ቺልድረን በሶማሌ ክልል ከተከሰተ የወራት ያለፈው የጎርፍ አደጋ የውሃ መጠኑ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም ትንበያዎች የሚያመለክቱት በመጪው የዝናብ ወቅት ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንዲሚችል ስለሆነ፣ ህብረተሰቡም አሁንም ካለፈው የጎርፍ አደጋ ገና እያገገመ በመሆኑ፣ ትልቅ ፈተናና ስጋት መፍጠሩን በቦታው የሚገኘው…
#SavetheChildren

“ በሚያሳዝን ሁኔታ 70 ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸውን አጥተዋል። 9 ሰዎች በኩፍኝ ሞተዋል ” - የህጻናት አድን ድርጅት

በሶማሌ ክልል በተለይም #የጎርፍ_አደጋ በደረሰባቸው ወረዳዎች በተፈናቀሉ ወገኖች የተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሆነ የክልሉ የህጻናት አድን ድርጅት (Save the children) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የድርጅቱ ምሥራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አህመድ ፣ የኮሌራ ወረርሽኙ እንደቀጠለ መሆኑን በሴፕተምበር 2023 ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በድምሩ 7, 480 ሰዎች እንደተጎዱ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ በሰጡት ቃል፣ “ በሚያሳዝን ሁኔታ 70 ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸውን አጥተዋል። 9 ሰዎች ደግሞ በኩፍኝ ሞተዋል ” ብለዋል።

በተጨማሪም ከ2024 መጀመሪያ ጀምሮ 533 ሰዎች በኩፍኝ በሽታ እንደተያዙ፣ 9ኙ ሰዎች ለሞት የተዳረጉት በጎዴ ከተማ፣ ጎዴ ወረዳ፣ በራኖ አካባቢዎች መሆኑን አስረድተዋል።

ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ምንድናቸው ?

📣 በጎርፍ ለተጎዳ ማህበረሰብ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረግ ምላሽ፣ የአደጋ ጊዜ መጠለያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ለማደረግ አቅርቦቶችን ማጎልበት። የኮሌራ ክትባቶች ከፍተኛ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች መስጠት ይገባል።

📣 የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ መሠረታዊ እና አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ወሳኝ በሆኑ የጤና ተቋማት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ በመገንዘብ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የጤና መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ መዋዕለ ነዋይ ሊፈስ ይገባል።

📣 #ህፃናት በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሆናቸው ልዩ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል። 

#ጥሪ

(አቶ አብዲራዛቅ አህመድ)

" ለለጋሽ ማህበረሰቡ አንድ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ። ወረርሽኝ እና ተደጋጋሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚያመጣውን ከፍተኛ ጉዳትና ተጽዕኖ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመቀነስ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia