TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ከጥቂት ቀናት በፊት አገልግሎታቸው እንዲገደብ የተደረጉት የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዛሬም አገልግሎታቸው ወደ ቦታው እንዳልተመለሰ ለመረዳት ታችሏል። #ቴሌግራም ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አገልግሎታቸው እንዲገደብ ከተደረገ ቀናት ያለፉ ሲሆን ጉዳዩን በተመለከተ ያብራራ/ያሳወቀ የለም። የአገልግሎት ገደቡ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች (ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም…
#ETHIOPIA

በኢትዮጵያ የማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ገደብ ከተገደረገባቸው ስድስተኛ ቀኑን ይዟል።

" #ቴሌግራም " ን ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ መገናኛዎች ምክንያቱ በግልፅ ወይም በይፋ ባልተነገረበት ሁኔታ ገደብ ከተደረገባቸው ስድስተኛ ቀን ሆኗል።

ይህ መልዕክት ተፅፎ እስከተላከበት ሰዓት ድረስ አገልግሎቶቹ ያልተመለሱ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች " ኢትዮ ቴሌኮም " እና " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " አማካኝነት አገልግሎት ማግኘት አልተቻለም።

የአገልግሎት ገደብን በተመለከተ " በዚህ ምክንያት ነው ፤ ለዚህን ያህል ጊዜም ይቆያል " ብሎ ያብራራ አካል እስካሁን ብቅ አላለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ቤተሰቦቹ ለማጣራት ባደረገው ጥረት በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ኢትዮ ቴሌኮም "  ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ ፣ ዩትዩብ የመሳሰሉት የማህበራዊ መገናኛዎች አገልግሎት እየሰጡ የማይገኙ ሲሆን #ትዊተር፣  #ኢንስታግራም እና #ዋትስአፕ ገደብ ሳይደረግባቸው አገልግሎት እየሰጡ ነው።

ምንም እንኳን በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ አገልግሎቶች ላይ ገደብ ተጥሎ ቢገኝም በVPN አገልግሎቱን ማስቀጠል ይቻላል፤ ከዚህ ቀደም መሰል እርምጃዎች ከተወሰዱበት ጊዜ አንፃር ሲታይ በዚህኛው ከፍተኛ የሰው ቁጥር አገልግሎት ለማግኘት VPN የመጠቀም ሁኔታው መጨመሩን ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ለመረዳት ችለናል።

@tikvahethiopia
#AI

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች የእርቃን ምስሎች ስፔን ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠሩ ሲሆን ፖሊስ ምርመራ ላይ ነው።

በደቡባዊ ስፔን ውስጥ የምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎች ከእነርሱ እውቅና ውጭ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተዘዋወሩ በኋላ ድንጋጤ ውስጥ ገብታለች ሲል ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

እርቃን ምስሎቹ የተሰሩት ሙሉ ልብስ ለብሰው የተነሱትን የታዳጊዎቹን ፎቶ በመጠቀም ነው።

በርካታ ምስሎቹ የተወሰዱትም ከታዳጊዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ነው።

ምስሎቹ ከተወሰዱ በኋላም አንድ ግለሰብ እርቃኑን ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ምናባዊ ምስል የሚፈጥር መተግበሪያ በመጠቀም የታዳጊዎቹ ምስል እርቃን እንዲቀር ተደርጓል።

እስካሁን ዕድሜያቸው በ11 እና በ17 ዓመት መካከል የሚገኙ 20 ታዳጊ ሴቶች፣ የዚህ ድርጊት ሰለባ መሆናቸውን በመግለጽ በደቡብ ምዕራብ ግዛቷ ባዳጆዝ ውስጥ በምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ እና አቅራቢያው ሪፖርት አድርገዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ የተጋሩት ሐሰተኛ የእርቃን ምስሎች በታዳጊ ሴቶቹ ላይ የተለያዩ ተፅዕኖዎችን አሳድረዋል።

የተወሰኑ ታዳጊዎች ከቤታቸው ለመውጣት እንደተሳቀቁ ተነግሯል።

ይህ ጉዳይ ወደ አደባባይ የወጣው ከታዳጊዎቹ ሴቶች መካከል የአንዷ እናት በሆነችው የማሕጸን ሐኪም ማሪያም አል አዲብ ምክንያት ነው።

አዲብ ማኅበራዊ ሚዲያዋን በመጠቀም ባወጣችው መልዕክት ምክንያት ጉዳዩ የስፔን ሕዝብ መነጋጋሪያ መሆን ችሏል።

አዲብ ታዳጊ ሴቶችንና ወላጆችን ለማረጋጋት ስትል በማኅበራዊ ሚዲያ ባጋራችው ቪዲዮ " የወጡት የAI ምስሎች የተፈጠሩት በበጋ ወቅት ቢሆንም ጉዳዩ ወደ አደባባይ የወጣው በቅርብ ቀናት ነው " ብላለች።

" ምን ያህል ሕጻናት ምስሎቹ እንደነበራቸው አናውቅም። ምስሎቹ የወሲብ ፊልም በሚጫንባቸው ገጾች ላይ ተጭነው እንደሆነም አናውቅም ነበር። ይህ ሁሉ ስጋት ነበረብን " ብላለች።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎችን ባማውጣት የተጠረጠሩ ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 14 የሚደርስ ነው።

ፖሊስ ድርጊቱን እየመረመረ ሲሆን ምስሎቹን በመፍጠር ሒደት ውስጥ አሊያም በማኅበራዊ ሚዲያዎቹ #ዋትስአፕ እና #ቴሌግራም በማጋራት ተሳትፈዋል ያላቸውን ቢያንስ አስራ አንድ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ታዳጊ ወንዶችን መለየቱን አስታውቋል።

መርማሪዎች ታዳጊ ወንዶቹ ሐሰተኛ ምስሎችን በመጠቀም ታዳጊ ሴቶቹን #በማስፈራራት ማግኘት የፈለጉት ነገር ስለመኖሩ ለማወቅ ምርመራ እያካሄዱ ነው።

#BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጠንቀቁ⚠️ በምስሉ የተያያዙት በኦንላይን " ቀላል በሆነ ስራ ብዙ ትርፍ ታገኛላችሁ " በሚል #የማጭበርበር ስራ ተታለው ገንዘባቸውን የላኩ ሰዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ማስረጃ እና ያጨብረበሯቸውን አካላት የቴሌግራምና የዋትአፕ አድራሻ የሚያሳይ ነው። " ቀላል ስራ፣ ብዙ ትርፍ የሚያስገኝ ስራ " በሚል ከ65 ሺህ ብር እስከ 600 ሺህ ብር የተበሉ አሉ። ምንም እንኳን አጨብረባሪዎቹ በውጭ ሀገር…
#ተጠንቀቁ ⚠️

ከኦንላይ ዘራፊና አጭበርባሪዎች እራሳችሁን ጠብቁ።

ነገሩ እንዲህ ነው ...

ገንዘባቸውን ኦንላይን ተጭበርብረው የተበሉ ግለሰቦች መጀመሪያ በማያወቁት የውጭ ሀገር ስልክ ቁጥር በ #ዋትስአፕ / በ #ቴሌግራም መልዕክት ይደርሳቸዋል። ስልካቸውን / username እንዴት እንደሚያገኙት ባይታወቅም።

የሚደርሳቸው መልዕክት " ጥሩ የስራ እድል እንደሆነ ፣ በትንሽ ስራም ብዙ ትርፍ እንደሚያገኙ ፣ ይህ እድል ለነሱ የተመቻቸ " እንደሆነ የሚገልጽ ነው።

ቅድመ ክፍያ እንደሌለው ፤ ከ100 ብር አንስቶ እስከ 50 ሺህ ብር በቀን የሚያስገኝ እንደሆነም መልዕክቱ ይገልጻል።

እነዚህ አጭበርባሪዎች የሚያጭበረብሯቸው ሰዎች የሚያናግሩበት መንገድ ፍፁም ትህትና የተሞላበትና ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ስለሆነ በተበዳይ ዘንድ ጥርጣሬ እንዳይጫር ያደርጋሉ።

ልክ የማግባባት ስራቸውን ከሰሩ በኃላ ትንሽ ተልዕኮ ሊሰጧቸው እንደሆነ በመግለፅ ወደ " ጎግል ማፕ/ ሎኬሽን " ገብተው ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አድራሻ ስር ጥሩ አስተያየት እንዲሰጡ ያዟቸዋል። (ይህ ከማጭበርበሪያ መንገድ አንዱ እንጂ ብቸኛው አይደለም)

የሚጭበረበረውም ሰው እጅግ በጣም ቀለል ያለ ስራ ስለሆነ የተሰጠውን ተልዕኮ መወጣቱን የሚገልጽ screenshot ለአጭበርባሪዎቹ  ይልካል። እነሱም አካውንቱን ይጠይቃሉ።

ከዚህ በኃላ ነው ዋናው ጨዋታ የሚጀመረው።

ሰዎቹ ለተሰራው ስራ ክፍያ በሚል ከ300 - 1,000 ብር ከዚህም ከፍ ያለ ገንዘብ ያስገባሉ። ይህ ሰዎችን የማሳመኛና እንዳይጠራጠሩ ማድረጊያ መንገዳቸው ነው።

ይቀጥሉና ታስክ ይሰጣችኋል ስሩ ይላሉ። በተሰራው ስራ ልክም የተወሰነ ገንዘብ ይልካሉ። ይህ እንደ ሰውየው የመክፈል አቅም እየተገመገመ የሚደረግ ነው።

በዚህ መኃል ላይ " ኮሜርሻል ቤኔፊት " የሚል ነገር ያመጣሉ ይኸውም ከ1,000 ብር እስከ 1,000,000 ብር ሰዎች እንዲያስገቡ የሚጠይቅ ነው። ሰዎች ባስገቡት ብር ልክም በሰሩት ቀላል ስራ በፐርሰንት ትርፍ እንዳለው ይነገራቸዋል።

ለምሳሌ ፦ የሚጭበረበረው ሰው በዚህ ማታለያ ተታሎ 1000 ብር ቢያስገባ ሰዎቹ መልሰው በደቂቃ ውስጥ 1500 ብር አድርገው ያስገባሉ። (ይህ አንዱ የማሳመኛ መንገዳቸው ነው)

በዚህም የሚጭበረበረው ሰው ብሩን ከፍ በማድረግ ብዙ ትርፍ ለማግኘት ሲል በዛ እያደረገ ብር ይልካላቸዋል።

የተጭበርባሪውን ሰው የመክፍል አቅም ገምግመው አጭበርባሪዎቹ የተላከው ብር ላይ 500ም ይሁን 5000 ብር ጨምረውበት መልሰው ይልካሉ። (ይህን እድታምኗቸውና ብዙ ብር እንድታስገቡ ማሳመኛ ነው)

ድጋሚ ሌሎች ስራዎዥ ይላሉ በዚህም ከፍ ያለ ብር እንድታስገቡ ያደርጋሉ። የላካችሁትን ብር እንዳታጡ የሚሳጣችሁን ስራ እንድትወጡ ይጠየቃል። እናተም ብራችሁ ተበልቶ እንዳይቀር የብሩን መጠን ከፍ ወደማድረግ ትሄዳላችሁ። (በዚህ ሁሉ ሂደት ግን ሰዎቹ የምክፈል አቅማችሁን እያጠኑና ከፍ ያለ ብር ከቻሉ እስከ #ሚሊዮን ለመቀበል ጥረት ያደርጋሉ ስለሆነም በመሃል በመሃል የሰራችሁበትን እያሉ ያራሳችሁን ብር መልሰው ይልኩላችኃል)

የመክፈል አቅማችሁንም አይተው ለዚህ ማጭበርበር ስራ ታልሞ ብቻ ወደ ተከፈተው ግሩፕ እንድትገቡ ይደረጋል። (ሁሉም ግሩፑ ውስጥ ያለው አካውንት የአጭበርባሪዎቹ ነው)

እንዲህ እንዲህ እያለ በዛ ያለ ብር ከፈፀማችሁ በኃላ ስህተት ሰርታችኋልና እሱን ለማረም ስራችሁን ቀጥሉ ይላሉ። እናተም ብራችሁን ላለማጣት ውስብሰብ ችግር ውስጥ ትወድቃላችሁ።

በመጨረሻም እየተጭበረበራችሁ እንደሆነ ስታውቁ ታቆማላችሁ። ብራችሁም መና ሆኖ ይቀራል። ሰዎቹ ግን ብር አስገቡ ያኛውን ብር ለማስመለስ ማለታቸውን ይቀጥላሉ።

ብር የሚያስልኩት ኢትዮጵያ ባለ ሰው አካውንት ነው። 

በዚህ መንገድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባጣራው ብቻ ከ150 ሺህ ብር እስከ 600 ሺህ ብር የተበሉ አሉ። ይህም የሰዎችን ህይወት አመሰቃቅሏል።

ለምሳሌ ፦ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ሆነው ስማቸውን በይፋ መግለፅ የሚያስፈልግ ሰዎች #የተጭበረበሩት የገንዘብ መጠን እንደሚከተለው ቀርቧል ፦
1. 600 ሺህ ብር
2. 470 ሺህ ብር
3. 300 ሺህ ብር
4. 300 ሺህ ብር
5. 150 ሺህ ብር
6. 150 ሺህ ብር
7. 100 ሺህ ብር
8. 80 ሺህ ብር
9. 80 ሺህ ብር
10. 65 ሺህ ብር

ይህ እጅግ በጣም ጥቂቱ ነው።

በመሆኑንም ፦

1ኛ. ማንኛውም የቴሌግራም ሆነ የዋትስአፕ የውጭ የማይታወቅ መልዕክት አትመልሱ።

2ኛ. በምንም ተአምር በትንሽ ብር ኢንቨስት አድርጉና ትርፍ አግኙ የሚሉ ሰዎችን አታናግሩ አትመኑ ተጠራጠሩ።

3ኛ. አሁንም በዚህ ውስብስብ ነገር ውስጥ ያላችሁ ተጨማሪ ብር እንዳትበሉ አቁሙ።

በቀጣይ በዘርፉ ያለ የባለሞያ አስተያየት እናቀርባለን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia